ዕውነት መሆን የተሳነው ኦሮሙማ ቀጪ የመሆን አቅም የት ሊያመጣው ይሆን? ያምጥ።
ጋዜጠኛ ያዬሰው ሽመልስ ትናንት መታሰሩ ተደምጧል። ጥፋቱ የተሳሳተ መረጃ ሰጠ ይመስለኛል። ከእሱ በፊት ኦነጋውያን እከሌ ተከሌ ሳይባል የተሳሳተ መረጃ አይደለም የንፁኃን ደም ያፋሰሰ ተግባር ፈፅማዋል። እከሌ ተከሌ ሳይባል።
ውሸቱን ከሆነ የመንግስት ፖሊሲ ሆኖ ባጅቷል። ማሸበሩም የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የአደባቫይ ባዕል በመጣ ቁጥር አሸባሪዎች መጡ፣ ያዝናቸው መግለጫው ጫናው ተባጅቶበታል።
ገዳ ንጉሱ ጥላሁን ትንፋሻቸው ውሸት ነው። አቶ ለማ መገርሳ ቢሆኑ ከመሼ ኦሮሞ ፈርስትነታቸው እና ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን ምን ያህል 100 ሚሊዮን ህዝብ እንደዋሹ፣ ስንት አቅም እንዲባክን እንዳደረጉ ይታወቃል። አገራዊ ክህደትም ነው። ሥልጣን ባፍንጫው ይደፋ ያሉት ሰው በዴሞግራፊያቸው እንሟሟታለን እንጂ ቤተ መንግሥታችን አንለቅም ብለውናል።
ደምስስ፣ ንቀል፣ አስወግድ፣ ውረር ያዝም በኦነግ ሊሂቃን የባጀብን ዶፍ ነው። ለአማራ ክልል ሊሂቃን እርሸና የጦማሪ ስዩም ተሾመ እና የአጋፋሪዎቹ የንደት አካሂድ የትናንት ትዝታ ነው።
መዝለፍ፣ ማቃለል ዱላ ቀረሽ ማዋረድም እቴጌ ቤቲ እና ድርጅቷ ባጅተውብናል። ሌላ የተቃጠለው፣ የነደደው ተቋማት፣ ያለፈው ህይወት ሁሉ አንድም ተጠያቂ አላዬንም።
ታዲያ እነሱ በቀደዱት ሌላው ቢያስቀጥለው ስለምን ወንጀል ሊሆን ይችላል? ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ያነደዱ ገድለው የፎከሩ ነፍሶች ባሉት አገር?
አቶ ያዬሰው የሚያደርጋቸውን፣ እሱም ሲደረግ ቃለ ምልልሶችን አዳምጣቸዋለሁኝ። አፍቅሮተ ህወሃት አለበት። ጠሚር አብይ አህመድ እኮ ኢትዮጵያ ትልቅ ኃላፊነት ሰጥታ ያን ክደው ለግንቦት ሰባትም፣ ለኦነግም መረጃ ሲሰጡ እንደ ነበር ገልፀዋል። አገር ክህደት የአገር መሪ አደረጋቸው፣ ቀጭም ሆኑ። ሚዛን ለራስ ነው።
ግድፈቶች ሆኑ መተላለፎች እኩል ሲዳኙ ነው መልካም ነገር። አፍቅሮተ ህወኃት የሚያስቀጣ ከሆነ አፍቅሮተ ኦነገ ከአቶ ለማ መገርሳ ጀምሮ ሊያስቀጣ ይገባል። መዝለፍ፣ አፍ እላፊ ከሆነ የኦነግ ሚዲያዎች አንድአፍታን ጨምሮ ለፍትህ ይቅረቡ። አህያውን ፈርቶ መደላድሉን አይሁን ነው ጉዳዩ።
