ትንሽ ቆይታ ከጃዋሪዝም የአብይዝምን አቅላይነት ጎዳና ጋር ………
ትንሽ ቆይታ ከጃዋሪዝም የአብይዝምን አቅላይነት ጎዳና ጋር ………
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

#ጠብታ።
ወርኃ የካቲት የታቦቴ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን በስጋ የተለዬን ስለሆነ እያዘከርነው ቢሆን። ለ17 ዓመታት በዘለቀው በእምዬ ሲዊዘርላንድ በራዲዮ #ሎራ 97.5 መካከለኛ ሞገድ በወር ሁለት ጊዜ በዕለተ ሃሙስ በቀን ቅዱስ ከ15.00 -16.00 ጸጋዬ ራዲዮ በድንቁ አማርኛ ቋንቋ በሚተላለፈው መሰናዶ በአግባቡ በዬአመቱ ተከብሮ ይዘከራል። የራዲዮ ፕሮግራሙ የተመሰረተበት ዓላማም ግብም ይኽው ነውና። ለታላቅ ባለውለታ የቅኔ አባት መታሰቢያው ክብሩን፤ ልዕልናውን፤ የአማርኛ ቋንቋን የሥልጣኔ ትውፊቱን ማስቀጠል ነውና የትውልዱ ድርሻ።
አቶ ጃዋር መሃመድ ስለ አዲስ አበባ ሰሞኑን ያለው ቁምነገር አለ። ከዛ ያጎረፈ ሃሳቡ በፍፁም የተለዬ አዲስ አበባን የገነባትን #ጉራጌን አትዝለሉ ሲል ለኦሮሞ እና ለአማራ የአዲስ አበባ አቀንቃኞች መልዕክቱን ሳደምጥ #ቁጥር አንድ ውሽክ አልኩ። በነገራችን ላይ የጨመቱ ጉራጌ፤ ጋሞ፤ ወላይታ፤ አማሮ፤ አፋር ወዘተ ማህበረሰቦች ኢትዮጵያ ስለሰጣት ፈጣሪን አላህን ልታመሰግን ይገባታል።
ቁጥር ሁለቱ ውሽክታ ደግሞ በአገረ ጀርመን ላይ "እኛ መንግሥት መገልበጥ ሰልችቶናል" ሲል ውሽክ ብዬ ነበር። ኧረ በሞቴ አይሰልችህና ሞክረው በማለት መልሱንም ጥፌያለሁ። ሊንኩም ተቀምጧል።
ሰሞኑን ደግሞ በኦነግ ዓርማ በተንቆጠቆጠው አዳራሽ በአሜሪካ ኦሪንገን ላይ ተሰብሳቢወች በጀርባ በሚታዩበት የጃዋሪዝም ጉባኤ ላይ በኦሮምኛ ተናግሮ የተተረጎመውን " ማለዳ " በሚባል ዩቱብ ቻናል፤ "መንግሥት መገልበጥ ከሰለቸን ተሃድሶ ይባል፤ ተጠግኖ ተጠግኖ ይባል ሪቦልሺን ይባል፦ "የአብይን ሥርአት ለመጣል ከህወሃቲዝም አይከብድብንም" ሲል ቤቴ እስኪነቃነቅ ሳቅሁኝ። ይህቺ ሳቄ ለእኔም ትናፍቀኛለች፤ ለቤተሰቦቼ ብቻ ሳይሆን። ቤት እኮ ፀጥ እረጭ ያልኩ ነኝ። በጣም ዝምተኛ ነኝ።
እምዬ ሲዊዝን ኮሽ አይሏን ቢንቲዬን እመወዳቸውም ፀጥ ረጭ ስለሚሉ ነው። ፈንቅሉ ሳቅ ሲመጣ ግን ይደበላለቃል። እና አስነካሁት ነውእምላችሁ። አንድኛ ወር ሳይሞላ ሽግግሩ ነው "ከመገልበጥ ሰልችቶናል፤ ለመገልበጥ ቀላሉ" ሲል የተደመጠው። ሁለተኛ ህወሃትን "ገለበጥኩት$ ዲስኩሩ ግርም ይለኛል። ፋክት አንደበት ቢኖረው እላለሁኝ። በአንድ ደራሽ አክቲቢስት አቅም ከ40 ዓመት በላይ የዘለቀ ድርጅት ሲፈነገል ታዬኝ እኮ። ዕድሜ ጠገብ የሆኑ አገር የመሩ የግሎባል የተግባር ትንታጎች ተግባሪወች - ተቀምጠው።
