አዲስ አበቤ ሰብዕዊ መብቱ ሲረገጥ ባለቤት የለውም። ምንም የመኖር ዋስትና የለውም። ልጆቹ በዬዘመኑ በአደባባይ ይረሻናሉ፤ ካሳ ተከፍሎት እንኳን አያውቅም። ይታሠራሉ፤ ይሳደዳሉ። ልጆቹ በሰማዕትነት ተዘክረው አያውቁም።

 

ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።
(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)
ማዕዶተ ርትህ ሰባዓዊነት።
ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ
የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር
አዲስ አበባ።
የማክበረዎት ዶር ዳንኤል ሆይ!
አንድ ጊዜም ይህን ጉዳይ አጽህኖት ሰጥቼ አንስቼ ነበር። አዲስ አበቤ ሰብዕዊ መብቱ ሲረገጥ ባለቤት የለውም። ምንም የመኖር ዋስትና የለውም። ልጆቹ በዬዘመኑ በአደባባይ ይረሻናሉ፤ ካሳ ተከፍሎት እንኳን አያውቅም። ይታሠራሉ፤ ይሳደዳሉ። ልጆቹ በሰማዕትነት ተዘክረው አያውቁም።
እኔ ይህ ለምን ሆነ ብዬ ሳስበው፤ ሳወጣ ሳወርደው አዲስ አበባ ላይ ራሱን የቻለ አንድ የሰብዕዊ መብት ኮሚሽን ግብረ ኃይል አለመኖሩ ይመስለኛል። በሚመጣው ምርጫም ብዙ ቀውስ ሊከሰት ይችላል። ከአሁኑ ችግሩን ኮሚሽነዎት ተረድቶ ከማንም ከምንም ከዬትኛውም ክልል ያልተዳበለ የአዲስ አበቤ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይከፍቱ ዘንድ በታላቅ ትህትና አክብሮት እጠይቃለሁኝ።
አስፈሪ ደማና፤ አስፈሪ ድባባ ነው ያለው። ከምርጫ ጋር ተያይዞ በጣም እጅግ በጣም ተጎጂ የሚሆነው አዲስ አበቤ ነው። የሚያሳዝነው ጉዳቱ እንኳን በአግባቡ አይዘገብም። የተጎጂ ቤተሰቦች ሥማቸውን እንኳን አናውቅም።
ከሰኔ 16/2010 ጀምሮ እስከ ሸኜነው ሳምንት ድረስ አዲስ አበባም የደም ከተማ ሆና ነው የባጀችው። ሟቾቹ ደመ ከልብ ናቸው። ሰፊ የቃጠሎ፤ የዝርፊያም መከራ ሊኖር ይችላል። የትንንቅ ጊዜ ነውና።
እባክዎት የማክበረዎት አቤቱታዬን ከጉዳይ ጥፈው አንድ መላ ይሠሩለት። እርግጥ ነው የቀውሱ ብዛት፤ የመከራው ዓይነት ልክ የለውም። ግን ዋቢ አላገኜም። ይህን ባለፈው ጊዜም አመልክቻለሁኝ። ዛሬም መድገም ግዴታዬ ነው።
አዲስ አበቤ ሁልጊዜም ማገዶ፤ ሁልጊዜም መከራ ተቀባይ፤ ሁልጊዜም ፍዳውን የሚይ ቅን ህዝብ፤ ደግ ህዝብ፤ ቻይ ህዝብ ነው። እንደ ተረገጠ የሚኖር ህዝብ። አቶ እስክንድር ነጋ ሁነኛው ህሊናው ነበር እስከ ቲሙ እስር ቤት ነው።
በመስከረም 5/2011 ኦነግ ሲገባ የተረሸኑ 5 አዲስ አባቤ ደመ ከልብ ሆነው ቀርተዋል። የሟቾቹ ስም እና አድራሻ፤ ምስላቸው እንኳን የለንም። ከታሠሩት 1300 አዲስ አበቤ እነኝህ አልተፈቱም እስካሁን። ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞም የየኔታዋ ልጆች እንዲሁ እስረኛ ናቸው።
በቀጣዩ ምርጫ ምርጫ ከኖረም ምን ሊፈጠር እንደሚችል ከባጀብን መከራ ተነስተን መገመት ይቻላል። ስለዚህ እባከዎትን የተሟላ መሳናዶ አዲስ አበቤ ላይ እንዲኖር ያደርጉ። እባከዎትን?
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
27.03.2021
ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።