ቤርሙዳ ትረያንግል።

 

ዕለተ ሰኞ #ማዕዶተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ"
(ትምህርተ ዕንባቆም ፫ ቁጥር ፲፯)
 

 
#ማዕዶተ ጠባቂ። ዕለተ ሰኞ።
#ማፈር ውርዴት አይደለም።
#ውርዴው ካፈርኩ አይመልሰኝ እንጂ።
ከልባችሁ ሆናችሁ ቅኖቹ ሆይ አንብቡት።
ሁሉም አጀንዳዎች አቅም በፈቀደው ልክ የሚከወንበት ዕለት ነው ማዕዶተ ጠብቀኝ። ብቻ መከራው ነደደ ኢትዮጵያዊው ተፈጥሮም ተፈቅዶለት በማህበረ ፈርኦን ጭካኔ ተናደደ፣ የሰበር ሱናሜ ዋጠን።
ሦስት ዓመት ሙሉ ካለ ሠበር ውለንም አድረንም አናውቅም። በዬሰከንዱ ሰብር ነው። የወይኗ ልጅ ለዚህ መለከት ነው። መከራውን በልኩ አዳምጠን የሚሆን ጎዳና ለመቀዬስም እኛ ሰው ነን። ማሽን አይደለን ከአቅም በላይ ሆነ። ሁሉ ነገር።
ሆሊውድ ልባም ቢሆን መሄድ የነበረበት ኢትዮጵያ ነበር። ኖቤልም ለኦስካ ቦታ መልቀቅ ነበረበት። ጆከርም አክተርም የሆነ መከራ ከኦዳ ሥርወ በገፍ ነውና።
እርግጥ ነው ብረት የሆኑ ሰብዕናዎችን አያለሁ። ቀንም ሌትም የሚደክሙ። ፈጣሪ አብዝቶ ይጠብቅልን። አሜን።
#ማፈር እንዲህ ከባድ ነውን?
#ግን ማፈር እና መብት ምን እና ምን ናቸው?
መፍትሄ …
መፍትሄ …
#መፍትሄ ለፍትኃት መቼ ከች ይል ይሆን?
መፍትሄ ያለው "በቃ!" በበቃ መስማማት ሲቻል ነው። "በቃ!" የሚል የወል ድምፅ በሌለበት መፍትሄ እንደምን ይታሰብ?
#ቋንቋ ከማይችለው አረንቋ
ውስጥ መኖር ያባት ሰምጠናል።
 
ገልምተናልም።
 
" ዶር አብይ መመኪያችን … ?" ለዚህ የገደል አፋፍ ምን አቅም ኖሮን፣ በዬትኛው መቅኖ በዚህ ውስጥ ሰውኛነትን፣ ተፈጥሯዊነትን፣ ተስፋን ትውልድን እንጠብቅ?
 
አንዳንድ ጊዜ ብቻዬን ሆኜ የማህበረ ሄሮድስን ቅኝት የህወሃት የጭካኔ ዘመን እምንናፍቀበት ቀን ይመጣ ይሆን እላለሁኝ? ሥርጉተ አበደች ብትሉኝ በፀጋ ይስተናገዳል። ያው ፈንጋጣ ነኝ። ገድሜ እምኖረውም እሚረዳኝ ስለለ ነው። ቋንቋ ሊሸከመው ከማይችል አረንቋ ውስጥ መገኜት መታደል ነው ሰምጠናል።
 
የጭካኔው ዓይነት፣ የጭካኔው ይዘት፣ የጭካኔው ቁመና፣ የጭካኔው ተለዋዋጭነት፣ የጭካኔው ፍጥነት፣ የጭካኔው ሆድ ዕቃ እሱን ለመድፈን ያለውን የሰበር መንጋ መንጋጋት አስተውላችሁ ህይወት በኢትዮጵያ፣ ብትን አፈር በኢትዮጵያ እሰቡት እስቲ? ዕውን ሰውነት ከተሰጠን?
 
አጤ ዝናቡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በዬትኛው ቀዬ ብቻቸውን መንቀሳቀስ ይችላሉን? ነፃነት አዳይ ነኝ ባዩ የፓርኩ ልዑል፣ የፒኮክ ንጉሥ በኦዳ ቤተመንግሥታቸው ውስጥ እንኳን አይችሉም? ነፃ አይደሉም መሪው እራሳቸው። ተጠልፈዋል በኦፋዎች። ቤርሙዳ ትረያንግል።
 
ይህን ተሸክመህ " አብይ መመኪያችን፣ ኤርትራ አገራችን " የትኛው ፕላኔት ይሆን ሰው እዬኖረ ያለው? የሰውን የሰው ሥጋ የሚበላበት ባርባርያን ዘመን ላይ ተወስደህ በዛ ትምክህት እግዚአብሔርን መካድም ነው።
 
እግዜአብሔር አላህ የሰውን ልጅ የፈጠረው ለቤተ - መቅደስነት ነው። ያ አካልህ ተዘልዝሎ ቋንጣ ሲሆን፣ እህል ውኃ ሆኖ ሲበላ ሲጠጣ፣ ከተሞች ለመግባት ለመኖር በሰው ሬሳ ጠረኑ አላስቀርብ ብሎ ያ ውርዴ መሆኑ ቀርቶ ትምክህትህ ሲሆን፣ አንተ ራስህ የለህም። ግዑዝ ነህ።
 