ይህ ደዌ ነዌ ነው። ጠሚር አብይ አህመድም ይህ በሽታ አለባቸው። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችም ሆኑ የሚዲያ ሰወችም እንዲሁ። "ቢገፋት ይወድቃል" ሲሉ የባጁት "መንግስትን መጣል በአጭር ጊዜ እንዴት ይቻላል?" ወደሚል ስለተሸጋገሩ፤ አቅለሸለሸኝ እና ሳልጨርሰው ቀረሁኝ። "መጥኖ መደቆስ" ይላሉ እናቶቻችን። ይህ ለምን ሆነ ሲባል የዘመን ለውጥ ያደረገው ግዴታ ነው። ያልተጠበቀ ግን የሆነው እጅግ አስደንጋጭ ለብስጭትም የዳረገ ግሎባል ክስተት ስለተፈጠረ።
ሙሉ አቅም ቢኖር እንኳን ጊዜ ተለዋዋጭ ስለሆነ በልኩ አንደበትን ማናገር ይገባል። ልምድ - ተመክሮ ለዚህ ካላገዘ ለመቼ ሊሆን ይሆን? እን እኔ አቅልሎ ከመጀመር፤ አክብዶ መጀመር በስንት ጣሙ። "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል ይላሉ" ባለ ቅኔወቹ ጎንደሮች። ቢያንስ ጊዜውን ለፈጣሪ ለእግዚአብሄር መስጠት እንደምን #ያቃትት????
#ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ተቀለው የሚታዩ ሰው አይደሉም።
ለጅማሮ ውድቀቱ የሚጀምረው ከዚህ ላይ ነው። ህወሃትም ቀላል አይደለም። አይደለም ትናንት ዛሬም። ጠሚር አብይ አህመድም ቀላል ሰው አይደሉም። ኖቬልን እንደምን እንደተሸለሙ ማገናዘቡ በቂ ነው። ሙሉ ዕድሜያቸውን የተሰናዱ፤ በተሰናዱት ልክም ፍላጎታቸውን እያሳኩ ያሉ ሰው ናቸው። መረረንም - ጣመንም። ስሜነኞች አላችሁን??????
ያ ሁሉ በግል እና በጋራ በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፎ ህወሃትን ሲታገል የነበረውን እንደምን ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ፤ ወይንም ማጠቢያ ማሽን እንደገባ ጥርጥር ቀሚስ እንደሸበሸቡት ሂደቱን አጥንታችሁታልን? ለመሆኑ የአንተ የራስህ ሚሊዮን አጃቢ ስትታሰር ምኑ ዋጠው? ቢያንስ ውጪ አገር???? የትኛው የይፈታልን ሞገድ ነበር?? {}.
በግልም ሆነ በድርጅትም ሲታገል የነበረ የፖለቲካ ድርጅትም ይሁን ሚዲያ በወረፋ ተሰልፎ አገር ገባ። በደማቅ አቀባበል ተቀበሉት። የውጩ እርዳታ ይጎርፍ ነበር። ከዛ ሆቴል አስቀምጠው ቀለቡት። አንዳንዱ ግዞት ላይ ሆኖ ያለም፤ ያለፈም አለ። ትንፍሽ እንዳይል ተደርጎ ተለጉሞ የተቀመጠ። ሌላው ወደ የግል ህይወቱ ተመለሰ፤ ያልተመቼው የተፈቀደለት ብቻ ዳግመኛ #ስደቱን መረጠ። ለመሆኑ ኮነሬል ጎሹ ወልዴ? አቶ ኦባንግ ሜቶ የት ናቸው ያሉት? ለምን ተሰወሩ? ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ፤ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወይሳ አሟሟታቸው በምን ሁኔታ ነበር??? ብቻ ተፈቅዶለት ወደ ስደቱ የተመለሰው ንብረቱ ተራግፎ እና የወጠነው ከስሮ። ማዕረጉ እና ክብሩ ቀናንሶ ነው ይህ #በመተት ነውን??
