ወቀሳ ነቀሳ በተሻለ ደረጃ ሳይገኙ ከሆነ ነው አንካሳ።

 

ወቀሳ ነቀሳ በተሻለ ደረጃ ሳይገኙ ከሆነ ነው አንካሳ።
"ዬማዳንህን ደስታ ስጠኝ።
በእሽታ መንፈስ ደግፈኝ።"
(መዝሙር ፶ ቁ ፲፪)

 
(1) ያለን ነገር ማወቅ።
(2) ያለን ነገር ማጥናት።
(3) ያለን ነገር መመዘን።
(4) በአለ ነገር መነሳት።
(5) በአለ ነገር ላይ መደራጀት።
(6) ዬአለን ነገር ለመምራት በአለን ነገር ውስጥ ያለውን ዲስፕሊን ጠንቅቆ ማወቅ።
(7) በአለን ውስጥ ያሉ መልካም ነገሮችን ከደም ጋር ማዋህድ።
(ብስጭትን - ገረጭራጫነትን - ሞረድ አንጀትን ዬክፋት አውራ ጎዳናወችን አክ ማለት። አለን ለሚባለው ሁሉ ቀና ጎዳና ቀያሽ ነው።
ለዚህ ደግሞ እራስን መግዛት ይጠይቃል። በአንድም በሌላማ ዬውርጅብኝ ናዳ ዬሚወርድባቸው ሰብዕናወች በዬዘመኑ አሉ። እነሱን ዬራስ ለማድረግ አለን ዬምንለውን በጥንቃቄ ይዘን …
• ተደማጭ፤
• አሸናፊ ማድረግ ካልተቻለ ዬወቀሳ ተርቲም ዛሬን አያተርፍም፣ ለነገም ጭጎጎት ነው።
እዮባዊቷ ቅድስታችን ከዬትኛውም ተቋም በላይ ዬዘመኑ ዓውራ እንድትከስም ዬተፈረደባት አሳረኛ ናት።
• አጥኑት ዊዝደሟን።
• ሁሉን ረብ አድርጋ በከፍታ ላይ ትገኛለች።
• ሁሉን ነገር ታውቃለች። መሪዋ መንፈሥ ቅዱስ ነውና።
• ስለሆነም ተፍተፍ ዬለም።
• ባጉም ባጉምም አይታሰብም።
• ግልቢያም ትውር አይልም።
• ዬቂም ብቅልም ዬላትም።
• ያላት አርምሞ፤ ተደሞ፤ ጥሞና ፆም ጠሎት፥ ስግደት፤ ሱባዔ፤ ምስጋና፤ ዝማሬ፤ ቅዳሤ፤ ማህሌት ወዘተ …
እዮባዊቷን አለችን ማለት ይገባል፤ ነገረ ፍጥረቷ ቫወል ነው።
• እኛ እናሰግርሽ እንደ በቅሎ እንጋላብሽ ግን ቀኖናዋም፤ ዶግማዋም አይደለም።
• እዮባዊቷ ዬፖለቲካ ድርጅት አይደለችም።
• ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ለአገር ሰላም ብቻ ዬሚውል እንጂ ዛሬ ተሰርቶ ነገ ለሚፈርስ ግጥምጥም ጤዛ ዬፖለቲካ መንፈስ ገባሪ አይደለም።
• ነገረ ፍጥረቷ ቫወል ነው። ቫወል አልቦሽ ቋንቋ ዕብን ይሆናል።
ፎቶው ዙሪክ ባቡር ጣቢያ ላይ ነው። ኤልሲ ነበር ያነሳችኝ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።