አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል።

 

አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል።
"ዬደም ሰወች እና ሸንጋዮች ዘመናቸው ግማሽ
አይሞላም።:እኔ ግን አቤቱ እታመንኃለሁኝ።"
(መዝሙር ፶፪ ቁጥር ፳፫)
 

 
ትግሉ የአልሞትም ባይ ተጋዳይነትን ስለሚጨምር የሚያስከፍለው መስዋዕትነት የከፋ ይሆናል።
ግን አዲሱ ሃሳብ በአዲስ አቅማዊ ስልትና ስትራቴጂ በጥበብ ስለሚመራ አሸናፊ መሆኑ አይቀሬ ነው።
ይህ ስለተፈራ ነው አብሮነት የተሰረዘው በገዳ ምርጫ ቦርድ። አብሮነትን የገዳ ምርጫ ቦርድ በድፍረት እና በማናህሎኝነት ሲሰርዘው ኢትዮጵያን ሰርዟታል። ኢትዮጵያ መለያ ማልያዋ አብሮነት ነውና።
በሌላ በኩል አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል። አሰምሌሽንም ተፈጽሞባቸዋል። ይህ በጣም ረቂቅ አመክንዮ ነው። በእኔ ውስጥ እኔ ስኖር ብቻ ነው ሊታዬኝ የሚችለው።
አንድ ኢትዮጵያዊ ተቋም ሲደረመስ በእኔ ውስጥ ያለው መንፈስም አብሮ መደረመስ ታውጆበታል ማለት ነው። አብሮነት ጆኖሳይደ ሲካሄድበት እኔንም ይጨምራል።
• እኔ ተቋሜ ኢትዮጵያ ናት።
• ኢትዮጵያ ደግሞ የአብሮነት ማህደር ናት።
• አብሮነትን ሥሙ ትውፊቴም ትሩፋቴም ነው።
• ትውፊቴን የፖለቲካ አመንዝራዋ የገዳ ልዕልት ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ ሲፈጽሙት በእኔንም ላይ ፈረዱ።
እሳቸው 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዛገው ገዳቸው ላይ ነው ያሉት። እኛ ደግሞ 21ኛው ምዕተ ዓመት ሰውኛ እኛዊነት ላይ እንገናኛለን። መመጣጠን ያልቻልነውም በዚኸው አመክንዮ ነው።
„ጸጥተኛ ድምጽ silent majority“ አባልተኞችም የቀና ቀን ጠባቂዎች ናቸው። ስብጥራቸው ሁሉንም የአቅም አይነት ያሟላ ነው። እነኝህ ከሁሉም ጋር ያልነበሩ ድርጁ መንፈሶች የበቃ የአቅም መቅኖ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው።
ለእነኝህም ተቋማቸው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ስለዚህ እነኝህ ጨዋ ስኩን መንፈሶችም በድምጽ አልባው የገዳ የምርጫ ቦርድ ቦንብ ተደርምሰዋል።
አስተካሿ ተኳሿም የገዳዋ ልዕልት ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ ናቸው። ጸረ አብሮነት። ጸረ የአማራ ሊቃናት ልቅና። ሴቶች ቂመኛ በቀለኛ ሲሆኑ ከማዬት በላይ የከረፋም የመገለም ነገር የለም። ይጎፈንናል።
እኔን መሰል ነፍሶች የዛገው ሃሳብ የእኔ ሳይላቸው ረስቷቸው ወይንም ባሊህ ሳይላቸው የቆዩ በመሆኑ ባለቤት መሆን የሚችል አዲስ ሃሳብን ለመቀበል ንጹህ ሰሌዳ ናቸው ማለት ይቻላል።
የዚህ መንፈስ ቅን እና ንጽህና ያለው ስለሚሆን ወደ አዲሱ ሃሳብ የመጠቃለል ዝንባሌያቸው ሰፊ ነው። ለዚህ ነው ጭምት፤ የሰከኑ፤ በሳል ፖለቲከኞች …. የማይበልቁት።
ፖለቲካችን ከካድሬ ግርግር እና ኳኳቴ፤ ከፕሮፖጋንዳ ታንቡረኛ ወጥቶ ስክነት አስፈልጎኛል ወግዱልኝ እያለ ነው። ነፍስ ያለው ጆሮ ከተገኜ።