#ቲም ለማ፤ ቲም ገዱ ተነነ? ይህስ በድግምት ነውን?? ጠሚር አብይ አህመድ በፈለጉት ሰዓት የፈለጉትን #ህግ ጥሰው ይፈጽማሉ። #ሃግ ባይ የላቸውም። አቅማቸውን ካረጋገጡ በኋላ ያን የለለ፦ ልል ፓርላማ ይጠሩ እና በጭብጨባ አንፖል ያንፀባርቁታል። ይህ ማጂክ ወይንስ???
ሎሬት ዶር አብይ አህመድ አሊ መጀመሪያ በአገር ውስጡም፤ በውጩም ጉዳይ #ነኮርኮር ያደርጉ እና ፬ ኪሎ ማማቸው ላይ ሆነው ሲስቁ፦ ሌላው ያን አጀንዳ አድርጎ ደግፎ ሲባትል የሱማሌ ላንድ ጉዳይ፤ የተዋህዶ ጉዳይን ማንሳት ይቻላል። ከዛስ የደገፈውንም የተነተነውንም፥ የተቃወመውንም ጉልት ያደርጉ እና በጉዳዩ እንዳልነበሩበት ሆነው በአዲስ አቅም ሁሉንም ማህል ቤት ዘርጋግተው እሳቸው አዲስ ተውኔት ይጀምራሉ። #የእርቅ አንበል ሆነው። ይህስ ታምራት ነውን?
ቀውስ በዬአቅጣጫው ያደራጃሉ፤ ቀውሱን ይመራሉ፤ ዜናውና የቀውሱ ድርጊት እንደ ሞገድ ጋዜጣ ልበወለድ እኩል ሰበር በመሆን አገር ሲናኝ እሳቸው ከአገር ወጥተው ሌላ ሴሪሞኒ ላይ ከቸች ይላሉ? ይህስ ለጠፍ ክስተት ይባል ይሆን?
ሚሊዮኖችን አፈናቅለው፤ ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲሄዱ አስገድደው እሳቸው አንድ የውሃ የኤሌክትሪክ ዳንስ፤ ወይንም የጥቂት አዛውንት ቢላ፦ ወይንም የመኪና ፓርክ ምረቃ 11 ይሁኑ 12 የመስተዳድር ሹማምንታቸውን ይዘው በአጀብ ቀይ #ሪያን ሲቆርጡ ይገኛሉ።
ሺወች ተፈናቅለው፤ መቶወች ተገድለው ዋይታ በበረታበት ዕለት እሳቸው አንደበቶቻቸውን ያስከፋፍቱ እና ስለሚሊዮን ችግኝ ተከላ ታንቡር በባንድ ይደለቃል በሚዲያወቻቸው ላንቃ፤ አይጠዩቁም እሳቸው። ሚዲያ ፈሪ እንደ እሳቸው የለም። ግን በፈቃዳቸው ተኳኩለው ብቅ ይሉና "ችግኙ ይተከል አትከልክሉን፤ ለሞቱት ጥላ ይሆናል።" ይሉና በዛ ሌላው አቅሙን ሲያፈስ እሳቸው አዲስ እዮቤል ቤተ- መንግሥታቸው፤ ቤተ - መፃህፍታቸው፤ #የዙ መስፈሪያቸው ኮንስትራክሽን ላይ ይገኛሉ። በዚህ አያበቁም ከሠራተኞቻቸው ጋርም #በቦላሌ ሱሪ ሜዳ ገብተው ኳሷን ይደልቃሉ። ወይ የሰንበት የጎመን ገብያ ከፍተው ችርቻሮ ወይንም ዘይት አከፋፋይ ወይንም አስኳባ ይዘው ከተማ ጽዳት ……? የዶር አብይ አስኳባ የት ገባ ይሆን??? ድምጡ ስለጠፋ።