መቀሌን ወለጋን ማዘዝ ሲያቅት ከሌላው ላይ መጎመር አይገባም። ምን ጠሚሩ በአሽሙር በዬስብሰባው ሲሳደቡ፣ ሲያቃልሉ፣ ሲያጣጥሉ፣ ሲያራክሱ ነው የሚውሉት ለዛውም ሰንበትን ታከው። ከሹመት ንግግራቸው ውጪ ሙሉ የታረመ ንግግር እኔ አላዳምጥም። ለዚህም ነው ሙግቱን ያቆምኩት። የሚድኑ ስላልሆነ።
እንደ መሪ ሪፈር ማድረግ ሁሉ አልተቻለም ንግግራቸውን። ይህ እኔ በጣም እማዝንበት ጉዳይ ነው። ትውልድን ለመገንባት አብነታዊ ንግግር ወሳኝ ነበር። ለዚህ ነው እኔ ሁልጊዜ ዕውነት ይሁኑ የምለው።
የሆነ ሆኖ አቶ ያዬሎሰው ቀደም ሲል በደህንነት ይፈለግ እንደነበር፣ ወደ ትግራይ ለመሄድ በአውሮፕላን ለመጓጓዝ እንደተከለከለ አንድ ቃለ ምልልሱ ላይ አዳምጫለሁኝ። እርግጥ ነው ስላቅለሸለሸኝ አልጨረስኩትም። የሙት መንፈስ አምላኪ ስለሆነ ለመጨረስ አቅም አነሰኝ።
ይህም ቢሆን የሚያምንበትን ማምለክ መብት ነው። የኦሮሙማ መንግሥት በቀሉን ለመበቀል የሄደበት መንገድ ግን አልተመቸኝም። ነገር ግን ህወኃትን መደገፍ መብት ሲሆን የጋዜጠኝነት ኤቲክስን መከተልም መርኽ ነው። መብት እንዳለ ሁሉ ግዴታንም ማወቅ ይገባል።
አቶ ሌንጮ ባቲ ለአልጀዝራ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም ሲሉ ትልቅ ቅርድድ ውሸት ነበር። በኖቤሉ ጉባኤ ጠሚር አብይ አህመድ ይህን ብለዋል፣ የሚገርመው ሸላሚ ኮሜቴው ሙሉ መረጃ ነበረው።
ይህም ብቻ አይደለም ባሌ ላይ "ብልፅግና የማን ነው ብለው ይጠይቁናል እኛም የኦሮሞ ነው እንላቸዋለን" ያሉትን ለሌሎች ደግሞ "ወደ እናንተው ብልፅግና እንኳን ደህና መጣችሁ፣ ከዛም አልፎ የብልፅግና አባል የሆነ ነጋዴ ጠቅላይ ሚኒስተር ለማስደረግ መናፈቃቸውንም ነግረውናል። እንደ ተልባ ሥፍር ወለል ሲል የሚውል መሪ ያለው ትውልድ ያንኑ ቢከተል ምን ይገርማል፣ እንደምንስ ለካቴና ይሸለማል። የዘሩትን ነውና የሚያጭዱት።
ውሎ የሚያድር ቃል የለም። የጎንደር የመጀመሪያው ስብሰባ ጊዜ አንድ በሙሉ ዕድሜ ያሉ ሰው" ከደቀቀችው ጎንደር ወደ ተሻሉት ወደ ባህርዳር አዋሳ መሄድ ነው ሲሉ፣ እናንተ ወደዛ ስትሄዱ እኛ ጎንደር የጎደላትን አሟልተን ወደ ጎንደር እንመጣለን " ያሉትን ተስፋ አቃጥለው ዛሬ ጎንደር በጦር ያስደበድቧታል።
ስለሆነም እሳቸው የመርኽም፣ የዕውነትም መሪም አስተዳዳሪም ሊሆኑ አይችሉም። ለትውሉዱም የዕውነት የመርኽ ሞዴል ሊሆኑ አይችሉም። ያታክታሉ። አብይዝምን ያመነ ጉም የዘገነ ነው። ቃል እና ተግባር አራባ እና ቆቦ ናቸው። በአማርኛ ቋንቋ ኢትዮጵያዊ፣ በኦሮምኛ ኦነጋዊ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