እኔ እንደማስበው እነዚህ መንፈሶች „ጸጥተኛ ጭምታዊነት ድምጽ silent majority“ ያልተነካ የአዕምሮ አዱኛ ያላቸው፤ በስብዕናቸውም አንቱ የሆኑ፤ አደብ የገዙ፤ ጭምቶች፤ የማይቸኩሉ፤ በቁጥርም ብዙኃን በመሆናቸው እጅግ ጠቃሚ ሃይሎች ናቸው።
በተለይ እነሱ መስጥረው የያዙትን ምኞት ጋር አዲሱ ሃሳብ ካፈለቀው „ከአዲሱ ሃሳብ“ ማህጸን ጋር ተመሳሳይ ወይንም ተቀራራቢ ከሆነ ለመጠቃለል ጊዜ አይፈጅባቸውም።
ምክንያቱም ጊዜና ወቅት ጠበቂዎች በመሆናቸው የተስፋ ዘበኞች ለመሆን ማቄን ጨርቄን ሳይሉ በቀጥታ አቅማቸውን ለአዲሱ አስተሳሰብ ይሰጣሉ። ያዘሉት፤ አሽኮኮ ያደረጉት ቅምጥ ሃሳብ ወይንም ጣዖት ሰብዕና የለምና።
„ጸጥተኛ ድምጽ silent majority“ ቅኖች ናቸው። ህሊናቸውን፤ ውስጣቸውን ብቻ ሳይሆን ሰብዕናቸውን ፈቅደው ይሸልማሉ።
ከዚህ ላይ አዲሱ ሃሳብ ለእነዚህ ንጹህ መንፈሶች የተለዬ ጥንቃቄ እና አያያዝ ለማድረግ በህሊናው ቃል ማሰር አለበት። ድምፃቸውን ሲያሰሙ የሚያደምጥበት ድርብ ጆሮ፤ ሰፊ ልቦና ሊኖረው ይገባል።
ስለምን? ዝምታን ሰንቆ የተቀመጠ አዕምሮ የአቅሙን ልክ፤ የባህሬውን ሁኔታ፤ የሚወስደውን የእርምጃ ዓይነት፤ የማስታዋሉን ልኬታ ኮቴ ማወቅ አይቻልም። የተከደነ ሲሳይ ነው። ናድ ብለው ከሄዱ አዳጋው ሰፊ ነው የሚሆነው። ፍቅር ሲያልቅ ትዕግስት ይሰደዳል እኔ የምለውም ለዚህ ነው። …
• በጥበብ መከራን ስለመሻገር።
በዚህ ሂደት የቀደመው የዛገው ሃሳብ ከራሱም እያመለጡ በሚሄዱት፤ እንደገናም ባሊህ ብሏቸው የማያውቃቸው፤ ባለቤት ያልነበራቸው ህሊናዎች አብዛኛውን ቁጥር የያዙቱ በመሆናቸው ወደ አዲሱ አስተሳስብ ሲጠቃለሉ ከባህር የወጣ አሳ ይሆናል። ግማቱ ከአናቱ ይሆናል። የማረተው ወይንም የዛገው ሃሳብ ማህል ሜዳ ላይ አውላላ ሜዳ ላይ ተንገዋሎ ይቀራል።
በዚህ ወቅት የዛገው መንፈስ ስለሚወራጭ፤ ገርጭራጫም፤ ብስጩም ስለሚሆን የሚጠፉ ነፍሶች ስለሚኖሩ ሽግግሩን በቀላል መስዋዕትነት ለማድረግ „አደብ“ „ጭምትነት“ እንደ ፍልስፍና ሊወሰድ ይገባዋል። እያንዳንዱ መሬት ላይ ያለ ግለሰብ ሆነ ድርጅት ለራሱ ራሱ ዘበኛ / ተቆጣጣሪ/ ጠበቂ መሆን ይኖርበታል።
• ማስተዋልን የህሊና መሪ ማድረግ ይገባል።
• ብልህነትን የሰብዕና አዕምሮ ማድረግ ያስፈልጋል።
• በተለይ የእኔ ብለው ሃሳብ ለሚሰነዝሩ ቅኖች ሰፊ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ንጹህ ልባቸውን ማሰረከብ ግድ ይላቸዋል። „እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም“
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ እልህን/ ቁጣን ዋጥ አድርጎ መያዝ ያስፈልጋል። ህግ ተላላፊ መሆንም አይገባም። ባሩድን የተማመነ አውሬ በተፈለገው ጊዜ፤ የፈለገውን የማድረግ ኃይል አለው። በተለይ ሐገር ቤት ያሉት የሚናፍቁኝ ወገኖቼ ጥንቃቄያቸው ብልህ መሆን ይኖርበታል።
#ፎቶ ምሥርዬ ብርሃኔ ውዴ ትርታዬ ፍሪቡርግ ከደጓ ሲዊዝሻ ቅድስቷ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።