ዬአስተሳሰብ ደራጎንነት እና ጢስ ጢንብሳዊነቱ።

 

ዬአስተሳሰብ ደራጎንነት እና ጢስ ጢንብሳዊነቱ።
"ዬማዳንህን ደስታ ስጠኝ
በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።"
(መዝሙር ፶ ቁጥር ፲፪)
 

 
እነ ማበህረ ደራጎን በሄሮድስ መለስ ዜናዊ አንቀልባ በታቆረ ጥብቆ ህሊና ሊመጥነው በማይችል ቅዠት ውስጥ ሆነው እናያለን። ቅዠታቸውን ለማስቀጠል ያላቸው የአዕምሮ ብቃት አቅሙ አልተመጣጠነም። ያልገባቸው ጉዳይ ይሄ ነው። ስለዚህ ባነሰ ግምት ስድስት ዓይነት ጦርነቶች ተከፍቶባቸዋል። 
 
• አንደኛው፣ … የሻገተው አስተሳብን ለመሳቀጠል ያለ ከራሳቸውም ጋር ራሳቸው ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ።
• ሁለተኛው፣ … በራሳቸው ማህበርተኛ ወስጥ የተፈጠረ አዲስ ሃሳብ አቅም አለ አስምጧቸዋል።
• ሦስተኛው፣… በሃሳብ ልዕልና በሚያምኑ አቅሞች ሙግቶችን የመቋቋም ግብ ግብ ላይ ናቸው።
• አራተኛው፣ … በራሱ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ውስጥ የተከደነ የጦርነት ቀጠና ውስጥ የተጠለለ የዲፕሎማሲ ተጋድሎ አለ።
• አምስተኛው፣ … ከሁሉም ያልሆነ ግን የመንፈስ አቅሙ ሙሉዑ የሆነ፤ ልኩ ያልታወቀ አቅም ልዩ ኃይል አለ፤ ይሄ „ጸጥተኛ ፤ ጭምታዊ ድምጽ silent majority“ የሚባለው።
• ስድስተኛው፣ … የድሮ ዓለምዓቀፍ ወዳጆቻቸው ሂደቱን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪም በቅርበት እዬተከታተሉት መሆኑ ሌላው ፈተና ነው።
 
ለዚህ ሁሉ ፈተና የማህበረ ሌንጮ ህልማቸውን የሚሸከም የአስተሳብ/ የሃሳብ፤ የሰብዕና፤ የአዕምሮ ደረጃው ነገቲብ ላይ ነው። የዛገ ብርት ዝግት እዬጨመረ በሄደ ቁጥር ቀለሙ ብቻ ሳይሆን አገልግሎት የመስጠት አቅሙም ያኑ ያህል እዬተፈረፈረ ይሄዳል። ቀብር።
በሂደቱ ራሱን መሸከም እያቃተው ለበለጠ ክስመቱ ሆነ ዕድሜ ማጠሩ እራሱን በራሱ ያጣፋል። በዚህ ማህል በተነደለ ቁጥር መወተፊያ የሆነው የለበጣ ግርዶሽ ገመናው የአደባባይ ሲሳይ መሆኑ አይቀሬ ይሆናል። 
 
እራሱ „የሞጋሳው ብልጽግና“ ሥርዓታዊ ጉባኤ የሚጀመርበት ቀን ሆነ የሂደቱ መለጠጥም ከዚህ የመነጨ የውልቅልቅ ምርተት ነው። በውስጡ ቀዝቃ የሆነ የፍርኃት እና የራድ ጦርነት አለ።
 
በዛገ እና በማረተ ሃሳብ ውስጥ አዲስ የሚፈጠር በውስጥ የሚበቅል ነገር አይኖርም። ባትሪው አልቋል ወይንም ተቃጥሏል፤ እድገቱ ቁሟል። ጊዜው አልፏል። ከዜሮ በታች ነው። ይህ ማለት ቀዝቅዟል - ዝቅ ባለው ዕሳቤ፤ ከፍ ሲል ደግሞ ግግር በረዶ ሆኗል። እንዲህ እንዲሆን ያደረገው የታሰረበት ንድፈ ሃሳባዊ የአደረጃት መርህ የቀደመ ዕድገትን እየፈራ ራሱን የካሮት ሥር ስላደረገው ነው።
#ይህ አስቀንቶት የአማራ ፖለቲካ ዝፍቅ እንዳይል በጽኑ አሳስባለሁኝ።
 
ዘመን ጥሎት ያለፈው ጎሳዊ የሶሻሊዝም ቅሪተ አካል ሲፈርስ ከበላይ ነው። በዛ ላይ ዘመን የጣለው የተፋው ገዳ ሲታከልበት ደግሞ ድፍርስ ሞት ነው። ፍልስፍናው አንጡራ ጠላቱ የህሊና የአዕምሮ እድገት ፍቀት ወይንም ፍገት ነው። ህሊና አዕምሮ ሲያድግ የሚበልጥ ሃሳብ ስለሚያፈልቅ ሞቱ ስለመሆኑ ጠንቅቆ ያውቀዋል።
 
• ስለሆነም ከሞቱ በፊት አሟሟቱን የሚያበጅ ሳይሆን አሟሟቱን የሚያፋጥን ከይሲ ተግባራትን ከመፈጸም አይቆጠብም - የዛገው። የአስተሳሰብ ድህነት አለበታ! ስለሆነም የአስተሳስብ ድህነቱን ለመሸፈን ጭካኔው ሆነ አፈፃጸሙ የሚመራው በደመንፈስ አዕምሮ ነው።
ስለምን? መረጋጋት የሚያስችል እርሾ፣ ብጣቂ የሃሳብ አቅም ፍርፋሪ ስሌለለው። ፍርፋሪ አለ ከተባለ፤ ፍቅረ ንዋይ፤ ዝሙት፤ ጠበንጃ፤ የኢ-ሰብዕዊነት እርምጃ። አስከዛሬም ባለቀ ባትሪ እዬተገፋ ነው የተኖረው - ሪሞርኬ።
 
