"የሐኪሞቹ መሠረታዊ የሆነው የመብት ጥያቄ ምላሽ ይሻል!" (ነጭ ቁጣ - Witte Woede) የአቶ ያሬድ ኃይለማርያም ዕይታ
"የሐኪሞቹ መሠረታዊ የሆነው የመብት ጥያቄ ምላሽ ይሻል!"
ትናንት ከሃሳብ ገበታ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ዘግቤ ነበር። ድርጅታቸውም መግለጫ እንዳወጣ ሲገልጡ ሰምቻለሁኝ። አንድ ሃኪም ደም የሚሰጥ ላጣ በሽተኛ ደም መስጠቱን፤ ሌላ ሃኪም ከአባቱ የመጨረሻ መራራ ስንብት ይልቅ የበሽተኛው ቀዶ ጥገና በልጦበት በዛ ላይ እንዳተኮረ በዕውነት የተየሠረተ መረጃ ሲሰጡ ሰምቻለሁኝ። ዛሬ ከአቶ መላኩ በላይ ፔጅ ያገኜሁትን እንሆ። የጨመቱ፤ በንግግራቸውም ጥንቁቅ፤ ቋሚ የሆነ የሰባዊ መብት ትጋት ያላቸው በመሆኑ የማከብራቸው ናቸው።
የአቶ ያሬድ ኃይለማርያም ዕይታ …………
"በሕክምና ሙያ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች በድፍን ጦቢያ ላይ ያጠላውን የፍርሃት ድባብ ገፈው 'ኽረ እየተራብን ነው፣ ብዙ አመታትን ተምረን አገር እያገለገልን እኛ ግን ተረስተናል፣ ደሞዛችን የኑሮን ውድነት እንድንቋቋም አቅም የሚፈጥር አይደለም፣ በቀን አንድ ጊዜ መብላት አቅቶናል' በሚል ለአመታት ውስጥ ለውስጥ ሲያጉረመርሙበት የቆየውን ብሶት ዛሬ አደባባይ ይዘው መውጣታቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። መብትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠየቅ ስልጡንነት ነው።
መንግስት ትኩረት ከነፈጋቸው ዘርፎች መካከልና የመጨረሻው የትኩረት ተርታ ላይ የሚቀመጡት ትምህንትና ጤና ናቸው። ይሄን ለማወቅ ወደ መንግስት ት/ቤቶችና ሆስፒታሎች ጎራ ማለት በቂ ነው። አኪሞች በሽተኛን ጠረንቤዛቸው ላይ አጋድመው ቤተሰቦችን መርፌና ጓንት ገዝታችሁ አምጡ የሚሉበት አገር ከኢትዮጵያ ሌላ መኖሩን እጠራጠራለሁ። ለማንኛውም የሐኪሞቹ የመብት ጥያቄ አግባብነት ያለው ከመሆኑም በላይ ታጋሽነታቸውን የሚያሳይም ነው።
በቤልጅየም አንድ የሚታወቅና አሁን ወደ ትልቅ ተቋምነት የተቀየረ 'ነጭ ቁጣ" ወይም 'ነጭ እንቢተኝነት' (Witte Woede) በመባል የሚታወቅ የሐኪሞች የመብት ጥያቄ የሚታወስበትና በንቅናቄው ስም የሚጠራ ተቋምም አለ። ይህ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1988 የተካሄደው "የሐኪሞች ቁጣ - Witte Woede) ተቃውሞ ዋነኛ ጥያቄው ዛሬ የኢትዮጵያ ሐኪሞች ከሚያነሱት የመብት ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ ነበር። ከቀናት ተቃውሞ በኋላ ጥያቄያቸው በጎ ምላሽ በማግኘቱ Witte Woede ወደ ድርጅትነት ተቀይሮ የሐኪሞች መብት ተከራካሪ ሆኖ እስከ ዛሬ ቀጥሏል።"
እኔ መሠረታዊ የመብት ጥያቄ ካነሱት ሐኪሞች ጎን ነኝ! እናንተስ?
I stand in solidarity with Ethiopian health care peaceful advocacy. You can't save lives on empty stomach!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