የሰው አካል ለውሻ? የሰው አካል ለጅብ? ለቀብር በሠራዊት ጥበቃ? በጦርነቱ ምን ያህል ሰው አለቀ? መርዶ ተነግሯልን? የታገቱ ልጆችህ የት ናቸው? የተሰወረው ወገን ስንት ነው? ጉድጓድ ሲናፍቅህ ለአንተ አዘንኩልህ፣ አፈርኩልህም። መውደቅም መሳሳትም መኖር ነው። ዲያቢሎስነት "መመኪያ" ግን ሲኦላዊነት ነው። 
 
በሰውኛ ቋንቋ አንድም ነፍስ ትሁን የአገርህ ልጅ፣ ደምህ፣ ህይወትህ በውጭ ወራሪ ኃይል ስትደፈር ይህ ካልቆጨህ አንተ ማን ነህ ብዬ እንድጠይቅህ እገደዳለሁ። 
 
ሁለት ሰይጣኖች ህወሃት እና ኦህዴድ በሰይጣኑ ግንድ በሄሮድስ መለስ ዜናዊ ተፈጥረው በአረመኔነት ተቦክተው ተፈጥረው የሚያደርጉት የሲኦል ፋክቻ እና የአገራዊነት ዕሴትህ፣ ሰውነትህ ዕውነትን ማዬት ተስኖት የዚህ ሁሉ መከራ አምራች ጭካኔን መመኬዬ ስትል፣ ማፈር ሆይ! ተነንክን? እንድል እገደዳለሁ። 
 
ከመመኪያነት አልፎ ሙሴነት እኮ በውል ተፈረመበት። ከዲያቢሎሳዊው የመቃብር ሥፍራ አብይዝም ግን በቀል፣ እልቂት፣ ውርዴት፣ ከንቱነት ነው የተሰጠን። 
 
ማዬት ማመን ካልሆነ ያልተፈጠርከው ማዬትን ማዬት ያልቻለው ድውይ ሰብዕናህ ነው። ሰው ለወገኑ ነግ ለእኔ ካላለ ነገም ጨለማ ነው። ሰው የዳማ ጨዋታ አይደለም። ማፈር ውርዴት አይደለም። ካፈርኩ አይመልሰኝ ነው የውርደት #ውርዴ
#ተፈጥሮን የሳተ አሳቸነት ነቀዝ ነው።
 
ሁሉም ቂመኛ ከሆነ፣ ሁሉም በቀለኛ ከሆነ ትውልድ አይተርፍም። ፈፅሞ። ዲሞክራሲ በለው፣ ፌድራሊዝም፣ ፌድራሊዝም በለው ኮንፌድራሊዝም ከቂም ጋር ማህበርተኛ ከሆነ እራሱንም ተፈጥሮንም የሸሸ አሳቻ ነው።
 
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለኢትዮጵያዊነት እንጂ ኢትዮጵያ ጋር እዬተፎካከረ ላለ አጋንንት መጋረጃ ሊውልም አይገባም። በራሱ በሰንደቅ ዓላማው ክብር ላይም ማላገጥ ነው። ዲስክርምኔሽንም ነው እሱን ለብሶ እሱን የሚጠዬፋትን " ዶር አብይ መመኪያችን፣ ኤርትራ አገራችን" ማለት።
 
ኤርትራ አገራችን ነበረች። ዛሬ ግን ተወደደም ተጠላም ጎረቤታችን ናት። ኤርትራ አገራችን ስትል ፕሬዚዳንት ኢሳያስ መሪያችን፣ ሻብያ ፓርቲያችን እያልክ ነው። ይታይኃል ዕውነት ስትቀብር፣ መርህ ስትገድል። ምኞት መሆን አይደለም።
 
አብይዝምን፣ ሻብያይዝምን መደገፍ መብት ነው። ልሙጡን የነፃነት ቃና አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቁን መልበሰም ከማንም የሚጠዬቅ ፈቃድ የለም። 
 
ዕውነቱ ግን ሊደፈር ይገባል። ሠልፈኛው የለበሰውን ሰንደቅ ለዶር አብይ አህመድ እንዲሁም ለግብረ ኃይላቸው፣ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ብታለብሷቸው ይጠዬፋታል። 
 
ስለምን ፕሬዚዳንቱ ጎንደር ሄደው ፋሲል ግንብን ማዬት ተሳናቸው? ያን ያህል ሲመላለሱ አጤ ዝናቡ ዶር አብይ አህመድ አጤ ፋሲልን ለማዬት ስለምን ወኔው ሸሻቸው? ኢትዮጵያዊነት እዬሸሹ ስለሚገኙ ነው። ኢትዮጵያ ለቀብድ ማያዣነት ብቻ ስለሆነች ነው።
ንግዱ በብሔራዊ ሰንደቃችን አይሁን። ክብር፣ ማዕረግ፣ ድል፣ ሱቅ በደረቴ አይደለም እና። እናስተውል። መሳሳት ሰውኛ ነው። በስህተት ውስጥ ለመኖር መፍቀድ ግን የተፈጥሯዊነት ጥሰት ነው። 
 
ውል ይኖራል። ውሉ ግን ሰውኛ ጠረንን ከጣሰ የኢትዮጵያዊነትን ትርጉም፣ ንባብ፣ ሚስጢር አለማስተዋል ነው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/03/2021
ጎዳናዬ ሰባዕዊነት ነው።
ትምክህቴም እራስን አለመሸሸት ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።