የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አይቻልም። • የዛገው ብረት በማረተ ሃሳብ … ???

 

የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አይቻልም።
• የዛገው ብረት በማረተ ሃሳብ … ???
"ኃያል ሆይ በክፋት ለምን ትጎዳዳለህ?"
"ሁልጊዜስ በመተላለፍ?"
(መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፩)
 

 
የዛገው የጉራጁ ኢህዴግ ኦህዴድ የማረቱ ምርኩዞቹ የዚህን የአዲስ ዘመን መንፈስ ሰላሙን በማወክ ትንፋሹን ማባከን ቀዳሚው መስካቸው ነው። የማያዋቀው ነገር ግን የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አለመቻሉ ነው። አንድ ጊዜ ተፈጥሯል። እንደ ጉርሻ ዋጥ ተደርጎ ጸጥ የሚባልበት አይሆንም። አዲስ ሃሳብ ምጡ እስኪ ወለድ ድረስ ነው። ከተወለደ በኋዋላ ግን በራሱ ጊዜ እድገቱን መቀጠሉ የተፈጥሮ ህጉ ነው።
አንድ በህክምና ዶር. የተመረቀ ሰው በዕወቀቱ ላይ የተለዬ ስልጠና እዬወሰደ ያዳብረዋል እንጂ እንደገና ወርዶ 7ኛ ክፍል ላይ ስለተፈጥሮ ሳይንስ ልማር አይልም። ምክንያቱም አቅም ፈጣሪው አዕምሮ ወደላይ ከመዝለቅ በስተቀር ወደ ታች መውረድን ስለማይፈቅድለት።
አሁን ያለውን ቡቃያ የለወጥ መሻት በዛገ የምርኩዝ ጋጋታ፤ በወዬበ ኳኳቴ በፈለገው ዓይነት መጠራቅቅ መቋቋም አይችልም የአዳማ ሥርዕዎ መንግሥት። ይህ የለውጥ መንፈስ ከብሄራዊ አልፎ፤ አህጉራዊና ዓለምዓቀፋዊ ጫናም ፈጥሯል። ረቂቅ ነው። የፈጠረው ጫና በፍጹም ሁኔታ ኦህዴድ በሚያስበው መልክ በግርድፍ የሚሾከሾክ የገብስ ቆሎ አይደለም። በፍጹም። ሃሳብ ዬለም ብሎ አይመፃደቅ።
• መታዬት።
የዛገው ሙጣጭ ሃሳብ አዲሱን የለውጥ መንፈስን መቀበል ብቻ ሳይሆን ከአዲሱ መንፈስ ጋር ለመቀጠል እንኳን በግትርነት የሚሆን አይሆንም። የሚመጥን የአዕምሮ ብቃት፤ የሰብዕና ንጽህና፤ የሥነ - ምግባር ሞራል፤ የሥርዓት መዋቅራዊ ደርጁነት የለውም። ያስፈራውም ይሄው ነው። ቀውስ ባጀቱ የሆነውም ለዚህ ነው።
አሁን ኢትጵያ ከዬትኛውም ፍልስፍና ያፈነገጠ እና የወጣ ተፈጥሯዊነትን አቤት! ወዴት! ያለ አዲስ የሃሳብ ልቅና ላይ መገኜትን ትሻለች። ይህ ስለፈለገችው ሳይሆን የ21ኛው ምዕተ ዓመት ግሎባል ስጦታዋ ነው።
ስለሆነም ከአራዊት መንጋ፤ ከዘረፋ ጅረት፤ ከደም ማፈሰስ ሱስ፤ ከመስፋፋት ትዕቢት፤ የምትላቀቅበት አዲስ የሃሳብ ዓዕማደ ተስፋ ላይ ናት ባልልም በሃሳብ የላቁ ሰብዕናዎች ግን አያለሁኝ። ይህን የሃሳብ ቡቃያ የመሸከም አቅም የለውም እንኩቶው የዛገው የ50በ60 አዲሱ አብይዝም። ያረጠ ነው። ልማር ልስተካከል ከአረንቋ ልውጣ ካለ ድሪቶውን ሙጃውን አስወግዶ አዲስ ጆሮ ይግዛ።
