#ምነው ጠፋሽ ከሩህሩኃን የቀረበልኝ ጥያቄ ነው። በስሱ እንሆ።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ፣ ቀናውን መንፈስ
በውስጤ አድስ።" አሜን። (መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፲)
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች፣
የምናፍቃችሁ ማህበረ - ቅንነት፣
የቤተ - ሥርጉትሻ #የልብ ክቡራን ቤተኞች፣
እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብረ ይስፋ ደህና ነኝ።
፳ን ለመጀመር አብዝቶ #ከማድመጥ ጋር ለመገናኜት፣ ለመዋህድም ጊዜ መውሰድ ነበረብኝ።
ይህ ከምዕራፍ ፩ ጀምሮ የማደርገው የተለመደ
ተግባር ነው። ጠቃሚም ጎዳና ነው። ፍላጎትን፣
ሃሳብን አደራጅቶ ለማቅረብ አጋዥ ነው። መልክ
ይኖረዋል። #ቀለምም አለው።
የእኔ የፌስቡክን ዕድል የምመራበት መስመር ነው።
አግዞኛልም።
ዛሬ ሁሉ #ተናጋሪ ነው። ሁሉንም ማድመጥ ባይቻልም፣
የዘመኑን ግሎባል፣ አህጉራዊ ይሁን ብሄራዊ የፖለቲካ
ባህሪ ለማወቅ፣ ለመረዳት #ጥሞና ወስዶ፣ ለማድመጥ
መፍቀድ ከበርካታ የግድፈት ማዕበል ይታደጋል።
የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍም ከዲጅታሉ ዓለም ጋር ተለዋዋጭነቱ ፈጣን ስለሆነ ጨምቶ የግል ገፊ ስሜትን ማስከን ይጠይቃል።
ወጣትነት ተጠናቆ ወደ ጉልምስና ሲገባ የስሜት #ፍላትን ይሁን የፍላጎት ሱናሜን #ረብ ማድረግ፣ የአቋም ይሁን ውሳኔን ችኮላን #ተግ አድርጎ መመርመር፣ በእጁጉ ያስፈልጋል። ሙሉ #ዕድሜ በራሱ ከተደመጠም ያስገድዳል። ሁልጊዜ ወጣትነት የለምና።
ሌላው በእናት አገር በፈላስፊት ኢትዮጵያ እና በህዝቧ #የውስጥ ጉዳይ መዋለ ዕድሜን ሙሉ እንደ እኔ የሸለመ ሰብዕና መኖርም አለና በስሱ ከመኖር ጋር ለመወያዬት፣ ለመነጋገር፣ ለመፈታተሽም በአደብ እራስን እና የመኖርን ፍላጎት ለማጣጣም #ስኩን ጊዜ ያስፈልጋል።
እንደ እኔ ለረጅም ጊዜ፣ በተከታታይ አገር በቀል ሁነቶች ጋር መንፈሱን በሥርዓተ ተክሊል አጋብቶ ለሚኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ #ድካምም ይኖራል። በቤተሰብም ይሁን በአገር እንደሰው በሚደርሱ የውስጥ መራር የመለያዬት ሃዘንም፣ በጤናም መጎዳት አለና ለዛ #ጥገና ጊዜ ያስፈልጋል።
ሌላው በተጓዳኝ የሚሠሩ ተግባራትንም ስክሪፕት ማረም፣ የራዲዮ ዝግጅት ሊሆን ይችላል፣ ያልተደመጡ ሊደመጡ የሚገባቸው የዕውቀት ዘርፎችን ለመዳሰስም፣ የቤት ውበትን መጠበቅ ሊሆን ይችላል #ቀለም መቀባት ሊሆን ይችላል ብቻ እኔን በሚያስፈልጉ ሰብዓዊ ጉዳዮች እንደዚህ በተደሞ መርምሮ የጎደለውን ለማስተካከልም ጊዜ ያስፈልጋል።
መኖር በባከነ ቁጥር መባተል የሄሃሳብ ፍልሰትም፣ መፋለስም ይገጥማል። ይህ ደግሞ ለዘመናት የተገነባን የግል ሰብዕናን ያጎሳቁላል። ስለዚህ መኖር ሳያኮርፍ መቅደም ይገባል። #አትኩሮትን መመገብ። #ማስተዋልን ማጠጣት።
ሌላው ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት የሉሉ፣ የአህጉሩ፣ የብሄራዊ የኃይል አስላለፍ ፈጣን ተለዋዋጭ ሁኔታም በጣም #ሰክኖ ነገን አስቦ፣ ትውልድን #ጸንሶ ማድመጥ፣ መመርመር፣ አቅጣጫውን ተየት ወደዬት እንደሆነ መመርመር በአደብ ያሰኜዋል።
ሌላው በገጠመኝ የሚፈትኑ #ግብግብ የሚያሰኛቸው ክስተቶችም ይኖራሉ።
ፍጽምናከማንም አይጠበቅም። በሥራ ሂደት የሚፈጸሙ ግድፈቶችን በምልሰት ለመመርመር #ጥሞናዊነት ያግዛል።
ከላይ በስሱ በጠቃቀስኳቸው ጉዳዮች ጋር ተያያዥ የአቅም #ጥማት ያለባቸው የመኖር ጅረቶችን የእኔ ብሎ አትኩሮት መስጠት ይገባል።
ዛሬ ዕለተ ሰኞ ቀዳማይ ሰኞ #ምዕራፍ ፳ን ጀመርኩት። እንደ አንድዬ ፈቃድ የምዕራፋ ቆይታ የተሳካ ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው ከፈጣሪ እና ከማህበረ ቅንነት ጋር።
እግዚአብሄር አምላክ የአፈሙዝ ድምፆች #ጸጥ የሚልበትን ዘመን ለሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ ይስጥ። አሜን።
በዚህ በአዲሱ ዘመን የሰማይ እና የምድር ልዑል፣
የሰማይ እና የምድር ንጉሥ፣ የሰማይ እና የምድር ጌታ አማኑኤል አባቴ የውስጥ #ሰላማችን በሰጠን ልክ #ለሁላችን ያስክንልን። አሜን። አባታችን #ይቻለዋል። የሚሳነው የለምና።
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፣ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Seladssie.
28/09/026.
የናፈቀኝ የጸና #ሰላም እና ዕውነታዊ ርትህ ዕውናዊነት!
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