ማህበራዊ ንቃተ ህሊና እና ማህበራዊ ንቅናቄ ሰቆቃው እንጂ ፕሮፖጋንዳ አላመረተውም።

 ማህበራዊ ንቃተ ህሊና እና ማህበራዊ ንቅናቄ ሰቆቃው እንጂ ፕሮፖጋንዳ አላመረተውም።
ዕለተ ሮቡ ማዕዶተ ተናኜ
በከበበሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።

„ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)

ዛሬ ማዕዶተ ተናኜ ስለሆነ የሃሳብ ቀን ነው።
እምጽፈውም ትዕግሥቱ ኑሯቸው ለሚያነቡ ቅኖች ነው።
• ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ምንድን ነው? በጭልፋ ...
ማህበራዊ ንቃተ ህሊና የህሊና ማቹሪቲ ነው። ህሊና የነቃ እና ያልነቃ ተብሎም ይከፈላል። ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደረግ የግለሰብ ንቃተ ህሊና ሲደረጅ እና ይህ የግለሰብ የንቃተ ህሊና አቅም ወላዊ ወደ መሆን ሲሸጋገር ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ይባላል። ማህበረወዊ ንቃተ ህሊናው ማህበራዊ ንቅናቄ ሊፈጥር ከቻለ አብዬት ነው የሚሆነው።

አብዮት በሳቢያ ሳይሆን ምክንያታዊ በሆነ አምክንዮ የሚፈጠር ነው። በሳቢያ እና በምክንያት መሃከል ሰፊ የፍልስፍና ልዩነት አለ። በቀላሉ ሳቢያ ጫሪ ሆኖ ግን ጫፍ ቀሪ ነው። የሳብያ ውጤት ተላላ ነው። ለጥገናዊ ለውጥ ብቻ የሚሆን ነው።

ምክንያታዊ ግን ከሥር ተነስቶ ቁንጮ ፍላጎት አቀንቃኝ ነው። ነገር ግን መሪ ይሻል። እንደ እና ፊደል ካስትሮ፤ ቼጎቢራ አይነት ማለት ነው። የዓለምን ሚዛን ያስጠበቀውም ያ ዝልቅ ተጋድሎ ነው።

• መከራ የወለደው የበቃን አብዮት!

ወደ ቀደመው ስመለስ ይህ ያዬነው የቆረጠ ትዕይንተ ህዝብ በፕሮፖጋንዳ የመጣ አይደለም። ፕሮፖጋንዳው ቢሆን ቅቤ አቅልጡ፤ የሞድ መኮንኑ፤ የፓርክ ሚኒስትሩ፤ አጤ ዝናቡ የሄሮድስ ዶር አብይ አህምድ ፕሮፖጋንዳ ኾሽታም አያስነሳም ነበር። በአማራ ክልል እሳቸው ከመጡ ወዲህ 5 ታላላቅ ገድለኛ ህዝባዊ ንቅናቄ ተፈጥሯል። ምኞቶኞች አርቲስት አልማዝ ስታልፍ ነፍሷን በገነት ያኑርልን እና ነካክተውት ነበር። ለብ አላለም። እኔ ቤቴ ሆኜ ጅልነቱ ይገረምኝ ነበር። እስቅም።
ማህበራዊ ንቅናቄ በሌላ አምክንዮዊ ገፊ ኃይል እንጂ በግለሰቦች መልካም ምኞት አይወለድም። ፈጽሞ። ይህም ሆኖ ከመጠለፍ ሊድንም ላይድንም ይችላል። በኢትዮጵያ ታሪክ ሁልጊዜ እንደተጠለፈ ነው። ቢጠለፍም ጠላፊው በዲስፕሊኑ ውስጥ ስላልበቀለ ዲስፕሊኑን መሸከም አይችልም። ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ፊት ይመራል መሪው ተመሪ ሆኖ ያዘግማል። ውሎውም ፈርሶ መሠራት፤ ተሠርቶ መፍረስ ይሆናል።

ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት ማህበራዊ ንቃተ ህሊና የፈጠረው ማህበራዊ ንቅናቄ ሊጠለፍ ይችላል፤ ነገር ግን ወቅቱን ጠብቆ መልሶ ይፈነዳል። አዲስ አበባ ላይ እኔ ይህን እጠብቃለሁኝ። የልቡ አልደረሰም እና።

አሁንም የሚታዬው ገድለኛ የአማራ „የበቃን!“ አብዮት ቢጠለፍ፤ እንዲለዝ ቢደረግ መስዋዕትነቱ ገዝፎ ሌላ ጊዜ ይፈጠራል። ረመጡ አይጠፋም። ማህበራዊ ንቃተ ህሊና የፈጠረው ማህበራዊ ንቅናቄ ድሉ ሊዘገይ ቢችልም ግን ወስጡ ሁሉጊዜ እሳተ ጎመራ ያዘለ ነው።
በማይታወቅ ጊዜ ሊፈነዳ ይችላል። ችግሩ ይህ የህዝብ ማዕበል ከመጣ መሪ አልባ ከሆነ ጥፋቱ የገዘፈ ይሆናል። አቅጣጫ ቀያሽ ማህንዲስ በመንፈሱ የተደራጀ፤ በተፈጥሮው የተደራጀ ጭምት ፖለቲከኛ ይሻል።