የዓለም መርህ ያለው የሰዋዊነት መንፈስ ላይ ነው። ሰው መሆን! ለሰውነት ጠበቃ፤ ጋሻ፤ መከታ መሆን! ሰውን እንደ እንሰሳ የሚያታይበት፤ ሰውን እንደ ግዑዝ ከረጢት ነገር የሚታሰርበት - የሚፈታበት፤ ሰውን በጅራፍ ተዘቅዝቆ ታስሮ የሚቀጣበት፤ በራስ ወገን የመርዝ መፈተኛ የሚሆንበት፤ ሰው እንደ በግ የሚሸለትበት ዘመን በማክተም እና ለማስቀጠል በሚባዝኑ የመንፈስ ደኃወች መሃከል ነው ጦርነቱ።
ቀደም ባለው ጊዜ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ይውደቅ እንጂ ከዛ በኋዋላ ችግር የለም የሚሉ አመክንዮዎች በርካታ ስለነበሩ፤ መንፈስን ጥግ ለመስጠት አልተቻለም ነበር። አስፊሪ የሆኑ የጨለማ አምክንዮች ነበሩ።
አሁን ነገስ ምን? ለሚለው አስከ ታች ድረስ አቅም እያበቀለ፤ አቅምን በብቃት ኮትኩቶ እያበቃ የመጣ ድርጁ ኢትዮጵያዊ መንፈስ አለን ወይ ይህም ሌላ ሞጋች አምክንዮ ነው። ቢኖርስ ይፈቀድለታል ወይ?
ይህ የአቅም ተከታታይነት በተጠባባቂ አቅም በሙሉ ስብዕና የተገነባ ሊሆን ይገባል። ይህን አቅም ተተኪ አልባ ለማድረግ ያለው ቁልፍልፍ ነገር በዘመነ ህወሃት ከነበረው የአሁኑ እጅግ የከፋ ነው ጥልፍልፍ ነው። የኃይል አሰላለፉ ስብጥር ስንቅር ነወ። ለዚህ ነው ብዙውን ጊዜ በዝምታ እማልፈው።
አንድ ሰው ቢወድቅ ሌላ ተተኪ ብቃት ያለው ሊኖረው ይገባል። አንድ ሰው አቅም አንዲኖረው እርስ በርሳቸው ረቂቅ በሆኑ፤ ዘመኑ በሚጠይቃቸው መስመራዊ፤ መንፈሳዊ፤ ሞራላዊ፤ ሰዋዊ፤ እኛዊ መሠረት ያዬዘ ዲስፕሊናዊ አቅም አለን ለማለት የዛን ባለ አቅም ዲስፕሊን ሊሸከም የሚችል አለን ወይ ብሎ መጠዬቅ የህሊናዊነት ጉዳይ ነው።
ኦሮማራ ኢትዮጵያን የመምራት አቅም ሳይኖረው ነበር አቅም የለገስነው። ቅደመ ሁኔታም አላበጀነም፤ ውልም አልሰራልነትም ነበር። በተጠቅለል ተጥቅሎ የገማ እንቁላል ሆነ። ወይ እሱ ወይ ኢትዮጵያ ሊተርፉ አልቻሉም። ያ ሁሉ ግሎባል ድካም ለማህበረ ሌንጮ መደንከሪያ ሆነ። ዜጎች በአገራቸው ላይ የመኖር ዋስትናቸው አጡ።
በራሱ ጊዜ የበቀለው የተስፋ አቅም ሙት በቃ ተፈርዶበታል። በገማ እንቁላል ላይ ተስፋን ማጨት ስላማይቻል። በዚህ ውስጥ የስሜን ፖለቲካ ድቀት እና የኢትዮጵያም ተስፋ በማስቀጠል ቀርቶ ከዚህ ለመነሳትም ፈጽሞ ያልተደፈረ አመክንዮ ነው። ይህም ብቻ አይደለም የቅድስት ተዋህዶ መከራ እና ከፖለቲካውም ከአገሯም መሰደድም ሌላው የመከራው መንኮራኩር ነው።
