ድካምን እርቃን ላለማስቀረት #ዬቋንጃ ጉዞ ይቁም።
ድካምን እርቃን ላለማስቀረት #ዬቋንጃ ጉዞ ይቁም።
ትዕዛዝ አይደለም ዕይታ ቅናዊ በተለይ ለአማራ ሳተና ወጣቶች።
• ዬውቂ ደብልቂ ቅልቅል አደብ ይግዛ።
• ዬግርግር ሩጫ ተግ ይበል።
• ዬጥድፊያ ግልቢያም ይጨምት።
#መሪነት ሩቅ ማዬት እንጂ ቅርብ አዳሪነት ማለት አይደለም።
• አንደበቶች ይገሩ። ዬ፶ (50) ዓመቱን ዝልቦ መከራ ዬተሸከመው ዬአማራ ህዝብ መሪው መከራው፤
• ማኒፌስቶው ውዚደሙ ይሆን።
• ያገኜ ዬሚነዳው አይሆን።
#ዬመሪነት ጥበብ ተከታታይነትን ይጠይቃል።
ይህ ማለት ሙሉ ዬወጣት፥ ሙሉ ዬጎልማሳ፤ ሙሉ ዬባለግራጫማ ሰብዕና ጠቅልሎ አመራሩ ሊይዝ አይገባም። ተወራራሽነት ያስፈልጋል። ወጣቶች ዬወስፋት ማሳረፊያ እራፊ ተመክሮ ሳይሆን ጎታ መር ተመክሮን ከግራጫማው ሰብዕና ዝቅ ብሎ ለምኖ መማር ይኖርባቸዋል።።ጎልማሳውም እንዲሁ። ሙጥጥ ያለ ዬመሪነት ሂደት ድርቅ ዬመታው ይሆናል። ዘመን እና ዘመንንም ከመቃብር እንዳይቋቋሙ ያማምላል። ይህ ደግሞ ለትውልድ ታሪካዊ ዬልቅና ጉዞ ግድፈት ነው። ዬአሁኑ ኦነግ መራሽ አሳር ይህ ነው። ሲነሪቲ አንጡራ ጠላቱ ነው። እዬተከታተለ እዬመነጠረው ነው። ትናንትን እንደ ደመኛ የሚይም ጉድጓድ ነው።
ዬአማራ ወጣቶች ከዚህ ከተላጠ፤ ከተጋጋጠ፤ ከተሞነጫጨረ፣ ከተፋፋቀ ፍግ ሂደት ጋር እንዳይወዳጁ አበክሬ ላስገነዝባቸው እወዳለሁኝ። ለአማራ ዬተስፋ ጉዞ ታዳጊወች፣ ወጣቶች፤ ጎልማሶች #ዬላስታ አለታቸው ዬቀደምት ትውፊት፤ ታሪክ፤ ትሩፋት፤ ገድል፤ ዬጉዞ ተመክሮ ጥልቁ ዊዝደማቸው ሊሆን ይገባል። አትራፊነት ፈንታዚን ማምለክ ሳይሆን በራስነት ውስጥነት መመሰጥ፣ መወስን በህይወቱ ውስጥ መኖር ነው።
#ፎቶው ባርች ከአሜሪካ መጥታ ሳለ ያነሳችው ነው። ጣቴን ትወደዋለች። በተለዬ ሁኔታ።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