• ህዝብ መስታውት ነው። ማንም ሰው ከህዝብ የህሊና ዳኝነት አያመልጣትም።
• የ አማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ከተፈጠረባበት ከሐምሌ 5 ጀምሮ አለ እንዳለ ውስጥ ውስጡን እንደተንተከተከ። ጠቅላዩ በመጀመሪያው ምቅደመ ጉብኝታቸው ሰይፋቸውን ያሳረፉበት ሲሆን ከዛ ቀደም ግንቦት 7 እና ሪሞርኬዎቹ ብዙ በጣም ብዙ „የነጻነት ኃይል „ እያለ አታካች ጊዜ አሳልፈናል።

የሚገርመው እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ደፍሮ የ አማራ የህልውና እና የመንነት ተጋድሎ ብሎ የሚጠራ የፖለቲካ ድርጅትም፤ የፖለቲካ ተንታኝም እንብዛም ነው። ዕውቅና ያልተሰጠው ተጋድሎ ግን ረመጡ ቀጥሏል። እሳተ ጎመራ ነውና። ሂደቱ …

(1) የመጀመሪያው እንኳን ደህና መጣህልን። "ሺ ዓመት ንገሥልን" ነበር። አምነን ተቀብለንኃል ነበር።
(2) ሁለተኛው እዬጠረጠርንህ ነው ለተፈጥሮ ሃብታችን እና ለቅርሳችን ትኩረት አልሰጠህም ነው። ያላለቀ ግድብ ምርቃ ተዳፈው ሄደው ነበር።
(3) ሦስተኛው ልባችን እዬሸፈተ ነው። ክብራችን ተዳፍረኃል! ልጆቻችን ከሰወርክበት አምጣ! ከገደልካቸው ንገረን ነበር።
(4) አራተኛው ተዋህዶን አቃላኃታል፤ አቃጥለኃታል እጅህን አንሳ ነው ባዕዳዊነት እያዬንብህ ነው ወዮ! ነበር።
(5) አምስተኛው የሰሞኑ በተከታታይ የሚታዬው የማህበራዊ ንቃተ ህሊና የፈጠረው አብዮት ነው። መከራው እራሱ ነው ተጋድሎውን እዬመራ ያለው በህዝቡ። መነሻው ሰቆቃው ምድር ከምትችለው በላይ መሆኑ ነው። በዚህኛው ለድርድር ዝግጁ አይደለነም ነው።

ልቀቀን! ነው።
ልናይህ አንሻም።
ልናዳምጥህ አንፈልግም!
ካህዲ ነህ!
ጋዳይ ነህ! አንፈልግህም ነው።
ሂድልን! ወግድልን ነው።
አክ አንትፍ ነው!
ያስፈራል በጣም። ህዝብ ሲጠላ እንደዚህ ነው። ህዝብ መስታውት ነው።

ህዝቡ መሪ ነው ሊሂቃኑ ደግሞ ለመመራትም አቅም የላቸውም። በተደጋጋሚ ጽፌያለሁኝ። የተደራጀ ሃሳብ እንኳን የለም። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና አጀንዳ ሆኖ አያውቅም። የሚገርመው ይህ ነው።

አሁን መንደፋደፍ ነው። ከፒ ራይቱም እንዲሁ በሽሚያ ይደራል። አዲስ ደግሞ ድርጅትም እናይ ይሆናል። ስንፈረስ ስንሰራ አገር እና ትውልድ መኖርን ተዘረፈ። በቤተ - መንንግሥት ጦርም በአደባባይ ህዝብ ተረሸነ። ከተሞችም ነደዱ። ትውልድም አለቀ።

ሌላው አሳዛኙ ነገር በግልም በወልም የሚጥሩ ሊቃናት የ አማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ስብስብ ብለው የትኛው ድርጅት ውስጥ አንዲገቡ እንደተደረገ አስተውላችኋል ብዬ አስባለሁኝ። ለአማራ የሚቆረቆር ሰው እንደዛ ሊያደርግ ፈጽሞ አይችል። ፈጽሞ።

አገር ውስጥ እዬታደኑ ይታሠራሉ እዚህ ደግሞ ወደ ሌላ ድርጅት ይሸጋገራሉ። የአማራ የህልውና እና የማንነት ተጋድሎ ጠላፊው ስውርም ግልጥም ነው። ሁነኛ የቆረጠ አለገኜም። እንጂ ይህ ሁሉ አቅም ስንት ታምር በሰራ ነበር።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ። አሜን

ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21.04.2021
ተጋድሎዬ ለሱፍ እና ለገበርዲን ድልድል ሳይሆን ለሥርዓት ለውጥ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።