#ግን ሲገነግን።

 

#ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ - ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ በተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
 

 
#አሳቻ ጠቅላይ ሚኒስተር ያላት አገር በህማማት።
አሳቻነት ፈርጀ ብዙ፣ ወዘ ብዙ፣ ባህሬ ብዙ፣ ስሜተ ወዘተረፈ፣ መነሻውም መድረሻውም የማይታወቅ መስቀለኛ መንገድ ነው።
አጤ ዝናቡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሰብዕናቸው አሳቻ ነው። እስከ ዛሬዋ ዕለት እሳቸውም ማህበራቸውም አላወቁትም ነበር ዛሬ ይታወጅላቸዋል።
ዓዋጅ! ዓዋጅ! ዓዋጅ!
የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!
ጠቅላይህ ሰብዕናቸው አሳቻ ነው!… ንቃ!
እቴጌ መሬት ሆይ!
 
የዓለሙ ሎሬት አድርገሽ የሾምሽው፣ የሸለምሽው፣ የዓለም የሰላም አባትሽ ሰብዕናው አሳቻ ስለሆነ ነው አንቺም የተሸወድሹ፣ ኢትዮጵያንም ተጨማሪ መጭካኔ አሳር ያሳከልሽባት። ለአሳቸነት ዕውቅና ያለወቅቱ?
 
አሳቻ መንገድ ላይ የምትገኜው ኢትዮጵያ አሳቻ መሪ ስላላት ነው አሳቻነት ራዕዮዋ የሆነው። በአሳቻነት ራዕይ አሳቻ ትውልድ፣ አሳቻ ታሪክ፣ አሳቻ አደራ፣ አሳቻ መሆን፣ አሳቻ መኖር፣ አሳቻ ቤተሰብ፣ አሳቻ አዬር መኖር ግድ ነው።
ይህ በዬትም ዓለም ተፈጥሮ የማያውቅ የርግማን ናዳ ዕውቅና የሚሰጠው አልተገኜም። ለዚህ ነው። "ዶር አብይ መሪያችን፣ ኤርትራ አገራችን" ጉልሁ ሞቶ ሆኖ ታውጆ በአደባባይ ያዳመጥነው። 
 
ዕውነት ሸቀጥ ካልሆነ በስተቀር፣ መርኽ ጨርቅ ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያ ወደምን እዬሄደች እንደሆን የሚታወቅ ነገር የለም። እንሰሳዊ ይሁን? ግብረ ሰዶማዊ? ዋቄፈታዊ ይሁን አይዲያሊዝምአዊ? የመቃብር ሥፍራይዝም ይሁን ጋህነሚዝም? አይታወቅም።
ኢትዮጵያ እንደዚህ ዘመን የደረሰባትን መከራ፣ ያለችበትን ሁኔታ ለመመርመር ከብዶ አያውቅም ነበር። በላይ በላዩ የሚደፋው የማዕት ናዳ፣ የፌክ ድሪቶ ገለባን ከስንዴ የመለያ፣ የማንዘርዘሪያ አቅም አልተገኜም።
 
አቅም ብቅ ሲል ግርዶሽ ሠሪዎች ከተፍ ብለው በሰላ ምላሳቸው ከታትፈው አቅጣጫ ያስቀይራሉ። የሰለጠኑበት ያ ስለሆነ።
… እንጂ ሱዳን ባቅሟ 50 ኪሎ ሜትር ጥሳ ገብታ ለዛውም ተጋብዛ፣ በይፋ በአደባባይ የስሜን ፖለቲካ አመድ ሆኖ፣ ኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘን እዬነደደች መጠጊያ አለ ከተባለ ከአቶ ሙስጠፌ መንፈስ ውስጥ ብቻ ነው። 
 
ለዛውም እሱም ከስሩ ለመድፋት ምርኮኛው አቶ አባ ዱላ ገመዳ ጥሪያቸው ነውና ፍርስርሱን ለማውጣት የውስጥ የነቀርሳ ከነቲራ ናቸው።
መንገዱን አሳቻ ያደረገውም የሳቸው ዬስው ጠቅላይ ሚኒስተርነት የአቶ አባ ዱላ መከደን ነው። አደባባይ ላይ አጤ ዝናቡን ማይካቸውን ሰክተው ኢትዮጵያን አነደዷት።
 
እዬነደደች፣ እዬወደመች፣ እዬታረደችም ዓይናማነት ሆነ ጆሮም ተሰናበተ። አካልም ተከዳ፣ እንደራሴነትም ተሸሸ፣ እኔነትም ተዋሸ። ስለምን? ሁሉም አሳቻ መንገድ ላይ ስለሆነ። እኔ ግን አሳቻ መንገድ ላይ አይደለሁም። ጎዳናዬ ጥርት ባለ ፍላጎት ውስጥ ነው።
አሁን የውጭ አገሩን የመቃብር ሥፍራ የድጋፍ ሰልፍ እኔ እማዬው ሰልፋን አዘጋጁም፣ ሰልፋን መሪውንም ስታስቡት አሳቻ ነው። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሰንደቅ አላማ አብዝቶ የሚጠዬፍን ማህበረ ሌንጮን "ሎንግሊብ" ከማለት በላይ ውርዴትም፣ ክህደትም ውርዴም የለም።
 
#ግን ሲገነግን።
 
አጤ ዝናቡ ለወደፊት ተፈላጊ ናቸው¡¡¡ ሰኃራ በርኃ እራሱ ማመልከቻ አስገብቷል አሉ። ዝናቡን ያንዠከዥኩለት ዘንድ¡
አሳቸው ውሸት፣ ዕብለት፣ ቅጥፈት ኦክስጅናቸው ነው። ቅፅበታዊ ስለሆኑ በቅፅበት ሲቀያዬሩ ማህበራቸውም አብሮ ብልጭ ድርግም ይላል። ጀርመኖች ብሊንግ ብሊንግ ይሉታል። ሰውነት ሲሸሽህ አሳቻነት አንተን ይገልፅኃል።
 
ሌላው ቀርቶ እኔ የትኛውን የሰብዕና አይነት ጠቅላዩ እንደሚወክሉ ግራ ይገባኛል። ሲቃ ይሆን ግራጫ? ቡላ ይሆን ኮረኮንች? ልሙጥ ይሁን ሙልሙል? 
 
ይህ ይግባን። ይህ ሲገባን ግርዶሽ ሰሪውም፣ አንጣፊውም፣ ዝናብ አውራጁም፣ የኢማጅኔሽን ልዑሉም ጥልቅ መሰሪ የፍርሰት ሲቃ ይገባናል።
 
ከዕለታዊ ትርምስ ወጥተን በዘላቂ ጉዳዮች ላይ አትኩሮት፣ በዘላቂ የመፍትሄ ጎዳናዎች ላይ ጥናት፣ በድንግል ሰብዕናዎች ላይ ውስጥነትን ማስከን እንችላለን። 
 
አልጋው ረግቧል። በረገበ አልጋ ላይ ጥገናውም ሚስሊዱም መና ናቸው። ብላሽ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/03/2021
ጎዳናዬ ድንግል ሙሴን መፈለግ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።