ጉበትዎ እንደተጎዳ የሚነግሩዎት 10 ምልክቶች
ጉበትዎ እንደተጎዳ የሚነግሩዎት 10 ምልክቶች
ጉበት በአካላችን ትልቁ ኬሚካል አመንጪ አካል ነው። ጥቅሞቹ ብዙ ናቸው። 3 ዋና ጥቅሞች አሉት። ባይል የሚባል ምግብን ለመፍጨት የሚያግዝ አረንጓዴ ኬሚካል ያመነጫል። በሰውነታችን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያጸዳል። የሰውነታችንን ሃይል ፍላጎት ላማሟላት ግሉኮስ ያመነጫል። ከጉበት አስፈላጊ ጥቅሞች አንጻር ጤናውን መከታተል ለሰውነታችን ጤና አስፈልጊ ነው። ጥሩ አመጋገብ፣ አካል ብቃት እንቅስቅሴ እና በቂ እንቅልፍ ማግኘት ለጉበት ጤና አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። አልኮል እና ቡና ማብዛት የጉበታችንን ጤና አደጋ ላይ ይጥሉታል።
ጉበታችን ሲታመም ህመሙ በብዙ ሰውነት አካላታችን ላይ ይንጸባረቃል። የተለያዩ የጉበት በሽታዎች አሉ። የተለመዱት ሲሮሲስ፣ ሲስቲክ ህመም፣ የጉበት ፋቲ ህመም፣ የሃሞት ጠጠር እና ሄፕታይተስ ናቸው። ጉበትዎን ሁሌ የሚንከባከቡ ከሆነ ጤናዎ ላይ ለውጡን ያዩታል። የጉበት ጉዳት ካለዎ አስቀድሞ በመታከም የመዳን እድልዎን ያሰፋሉ።
የጉበት ጉዳት ምልክቶች
1) ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
derneuemann / Pixabay ብዙ ሰው የማቅለሽለሽ ስሜት እና ማስመለስን እንደ አደገኛ የበሽታ ምልክት አይቆጥራቸውም። ያለምንም ምክንያት የማቅለሽለሽ ስሜት ወይም ማስመለስ ካጋጠመዎ የእኩላሊት ወይም የጉበት ህመም ያመላክታል። ስሜቱ የተሰማዎ ግን በምግብ መመረዝ ወይንም በሌላ የተያያዘ ህመም ከሆነ የጉበት ጉዳት የመሆን እድሉ ትንሽ ነው። የጉበት ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች የማይለቅ የማቅለሽለሽ ስሜት ይሰማቸዋል። ይህ ስሜት የሚመጣው የጉበታችን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን የማስወገድ ሃይል ስለተዳከመ ነው። የምግብ አፈጫጭ ለውጥም ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ያስከትላል። በየግዜው የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ ስሜት ጤናችንን በከፍተኛ ደረጃ ስለሚያውክ የዶክተር ክትትል ያስፈልገዋል።
2) የድካም ስሜት
የማይለቅ የድካም ስሜት የጉበት ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል። የምንመገበውን ምግብ አፈራርሶ ወደ ሃይል የሚቀይረው ክፍል ጉበት እንደመሆኑ ሲጎዳ ስውነታችን ሃይል ያንሰዋል። ከዛም አልፎ ጉበት ለማጣራት የሚቸግረው መርዛማ ንጥረ ነገሮች ሰውነታችንን ያዳክሙታል። የድካም ስሜት ሌላ እዚህ ከተጠቀሱት ስሜቶች ጋር አንድላይ ከተሰማዎ ዶክተርዎን ማማከር አለብዎ።
3) የምግብ ፍላጎት መቀነስ
የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሌላ የጉበት ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል። የምግብ ፍላጎትዎ ከቀነሰ እና እዚህ ከተጠቀሱት አንድ ሌላ ስሜት ካለው ዶክተር ማማከር አለብዎ። የጉበት ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች የምግብ ፍላጎታቸው ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ይችላል። ይህም የሚሆነው ጉበታችን ሃሞት ማምረት ሲከብደው ነው። ሃሞት ምግብ እንዲፈጭ የሚያደርግ ንጥረ ነገር ሲሆን የሱ ምርት መቋረጥ የምግብ ፍላጎታችን እንዲጠፋ ምክንያት ይሆናል። የምግብ ፍላጎት መቀነስ እራሱ ድካም ስሜት እንዲሰማን በማድረግ ለማገገም እንድንቸግር ይሆናል።
4) ምግብ አለመፈጨት
ሊቨር የሚያመርተው ሃሞት ለሆድ መፍጨት አስፈላጊ ንጥረ ነገር እንደመሆኑ፣ ጉበት ሲጎዳ የሚያጋጥመን የመፍጨት ችግር ለተቅማጥ ሊያጋልጠን ይችላል። የሃሞት መመረት ችግር ሃሞት ጠጠር፣ የሆድ መነፋት፣ የሆድ ድርቀት እና አጣዳፊ ተቅማጥ ሊያመጣብን ይችላል። ጉዳቱ ከፍተኛ ሲሆን ከፍተኛ የሆድ ህመም ስሜት እንዲሰማን ምክንያት ይሆናል።