ለመዘናጋት እራሱ አቅደው የተነሱ ናቸው። ማዛሉ በዕቅድ ውስጥ ነው - አይደለም ለሥራ። አንድ ጥምቀት በሚዲያወቻቸው በሱማሌኛ፤ በትግረኛ፤ በኦሮምኛ፤ በአረብኛ እና በአማርኛ ቋንቋ መግለጫ ሲሰጥ ነበር። ይህ ለምክንያት ነበር። አሁን የአማርኛ ቋንቋ የፈረንሳይ ቋንቋን ያህል እንኳን ክብር አጥቶ ህገ - መንግሥት ጥሰው በፓርላማ አጸደቁ?? የልባቸውን የሚያደርሱት ጥምልምል ባለው የተግባር አዟሪታቸው ነው።
አይደለም ከማህበረ ኦነግ፦ ከሌላም እንደ እሳቸው ያለ ለተልዕኮው ስኬት ሳይዘናጋ ዕድሉን ካገኛት ከመጋቢት 18 ቀን 2010 ቅጽበት ጀምሮ እንቅልፍ ሳያምረው የባተለ አንድ ሰው ማግኜት አይቻልም። ታስታውሳላችሁ የህወሃት ሁለተኛ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስብሰባ አልተገኙም ነበር። አቶ ጃዋር መሃመድ ሞግቶም ነበር። በዛን ጊዜ አቋማቸውን ቢያሳውቁ ኖሮ ለዚህ ዕድል የመብቃት ገጠመኛቸው አሮ ይቀር ነበር። እና አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ)ከህወሃትም ይልቅ ከባዱ ፈተና #አሳቻው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ናቸው። ሴት የውጭ አገር መሪወችን በስልክ ሲያነጋግሩ፤ ተባዕቶችን ሲያነጋግሩ ቃናው አንድ ነው ብላችሁ እንዳታስቡ። ሌላው ቀርቶ በኃያልነት ከሚታወቁት ከጀርመን እና ከፈረንሳይ መሪ ጋር ያለውን የአቀራረብ ሁነት ተመልከቱት።
ኤርትራ፤ አረብ ኢምሬት፤ ሱማሌ፤ ኢጣሊያን መሪወቻቸው እንዴት አቀባበል አደረጉላቸው? የኢሚሬት ሠረገላም ነበረው። የጀርመን ግን ውጭ ጉዳይ ሚሩ በወቅቱ አቶ ደመቀ መኮንን እንኳን እንዲቀበሏቸው አላደረጉም። ይህን ለምን? እንዴት ብላችሁ ጠይቁ?
ታስታውሳላችሁ ባልታሰበ ቀን #እስራኤል ሹልክ ብለው ገብተው፤ እጅ መንሻም ይዘው እስራኤል እንዴት እንደገቡ? በዛው ሰሞን የአውሮፓ ህብረት ቁንጮ ዶር ኡርዙላን ጋብዘው በራሳቸው ሹፌርነት እንደምን እንደ አቀማጠሉ አያችሁት?