የጥገና ለውጡ በራሱ ተጋድሎውን የመሸከም አቅም አምጦ ሊወልድ ግድ ይለው ነበር። ግን ካለ አቅሙ በተለጠጠው ተቃባይነት በራሱ ጊዜ ዳጥ ውስጥ ነው የወደቀው። ተባባረን ያስወገድነው ሥርዓት ከእነ ሙሉ መዋቅሩ ለማስቀጠል ያለው ፋታ የለሽ ግብግብ የነገን ተስፋ ያረግበዋል።
በተለይ በተፎካካሪ ጎራ ያሉት የአማራ ሊቃናት የገነቧቸው የፖለቲካ ድርጅቶች በዓዋጅ በገዳዋ እቴጌ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ የፖለቲካ አመንዝራነት መቃብር ተልከዋል። በአማራ ተጋድሎ ከተቀቀሉት ማህበረሰቦች ጎልተው የሚታዩ አንድም የአማራ ሊቃናት ወደ ቀጣዩ የምርጫ ውድድር አይገቡም። ጎንደር፤ ጎጃም በልሙጥነት። በገፍ መከራ የተቀበሉ ማህበረሰቦች።
የስሜን ፖለቲካ በማግለል ዘመቻ ላይ እዬኳተነ የሚገኜው የኦዳ ሥሯወ መንግሥት እና የገዳ ምርጫ ቦርድ ሂደቱ በአንድ እጅ ማጨብጨብ ነው የሚሆነው።
ኦርቶዶክስ እና ተዋህዶ ከፖለቲካ ለማውጣት ያለው ረቂቅ ዘመቻ የተሳካ ቢመስልም እነኝህ ኃይሎች „ጸጥተኛ ፤ ጭምታዊ ድምጽ silent majority“ የሚባለው ውስጥ ቀላል የማይባል ኃይል እኔን ጨምሮ እንዳላቸው አይታወቅም።
የአማራ የህልውና ተጋድሎ መስዋዕትነቱ ዕውቅና እንዳያገኝ ከወያኔ ባላነሰ ውጪ ሐገርም ሰፊ ፈተና ነበር። ዛሬም። የአማራ የህልውና ተጋድሎ እጅግ በተሻለ ሁኔታ ግራ ቀኝ እስሩን ጥሶ ወጥቶ እኩል እውቅናውን ማስጠበቅ ቢቻልም ይህን ዲስፕሊን ከግርግር ፖለቲካ አውጥቶ ስኩን ድል ያገኝ ዘንድ ያለው ተስፋ ግን ሙቀቱን ለመለካት ጊዜ የሚጠይቅ ይመስለኝ።
በአደባባይ ከሚሰሙትም፤ ከሚደመጡትም በላይ ያሉ ረቂቅ የመንፈስ ሃብቶች አሉት ተጋድሎው። ስለምን? አዲሱ ሃሳብ ስለነገ ያለው ዕይታ ያልደፈረሰ፤ ያልተስረከረከ ግልጽና ቁልጭ ያለ በመሆኑ ምክንያት አቅሙን አቅም ለማድረግ በቅርበት ውህድነትን ዘመን በራሱ ጊዜ፤ ፈጣሪ አምላክም በኪነ - ጥበቡ ስለባረከው። ይህ ማለት ግን ዲስፕሊኑን መሸከም ካልተቻለ ያ ቅምጥ ኃይል ልቦናው ሊሸፍት ይችላል። ሊበተነም። እኔን ጨምሮ።
የሆነ ሆኖ ከዚህ አፈንግጦ የዛገው ብረት በማረተ ሃሳብ ጊዜውን በጅ በለኝ ቢለው ብዙም የሚያወላደው አይሆንም። ጅው ወደ አለው ገደል ራሱን የሚለቀው ራሱ ይሆናል።
ቅራኔው እዬተካረረ፤ እዬተወጠረ በሄደ ቁጥር በራሱ ነፍሶች ላይ የዘለዓለም የበቀል ስንቅ ተክሎ ያሸልባል። ትናንት ዛሬ እንዳልሆነ ሁሉ ነገም በራሱ ቀን ስለሚመጣ ዛሬ ሊሆን አይችልም።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።