5) የሽንት ቀለም መቀየር
በቂ ፈሳሽ እየወሰድንም ሽንታችን የጠቆረ ቀለም ካለው የጉበት ችግር ምልክት ሊሆን ይችላል። ሽንት ሲጠቁር ወደ ብርቱካናማ ወይም ወደ ቡኒ ቀለም ያጋድላል።ጥቁረቱ የሚከሰተው ደማችን ውስጥ የቢሊሩቢን መጠን ሲጨምር ነው። ይህም የሚከሰተው ጉበታችን ንጥረ ነገሩን ለማስወገድ በመቸገሩ ነው። የጠቆረ ሽንት በቂ ውሃ ባለመጠጣት፣ ቫይታሚን ቢ በመውሰድ፣ መድሃኒቶች በመውሰድ፣ በሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፣ በእኩላሊት ህመም እና በኢንዛይሞች እጥረት ሊከሰት ይችላል። ሽንትዎ ለረጅም ግዜ ጥቁረት ካሳየ ዶክተር ማማከር አለብዎ።
6) የቆዳ ቢጫ ቀለም መያዝ
አንድ የጉበት ህመም ምልክት ጆንዲስ ወይም የቆዳችን፣ የአይናችን እና የጥፍራችን ቀለም መበጨጭ ነው። በደማችን እና በቆዳችን ቢሊሩቢን ሲበዛ የቆዳችንን ቀለም ወደ ቢጫ ይቀይረዋል። በደህና ግዜ ጉበታችን ይህንን ንጥረ ነገር ያስወግደው ነበር። ጆንዲስ የጉበት ብቻ ሳይሆን የጣፍያ በሽታ ሊያመላክት ይችላል።
7) የሰገራ ቀለም ለውጥ
OpenClipart-Vectors / Pixabay የሰገር ቀለም መቀየር የጉብት ችግር ሊያመለክት ይችላል። በደንብ የሚሰራ ጉበት ወደ ሰገራችን ሃሞት እንዲገባ ያደርጋል። ይህ ሃሞት ነው ሰገራችንን ቡኒ ቀለም የሚሰጠው። የጉበት ቃጠሎ ወይም ጠባሳ ሰገራችን ቢጫ ወይም ቀይ አፈር መሰል ቀለም እኒዲያመጣ ያደርጋል። አልፎ አልፎ የሚታይ የሰገራ ቀለም ለውጥ አሳሳቢ አይደለም። ነገር ግን ተደጋግሞ ይሚከሰት ከሆን ዶክተር ማማከር ተገቢ ነው።
ሆድ ላይ የሚታዩ ለውጦች
ሆድ ላይ የሚታዩ ለውጦች ሌላ የጉበት በሽታ ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ። የታችኛው ሆዳችን የሚያብጥ ከሆነ ወይም ህመም የሚፈጥር ከሆነ አሲተስ የሚባል በሽታ መገለጫ ሊሆን ይችላል። አሲተስ በሆዳችን የሚፈጠር የፈሳሽ ክምችት ነው። ይህ የሚከሰተው ጉበታችን ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገደ ነው። አሲተስ በሌላ በሽታም የሚፈጠር ስለሆነ ዶክተር ማማከር ተገቢ ነው።
9) የሰውነት ፈሳሽ መያዝ
የጉበት ጉዳት በእግራችን እና ቁርጭምጭሚታችን ላይ የፍሳሽ ጥርቅም በመፍጠር እንዲያብጡ ያደርጋል። ይህ ህመም አሲተስ ከተባለው በሽታ ጋር ይያያዛል። የውሃ አዘል እብጠት ህመም ሌሎች መንስኤዎች ሰውነታችን ላይ የሆርሞን መዛባት፣ የእኩላሊት ችግር፣ የልብ በሽታ እና ሊምፋቲክ ሲስተማችን ላይ የሚፈጥሩ ችግሮች ናቸው።
10) የቆዳ ስሜት መጨመር
andreas160578 / Pixabay ሌላ የጉበት ጉዳት ምልክት የቆዳ ስሜት መጨመር ነው። ቆዳችን በቀላሉ ሊቆስል ይችላል። የደም ቧንቧችን ቆዳችን ላይ ሊያፈጥ ይችላል። እነዚህ ችግሮች ጉበታችን በቆዳችን ላይ የሚፈጠሩ አሳካኪ ሃይሎችን ማጥፋት ባለመቻሉ ነው። ቆዳ ማለስለሻ ቅባቶች መጠቀም ስሜቱን ሊያበርድልን ይችላል ግን የጉበታችንን ችግር ካላጠፋን ሙሉ በሙሉ አያድነነም።
ሌሎች የጉበት ጤንነት መጠበቂያ መንገዶች
መጠጥ መጠጣት ማቆም፣ ማጨስ ማቆም፣ እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ የወይን ፍሬ፣ አፕል፣ አቮካዶ፣ ሎሚ የመሳሰሉትን ጉበትን የሚያድሱ ምግቦች መመገብ፣ በየቀኑ ሁለት ወይም ሶስት ስኒ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት፣ ቫይታሚን ሲ የያዙ ምግቦች መመገብ፣ ጨው እና ስጋ መቀነስ፣ በየቀኑ እንቅስቃሴ ማድረግ። መራመድ፣ መዋኘት፣ መሮጥ ይረዳሉ፣ የሆድ ድርቀት እንዳይኖርዎ መጠንቀቅ፣ ኮሌስትሮል መጠንዎን መቀነስ፣ ስኳር በሽታ ካለብዎ የደም ስኳር መጠንዎን ቁጥጥር ያድርጉ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