ውጥር ተደርገው ሲያዙ የሚያበርዱበት ዘይቤያቸው #ፈጣን እና የተከደነ ነው። እና አቶ ጃዋር መሃመድ ይህ አንተ አለህን? ሊኖርህ የሚችለው ተናጋሪ አንደበት፤ ኦዲዬንስን መቆጣጠር የሚችል የንግግር ጥበብ ብቻ ነው ወይንም አክቲቢስትነት ይህንንም ያስነኩታል አያ አጅሬ ሲያሻቸው እንደ ካድሬነት፤ ሲላቸው እንደ ማጅስቲ።
የሆነ ሆኖ በአሁኑ ሰዓት ቀውስ ላደራጅ ብትል የአንተ የሆኑት በብዙ የተሰወሩ ፕሮጀክቶች ውስጥ አስገብተዋቸዋል። በሚዲያ፤ በተውኔት፤ በደህንነት፤ በስኮላር ወዘተ …… ብዙ #ተራርቃችኋል።
ጠሚር አብይ ልካቸው ጭምቱ ዶር ለማ መገርሳ ብቻ ነበሩ ከማህበረ ኦነግ። ሊደመጡ የሚችሉ። ሳንጠግባቸው ኦነግ ሆኑብን እንጂ። ብቻ ለዛውም በዚህ ልክ የህዝብን ህሊና አፍዞ እና አደንዝዞ ኦነግ ካቀደው 200 % እጥፍ በላይ ዶር ለማ መገርሳ ስለማሳካታቸው እርግጠኛ አይደለሁም።
ሌላው ለህሊናዊነት የማሳስበው አሁን ባለው ሁኔታ የማህበረ ኦነግ መንፈስ ታምኖ አጋርነት የአቅም ብክነት፤ ተጨማሪ #ፋስ መናፈቅ ይመስለኛል። እኔ እንዲያውም አንተ ባትሆን ማድመጡም፥ መሞገቱም ፍላጎት አይኖረኝም ነበር። የነፃ አውጪ ግንባር የበታችነት የሚጨፍርበት ዝልኝ ፖለቲካ ስለሆነ አቅም ማባከን ተፈላጊ አይደለም።
#የጃዋሪዝም የትግል ማኒፌስቶ፤
የሰጠኽው መመሪያ "ግብር አትክፈሉ ነው።
1) " አብይዝም ግብር ላልከፈለ አገልግሎት ቢያቋርጥ ምን ይኮናል? አሁን ለዛ መከረኛ የተጋሩ ህዝብ እምፈራው ይህን ነው። በጀቱ ቢቆም ምን ሊኮን?
2) ሌላው "ኢንቤስት አታድርጉ ነው።" ሰላም በሌለበት አንተ ባትናገረውም ወፈፌ ሃብ ት አይኖርም ሄዶ እርቃኑን ለመመለስ የሚባዝን። ከዛ የሚቀለው እንደ እኔ ……
"ገንዘብ በባንክ አትላኩ ሊሆን" ይችላል። (+±)አባ መላ አባ መላነት በፕሉስ ሚኑስ ነው፤ ዶር አብይ ከአሰቡበት ለዚህም 24 ሰዓት ጭንቅላታቸው እንደ ሞተር የሚሰራው ዶር አብይ ማሰሪያ ገመድ ያበጁለታል። ቀላል ሰው አይደሉም። ዲጅታሉንም ተክህነውበታል ኦኮ።
#ቁልፍ።
አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ )#የኢንሳ መስራች መሆናቸውንም የረሳኽው ይመስለኛል። በዚህም ይበልጡኃል። ሥርዓት ውስጥ እዬሰሩ በማደግም ይበልጡኃል። ሚሊተር ውስጥም በማገልገል፤ በሶሊዳሪቲ ላይም ውጭ አገር ሄደው በመሳተፍ ይበልጡኃል። 6 ዓመታት አገር መርተዋል። የአለም ኮከብ የሚባሉ አገሮችንም አይተዋል። ልምዱ፤ ተመክሮውን እሰበው። እንደ ፈንግል እንደያዘው ዶሮ በቀላሉ አንድ መንግሥት መፈንገል አይቻልም። የጠሚር አብይ ተፈጥሮም አሳቻ ነው። ለኢትዮጵያ ፖለቲካም፦ ፖለቲከኞችም የገዘፋ ፈተና ናቸው። ለመፍትሄው በሙሉ አቅማቸው ፈቅደው ተሳታፊ ካልሆኑ አልሻባብን፤ ሱዳንን ቀጥል ሊሉ ይችላሉ።
