የመቃብር ቀን መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓም።

 

የመቃብር ቀን መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓም።

 
የተረገምንበት መጋቢት 18 ቀን ነው።
በዚህ ቀን እኮ ነው መከራ ይምራን፣ መወረር ናፈቀን፣ መፈናቀል በገዳ ሽው አለን፣ መመንጠር ትዝ አለን ብለን ለማህበረ ኦነግ ሥልጣነ መንበሩን ያስረከብን። ወደ ሲኦል እራሳችን የጨመርንበት እርጉም ዕለት።
ጉዳዩ የተከወነው በመንፈቀ ሌሊት ነበር የዛሬ ሁለት ዓመት የለማ ዕፀበለስ ወደ ጋህነም የለቀቀን ግራጫማ ቀን። ያ ሁሉ ቀን ከሌት የደከምንበትን የነፃነት ተጋድሎ እልል ብለን ለማህበረ ኦነግ በግርባው ብአዴን ድምፅ ሥልጣኑን ለአረመኔው ማህበረ ሌንጮ የሸለምንበት የፀፀት ዕለት።
3. 5 ሚሊዮን ህዝብ እንዲፈናቀል፣ የጌዲኦ፣ የቡራዩ፣ የለገጣፎ ለገዳዲ፣ የባህርዳር፣ የአርሲ ዶዶላ፣ የባሌ ሮቤ፣ የወላይታ፣ የጋሞ፣ የመጠነ ሰፊው የአማራ ሰቆቃ ናፍቆን ማህበረ ሌንጮን አጨብጭበን ተቀብለን የዕንባ ስንቅነትን የተሸከምንበት ጥቁር ጠራጠሮ ቀን መጋቢት 18 ቀን። የመቀብር ሥፍራ ኦሮሙማ።
ሁለት ዓመት ሆነን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቆ ለተነሳው ወረራ፣ መስፋፋት ፖሊሲው አድርጎ ለሚጓዘው ለጨካኙ ኦሮሙማ ፈቅደን እና ወደን ምርኮኝነቱን ከተቀበልን። አቤት ስትቱ ሰው ክንብንቡን አውልቆ፣ ለጥቅም ተንበርክኮ ገበሮ ሆነ? ቁጥር ስፍር የለውም።
ለአራጅ ከተመቻቸን ድፍን 24 ወራት። የእምነት ተቋማትን እንዲፈልሱም ከፈቀድን እንሆ እንደዋዛ ሁለት ዓመት። የኦዳ መሳፍንታት ዝምንም ካሉ በበቀል፣ በመስቃ በዲስኩር ከሚቀጠቅጡን ሁለት ዓመት ተቆጠረ።
እጃችን አጣጥፈን የለማወአብይ ሲኦላዊ ዲሞግራፊ መሞከሪያ ጣብያ ለመሆን የፈቀድንበት የመቃብር ቀን መጋቢት 18? በጥቂቱ የወረደውን መከራ በምልሰት እንሰበው። ጎንደር ለድል ካበቃ በኋላ እንሆ በዕለቱ ሌላ የአፈና ተግባር እዬተከወነ ነው።
ቂመኛው የኦነግ ልብ ፈርኦነዊነቱን እያሳዬን ነው። ለዚህም ነው ብልሁ ተንባይ ነብዬ ብጄ አሳምነው ፅጌ የደረሰው መከራ ከ500,ዓመት ከነበረው የከፋ ነው ተከበናል ያሉት።
ከቂም በፀዳ፣ ከበቀለኝነት በራቀ ሁኔታ በሁለት ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ ከሰረች እንጂ አላተረፈችም በማስተዋል ሆነን ከመረመርነው። 48 ወራት ሙሉ ዕንባ ነበር። ያልታዬ የጭካኔ ዓይነት የለም። ሁለመናችን ነው ያራገፋት።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ዕውነትን እና መርህን እንወግን ሰው ከሆን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።