ከዬት ልጀምረው? #ዕውነት #ጋራጅ #አያስፈልገውም።

 

ከዬት ልጀምረው? #ዕውነት #ጋራጅ #አያስፈልገውም
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
ክፍል አንዱን ያዳመጡ "ልብ ወለድ ያሉት" አሉ። ልበወለድ ነው ብንል ጸሐፊው #የፋክት ልበወለድ ጸሐፊነቱን መካድ የሚገባ አይመስለኝም። እን በወርኃ ታህሳስ በ2019 የፃፍኩት እኮ አለሁኝ - በህይወት። ሂደቱን ብቻ ተመልክቼ። እንኳንስ ድርጊቱ በቁሙ በሚነበብበት፤ በሚተረጎምበት ወቅት ዛሬ ላይ። ሂደቱ ለሁሉም አይጠቅምም። #ክህደትም ነው። መታመንን የሰለቀጠ። 
 
የሆነ ሆኖ ከሦስተኛ ወገን የሚመጡ ጉዳዮች ቅመማ ቅመም ሊጨማመርበት ቢችልም ጭብጡ ግን ፋክት ተኮር ነው። ጠንክረው የወጡ ተደጋጋሚ #ዝንባሌወች እንዳሉ ተመልክቻለሁኝ። አትኩረተ ኤርትራ፥ ነገረ ጎጃም እና ጎንደር። ጥቅሙ ግን አቅም መግቦት ላይ የባጁትም እራሳቸውን ይመዝኑበት። አባ ጎልጉል አቶ ሽመልስ አብዲሳ እኮ #እንቅጩን ተናግረዋል። "ኮንቢንስና ኮንፊይዝድ" በማለት። #ለ7 ወራት የማህበረ ኦነግ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሽጎ ተቀምጦ በኋላ ወጣ። ከወጣ በኋላ ጥድፊያ ነበር የኮፒ ራይት። በዛ ውስጥ እምሽክ ስላለው የኢትዮጵያ ተስፋ ይሁን የአማራ ሰቆቃ ባለቤት አልባ ነበር።
 
ማህበረ ቅንነት ይመስላችኋልን አዲስ አበባ በፌድራሉ ሥር እንዳለች? #እእ። እኔ ለአምስት ዓመታት ጽፌበታለሁኝ። ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ናት። ለኦነግ የተገባው ቃል የኤርትራው ስምምነትም ይሄው ነው። ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ወደ ኤርትራ ሲጓዙ ዜና ነበር። ሲመለሱ #ፀጥታ። 
 
በወቅቱ ብሎጌ ላይ ጽፌበት ነበር። 5 የአዲስ አበባ ልጆች ተረሽነው፦ 1300 ወደ ጦላይ የተላኩትም ለኦነግ #ርችት ነበር። እስከ አሁን እስር ላይ የሚማቅቁም አሉ። ፎቶውን እለጥፋለሁኝ። የቡራዩ፤ የለገጣፎ ሰቆቃም ከዚህው ጋር የተያያዘ ነው። የሸገር ምስረታም ይሄው ነው። ከጉለሌ ወደ ባህርዳር የተሸኙ እኛወችን አታስታውሱም። ያለመዟቸው ታማኝ ውሾች ሁሉ ሲሸኟቸው አላያችሁምን??
 
እና ለእኔ ያዬሁትን፤ የታዘብኩትን፤ የማውቀውን ፋክት አብራራልኝ እንጂ የሆነውን፤ ያዬሁትን፤ አስቀድሜ ሰግቼ የፃፍኩበትን ያውም ጠሚር አብይ አህመድ አሊ በገፍ ደጋፊ እያላቸው የሞገትኩበትን ፋክት በትረካ መልክ ቢቀርም፤ የሚስጢር ሰነድ ቢባልም ፋክትነቱ አደባባይ የዋለ የወርቅ እንክብል ነው። አንባቢም፤ ተርጓሚም አመሳጣሪም አይሻም። #ዕውነት #ጋራጅ #አያስፈልገውም
 
አንድ አገር መርኋ አሉታዊ ዴሞግራፊ ከሆነ ይህ አይቀሬ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የመወያያ አጀንዳ ይህን ማድረግ አልፈቀዱም፤ ወይንም አቃለውታል። የሁለተኛው የአለም ጦርነት መነሻም፤ ድቀትም እኮ አሉታዊ #ዴሞግራፊ ነው። የኢትዮጵያ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ #አሉታዊ #ዴሞግራፊ ነው። አሁን በዘመናዊ መልክ ብቅ ብቅ እያለ ነው በዓለም ዙሪያ። በኢትዮጵያ 6 ዓመታትን አስቆጠረ።
ይህ ሥርዓት ዕውቅና ያገኝ ዘንድ #ምርጫው ላይ ሁሉም ትጋት ላይ ነበር። #ከርዕዮት #ከቴዲ ሚዲያ በስተቀር። #አሉታዊ #ዴሞግራፊ እውቅና ባገኜ ማግሥት ሁሉም ተገልብጦ ተቃዋሚ ሆነ። በአብይዝም ድጋፍ ቀጣዮችም ጥቂት አልነበሩም። እኔ እማያምረኝ ነገር ከኖረ ዝምታ ርስቴ ነው። ዝም ነበር ያልኩት። ብዙ ቀዳዳ ስላለ በዛ እተጋለሁኝ።
 
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።
- ዲሴምበር 16, 2019
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
 
ገና በ2019 የፃፍኩት ግን እንሆ …… ከዛሬው የአንከር ሚዲያ መረጃ ጋር አነጣጥሩት። ለእኔ "ልበወልለድ" ከተባለም ከዕውነተኛ ፋክት የተነሳ ነው ብዬ ነው እማምነው። ብዙ በጣም ብዙ ጥልቅ ያልተገለጡ #ተሰውረው የተከወኑ የእኛነት ምዝበራወች፤ ድምሰሳወችም ይኖራሉ። ይህ ቅምሻ ነው የሚመስለኝ። 
 
 
ምን እንድርግን? በራስ አቅም ፈጠራ #በአቅም #ጥራት ለማፋፋት ከዜሮ መጀመር ያስፈልጋል። በተለይ ለዲያስፖራው።
«Anchor Media የጅማው ስብሰባ - የሚኒሊክ ቤተመንግስት የሚባል የለም፥ የሚኒሊክ ሀውልትም ይነሳል፥ ገና እናራግፋለን»
«Anchor የጅማው ስብሰባ ክፍል 2 - ነፍጠኛው ዳግም እንዳያንሰራራ አድርገን ሰብረነዋል፥ ሁሉንም ነገር በእኛ ቁጥጥር ስር የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው»
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/02/2025
 
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
የሚያድነው መንገድ #ታማኝነት ብቻ ነው። #ክህደት #ገደል ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?