በሌላም የእርስ በእርስ ግጭትም የከፋውን ሊመርጡ ይችላሉ። እኔ እምፈራው ይህንን ነው። ተቆላምጠውም ከተሳካ ጥሩ ነው። በትንሹ ነው የሚበሳጩት። የ100 ቀን ጉዟቸው ባህርዳር ላይ ስለ አኖሌ ሲነሳ ሌላ ሰው ሆነው ነበር። ማለት የእንቅፋት አንከር ለጉዟቸው የነበረ በኽረ ጥያቄ ስለነበር። አሜሪካ ላይም ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ጸጋዬ ላቀረበው ጥያቄ እንደምን አንደነበር አስተውለናል። ጥንቃቄ በእጅጉ የሚያስፈልጋቸው ሰውኛ እና ተፈጥሯዊ ጉዳዮች አሉ። ሚሊዮን ታማሚ፤ ህፃናት፤ አዛውንት፤ አቅመ ደካማ፤ አካላቸው ችግር ያለበት ወገኖች አሉን። ድህነቱም አለ። የለት የሌላቸው። ኃላፊነት የጥቂት ሰው ሳይሆን የሁላችንም ነው። መጠንቀቅ አለብን።
#ሂደትን ማጥናት ለጠንቃቃነት የፊደል ገበታ ነው።
የሃድያ ህዝብ የዶር አብይ አህመድ ጽኑ ደጋፊ ነው ሲባል ሰምቻለሁኝ። ነፍሳቸውን ይማረውና ፕ/ በዬነ ጴጥሮስ አልፈዋል። በአካልም በተደጋጋሚ ተገናኝተን - ተሟግተናል። አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ)ለመሆኑ አሟሟታቸውን አስበኽው ታውቃለህ። ከእሳቸው ህልፈት በኋላ የነበሩ ሴሪሞኒወችንም #ነጠብጣቦችን አያይዘህ እስቲ ወግ ይድረስህ እና ሰከን ብለህ መርምራቸው። ፖለቲከኛ ነህ እና። "ሳይንቲስት፤ ስትራቴጅስት" የሚለውን አልቀበልም። በሳይንቲስትነትህ አዲሱን ግኝትህን፤ በስትራቴጅነት ካፒቴንነት ውሃ ያልነካውን የፖሊሲ ትልምህን እና ስኬትህን ቁጭ አድርግ - እኔ እንድቀበለው።
ጄኒራል ባጫ ደበሌ ምክትል አዛዥ እስከ አሁን እንደሆኑ አስበኽው ታውቃለህ? ቦታው በሳቸው ኃላፊነት ሥር ነው። የኬንያ ደግሞ አንባሳደር ናቸው። ሰሞኑን ከአንድ የፋኖ ክንፍ ጋር ለመወያዬት ከአህጉሩ ድርጅት ኦነግ፤ ከኢጋድ ደግሞ ኦህዴድ ስልቱስ ትልሙስ ለምን ይሆን??? የረቀቀ ትርጓሜ አለው። "የሰበርናቸው" ፈሊጥ ነው።
አሁንም ብቁ አክቲቢስት፤ ጥሩ ተናጋሪ፤ ትጉህ የሚዲያ ሰው፤ ጥሩም ጸሐፊ፤ ጥሞና አክባሪ እንደሆንክ አምናለሁኝ። ሆነህ ስላዬሁህ። በተለይ የጥሞናህ ጊዜ የሳበኝ ወቅት ነበር። ጠሚር አብይ አህመድን የመተካት አቅሙ ግን ገና ነህ። ከሥር ሲስተም ውስጥ ታሽተህ፤ እንደ ገብስ ቆሎ ተሾክሹከህ፤ እንደ ስንዴ ተፈትገህ፤ በህግ ሥር ሆነህ ታዛዥ ሆነህ መምጣት ይኖርበኃል። አደብ፤ ስክነት፤ እርጋታ፤ በውሳኔ መጽናትም፤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን ወዶ መቀበል፦ ፀፀትን፦ ይቅርታ መጠየቅን፤ ከበቀል፤ ከቂም ከቅናት ፀድቶ ቅንነትን ማብራት በቀጣይ የሚጠበቅብህ ይመስለኛል።
አጽዴቄ እማጠቃልለው አብይዝም ከህውሃቲዝም አይቀልም። እንዲያውም እንደ መርግ የከበደ ነው። ቁልፍልፋን አላስተዋልከውም። ከኦነግ፤ ከኢዜማ፤ ከአብን ለሥልጣን የወሰዷቸውን ሰብዕናወች ለምን ስለምን ተመራመርበት ……… የአብይዝም የማዛል አትራፊነት ዘርፈ ብዙ ነው። በቅጽበታዊ ዕሳቤ እና በቅጽበታዊ ንቅናቄ የሚሆን አይደለም። ምራቁን የዋጠ ዊዝደም ይጠይቃል።
