በቃ! በቃን ሱባኤም ነው። በሱባኤ ወቅት በድዋ እና በፆም የተወለደ።
በቃ! በቃን ሱባኤም ነው። በሱባኤ ወቅት በድዋ እና በፆም የተወለደ።
• በቃን! ህዝባዊ አብዮትም ነው። ለህዝባዊ አብዬት የሥርዓት ለውጥ!
„ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)
በቃ!
ተደሞው በቃ ዕድምታው ለድርርድር የሚሆን አይደለም። ድርድር ውል ለበቃ! ግርግር ነው።
በቃን! ለማድመጥ ጆሮ የሌለው ፖለቲከኛ ዓይን ያለው ጆሮ ከቤተ - እስራኤሎች ቢያፈላልግ ይሻለዋል።
በቃ! ማለት በቀላል ቋንቋ ብርጭቆ ውሃ ቢሞላ ከዛ ላይ ጠብታ መጨመር አይቻልም። እንደዛ ማለት ነው።
በቃ ተርጓሚ አስተርጓሚ አያስፈልገውም።
በይቅርታ፤ ብምንትሶ፤ በቅብርጥሶ፤ በጓዳ ድርድር የሚሆን አይደለም። በቃ! ለዛውም የህዝብ በቃን! የሚጨመር የሚቀነስ ቦታ የለንም ነው። የምናደምጠው - የምንዋዋለው - ውል የለም ነው። ይህን የበቃን! ንቅናቄ ለመመራት የህልውና የተጋድሎውን ዲስፕሊን ለመሸከም ዲስፕሊኑን ምን እና ምን ነበሩ ብሎ ማጠዬቅ ይገባል። የህልውና ተጋድሎ የጫጉላ ሽርሽር አልነበረም እና። የህልውና ታገድሎ የግጥግጥ ዳንኪራ አይደለም እና።
ድንቁ ነገር ረመዳን በገባ ማግሥት ፤ ሁዳዴ ሳይጠናቀቅ ነው ይህ ሞገድ የተነሳው። ሞገዱ ከሰማይ ነው ብዬ ነው እማምነው። ግልገል በለስ ላይ ነው የተጀመረው። የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ቀጠሉት፤ ፍኖተ ሰላም ተከተለ ከዛ ሙሉ ጎጃም እና ሙሉ ወሎ በአኃቲ መንፈስ እራሱን አደራጅቶ ቀጠለበት።
ተጋድሎው የህዝብ ነውና የኮፒ ራይቱ ነገር ላይ ከማተኮር የወለቀ፤ የሾለከ፤ የተነደለውን የኃላፊነት ልክ ቁጭ ብሎ መመርምር ያስፈልጋል። በቃን! ምንም ነገር አናስተናግድም ነው። ቅድመ ሁኔታም ድህረ ሁኔታም አንሻም ነው።
ዘመን ከዘመን የተከዳው የአማራ ህዝብ መሪ ቢያገኝ ከመጨረሻ የማያወላዳ ውሳኔ ይደርስ ነበር። ግን በግን መበጋገን ነው።
የቤተ - መንንግሥት የሻይ እና የቡና ሴሪሞንያል ድርድር ምን ያህል ግብር እንዳስገበረ ይታወቃል። በጣና እና በላሊበላ ጉዳይ ቅልጥ ያለ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄዷል። ገና በማለዳው። ከዛ በታጉቱ ተማሪዎች ላይ ገድል ታዬ። ከዛም በተዋህዶ ላይ በደረሰው ጥቃት ያን የመሰለ ድንቅ ህዝባዊ ትዕይንት ተካሄደ።
ይህም ብቻ አይደለም እቴጌ ጎንደር 45 ቀናት ምህላ ላይ ነበረች። እስልምናም እንዲሁ ለተወሰኑ ቀናት ጸሎት ላይ ነበሩ እዛው ጎንደር ላይ። ይህን ሁሉ ተጋድሎ ግን መሪ አላገኜም ፈሶ ቀረ። የልምድ፤ የክህሎትም ችግር ያለ ይመስለኛል። አማካሪም እንዲሁ።
የኔታዋ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የምህላ ተደሞ ጎንደር በአርምሞ! ከጥቅምት 01 ቀን እስከ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓም።
የአሁኑንስ እንደምን ሊመራ? እንዴትስ ሊተዳደር? ምንስ ሊሆን ይሆን? ያሳስበኛል።
ምክንያቱም የማህበራዊ ንቃተ ህሊናን የሚሸከም ህዝብ አለ። የተደራጀ ቋሚ የሆነ ተቋም እና ሙሴ ግን የለም። ለዚህ ነው ያ ሁሉ ግብር የተከፈለለት የጎንደርወጎጃም የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ፈሶ የቀረው። ያተረፈው ነገር ምንም የለም።
ብዙ ተቋማት ተመሰረቱ። ለአማራ ዕንባ የሚያስቆም ሰቆቃ የሚገታ የተገኜ ነገር የለም። ሌላው ቀርቶ ውጭ አገር ያሉ የአማራ ተቋማት ሥማቸው ነው እንጂ አማራነት የሚተጉት ለብሄራዊነት ነው። የህልውና ተጋድሎው ቋሚ መንፈስ አላገኜም። ሲጀምሩት በሌላ መንፈስ ተጠልፈው ሚዲያ ላይ ተስፋው ተቀብሮ ይቀራል።
• ለበቃን! ለጠፍ አያስፈልገውም።
• በቃን ጨርቅ አይደለም በሜትር የሚመተር በቦንዳ የሚቸረቸር። ወይንም ጨርቁ አደጋ ሲገጥመው የሚጣጣፍ እንደ ድሪቶ።
በቃን! ፖለቲካዊ ውሳኔ ይሻል። ፖለቲካዊ ውሳኔ ደግሞ የሥርዓት ለውጥ ነው። የማያዳግም ቋሚ ህዝባዊ መፍትሄ የሚያሰጥ። በቃን! አብዮት ነው።
• የኢህዴግ ጉራጅ ኦነጋዊ የገዳ ኦዳም ልኩን አውቆ ለህዝባዊ ውሳኔ አፋጣኝ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል። ለዚህ መፍትሄ ያፈለቁት አቶ ልደቱ አያሌው ነበሩ። ያ ቢደመጥ ዛሬም የምናዬው ነገም የሚመጣው መከራ ይቀር ነበር። ከሳቸው ቀድመው ነብዬ ብ/ጄኒራል አሳምነው ጽጌም ተናግረዋል። በጥይት ተደብድበው የተረሸኑትም በዚህ ምክንያት ነው። መስዋዕትነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ የዝክር ውሎ ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21.04.2021
ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር።
ተጋድሎዬ ለሱፍ እና ለገበርዲን ድልድል ሳይሆን ለሥርዓት ለውጥ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