• መጠበቅ። 
 
ዝገት ካለበት ከታቆረው ውስጥ ስለሆነ፤ እራሱን እያጠፋ ስለመሆኑ አይታዬውም። ዝገቱ ሆነ ምርተቱ ከውስጥ ነው። እርምጃው ውስጡን እያደሰ ወደፊት በአሸናፊነት የሚያስገሰገስው ይመስለዋል። እእ።
 
ስለዚህ በህልም ሰረገላ ራሱን ኮፍሶ እያሰመጠው ነው የሚሄደው። በቆየበት ዘመን ሁሉ እዛው ላይ ሲዳክር ስለኖረ የሃሳብ ልቅና የፈለቀበትን አካባቢ ሲይ አያስችለውም። ግርዶሽ አለበት። 
 
ግርዶሹ ራሱን እያታለለ መኖር እንደሚችል ግብረ ምላሽ ይሰጣዋል። የተነፋ ህልም። መቃተት። «ለመጪው ጊዜያት በዓለም ከሚኖሩ ሁለት ኃያላን አንዷ ኢትዮጵያ ትሆናለች» የህሊና ዱድማ ዳንቴል የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን ድውይ ዕሳቤም ከዚህ አንጻር ማዬት ይቻላል።
 
የፕሮፖጋንዳ መሳሪያዎቹ፤ የጸጥታ ማስከበሪያ ስልቶቹ፤ የደህንነት መዋቅሮቹ እነሱን እንዳሻቸው እንዲፏልሉ የሚያስችለው የኤኮኖሚ አቅም የሚፈጥሩለት መዋቅራዊ ሰንሰለቱ ቀን ሲያጡ እንደሚክዱት ወይንም ከአገልግሎት ውጪ እንደሚያደርጉት አያሰተውለውም የዛገው ዕሳቤ። በዘመነ ህወሃት የነበረው ዛሬ ተገልብጦ የሌላ ታንቡር መደላቂ ሆኗል። ነገም ይኽው ይቀጥላል። አያድኑትም!
አንድ አደጋ ያለበት አካባቢ ለማዬትም የሃሳብ አቅም ወይንም ድርጁ አዕምሮ ያስፈልገዋል። ሽሁራር በበላው ቸረቸራ አዲስ ጥንስስ አይጠነሰሰም። 
 
አሁን ግብ ግቡ „ዘመን“ „ታሪክ“ „ሁኔታን“ ያደመጠ አዲስ ሃሳብ ጎልቶ፤ ደርጅቶ፤ ጎልብቶ እንዲወጣ ማሰብ፤ ማሰብ፤ ማሰብ ያስፈልጋል።
 
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ የዛገው ሃሳብ አዲስ ሃሳብ ይዞ የወጣውን መንፈስ ጥሶ ለመውጣት አያስችለውም። ስለምን? መቀበልም እኮ አዕምሮ ሲኖር ነው። የተሟላ ሰብዕና ሲኖር ነው። አንጎል ብቻውን መኖሩ የአስተሳሰብ ድህነትን ሊከላ አይችልም። በፍጹም! አንጎልማ እንሰሳትም እኮ አላቸው አይደል? ለዚህ ነው ዘመኑን ያነነበ የሃሳብ ልቅና በጎን ሌላ ተፎካካሪ ተሰናዳለት በማዕከል ግዞት ተፈረደበት። እኔ የማህበራዊ ንቃተ ህሊና መሪ ነን የሚሉት ኩስምን ጥንዙል አቅም በዚህ ልክ ነው እማዬው። 
 
አዲሱ ሃሳብ አዳጊ- ተራማጅ እና ስልጡን ነው። ያሸትም። የልቅናው ምንጭ ሰዓት ነው። ሰዓት ይለፍ ይሰጠዋል። ፈሪዎች ደግሞ ይጫኑታል፤ ይወሩታል፤ ይጠልፉታል ወይ ያግቱታል። 
 
ነገር ግን አዲሱ ኃሳብ ሁሉጊዜ ያሽታል መቃብር ውስጥም ሆኖ። ይህ የሚሆነው የትውስት ውራጅ ሳይሆን በራሱ ህሊና የበቀለ ስለሆነ የራሱ ስልት እና ታክቲክ እየፈጠረ፤ ወቅቱን እያደመጠ በሄደ ቁጥር የፈለቀው አዲስ ሃሳብ እዬዳበረ፤ እያደገ፤ እዬጠነከረ የመሄድ ተስፋው የፋፋ ይሆናል። ይህ የፋፋ አዲስ ዕሳቤ ህሊናዊ ሂደት በራሱ የሚሰጠው፤ የሚፈጥረው ሌላ የሙቀት ስበት Gravity ስበቃም አለው።
ለዚህ አዲስ ሃሳብ ከማረተው አስተሳሰብ አፈንግጠው የሚወጡ አዳዲስ ቡቃያዎች / ችግኞች በራሳቸው ጊዜ ይኖራሉ። እነዚህ ድርብ ግፊት እና ግጭት ሲፈጥሩ የማረተው ሃሳብ ቀስ እያለ አቅሙ እዬተሸበሸበ፤ ግርማው እዬሟሟ፤ ተስፋው እዬሸሸው ይሄዳል።
#ፎቶ አስኔ ቤቱም ዬአስኔው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።