ሃይማኖት ላይ የሰሩት ሂንዲዩዝም፤ ቡድሂዝም፤ ፒኮክኢዝም፤ ኢነርጂዚም፤ እስላሚዝም፤ ማርክሲዝም፤ ክርስቲያንዝም፦ ተቀይጠው መልክም ቀለምም አልቦሽ ሆነው እንዲንሳፈፋም እዬሠሩበት ያለ ገመና ነው። ካሰኛቸው ሰይጣኒዝምም ቤተኛ ይሆናል። ጥቁር እና ግራጫ ቀለም፤ ጥቁር አረንጓዴ ወዳጆቻቸው ናቸው። ለምን??? ጠይቅ የሚዲያ ሰው አይደለህ። ሎጎቻቸውን ሁሉ ጠረጴዛህ ላይ አስቀምጠህ መርም የፋና ላምሮትንም እንዳትረሳ።
አሁን ያለው ሥርአት የአማራ እና የኦሮሞ ነው አትበል። ይህ ግዙፍ ስህተት ነው። በመቁንን የሚሰጠው ለአማራ አማራ የሚወከለው ውህድ ማንነት ከኖረው ብቻ ነው። ጨመርኳቸው የሚሏቸውን ኮታ ከአማራ ተወስዶ ነው። የግማዱን ልክ እዬው። በህዋህት ጊዜ ት/ሚር፤ ጤና ሚር ወዘተ የብአዴን ነበር ዛሬ???? ለዛውም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ አለመሆናቸውም ይረጋገጣል። ላይ ላይ መጋለበ ሳይሆን የማህበረሰብን ችግር ለማስወገድ በስክነት ውስጥ እቃውን ማጥናት ይጠበቃል። በህወሃቲዝምም፤ በአብይዝም። በቀጣይም እናንተ የምትሹት ይህ ነው ከአማራ ሊሂቃን አቅም የጸዳች ኢትዮጵያ። ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዊዝደም የራቀው። አዲሱ የአማራ ትውልድ ግን ይህን በይሁንታ የሚያሳልፈው ፈጽሞ አይመስለኝም።
የአቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) የለሽታ ዘመን ሂደት #ስንብት በመባነን አህዱነት ለዛሬ --- ክሱቱነት። #የት ተባጄ?????!!!!
እኔ በመራሁት #አንድም #የትግራይ #ተወላጅ #አልተጎዳም።" (አቶ ጃዋር መሐመድ (ሃጂ) ከጋዜጠኛ ቴወድሮስ ጸጋዬ በርዮት ሚዲያ በነበረው ቆይታ። ) የአማራ ህዝብ ከቀደምቶቹ ጋር ሆኖ ባበጃት አገሩ ያን ያህል ግፍ የተፈፀመው #በወል ውሳኔ ነው ለካ።
"ጠሚር አብይ አህመድ እና አቶ ጃዋር መሃመድ ሁለቱ ብቻ ለምርጫ ቢቀርቡ ምርጫዬ አቶ #ጃዋር #መሃመድ ነው። (ዶር ዮናስ ብሩ በአንድ አፍታ እና አንከር ሚዲያ። ) ኢትዮጵያን እንዴት ብትለካ? እንደምን ብትገመት? እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ተወዳዳሪ አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) #ብቻ ቢሆን #ምርጫዬ አይሆንም። በፍፁም።
- ጃንዋሪ 17, 2025
#የገለበጠም #የተገለበጠም #የለም! #በሞቴ መንግስት መገልበጥ #አይሰልችህና #ሞካክረው። እኛም እንይ ………
#የጃዋሪዝም #ሞገድ #ዳጥ።
- ፌብሩዋሪ 06, 2025
የኔወቹ ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፦ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/02/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