የሱማሌው ችግር የተፈታበት መንገድ እንደገና ታጥቦ ጭቃ - ዳጥ ላይ? ህም!

ጭጎጎታማ ዳመና።
„ሰማይ ጽድቁን ይናገራሉ፤
እግዚአብሄር ፈራጅ ነውና።“
መዝሙር ፵፱ ቁጥር ፲፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23.01.2019
ከእመ ዝምታ።


ጤናይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ። ዛሬ ብራ ነው። ብራ እወዳለሁኝ። በዛ ሰሞን ዘሃበሻ ስለ ሰብዕዊ መብት ጽኑ ተሟጋቹ አቶ ሙስጡፋ ዑመር ከሥልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ሹክ ብሎን ነበር። መርዶ ነበር ለእኔ። ድክም እያለኝ ነበር ያዳመጥኩት። መረጃው ቀዝቃዛ ነበር ስቀበለው። ብርድ ብርድ ብሎኝም ነበር። 

ዛሬ ደግሞ አንድ አጭር ውይይት ከአንድአፍታ አዳመጥኩኝ። እጅግ እማከብራቸው አክቲቢስት አቶ ጀማል ዲሪዬ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ነው። እሳቸው የፕሬዚዳንቱ የህግ እና የሰባዕዊ መብት አማካሪ መሆናቸው እጅግ ድንቅ ነገር ነው። በዚህ ደስ ብሎኛል። ግን ሊሰሩበት የሚገባው እርግጠኝነት ድጋፍ አልባ ነው። ብረት መዝጊያ የሆነ መንፈስ ያስፈልጋቸዋል።

የሱማሌ ጉዳይ የተፈታበት መንገድ ከሁሉም አገር ውስጥ እርምጃዎች እጅግ የላቀው ነበር ማለት እችላለሁኝ። ታጥቦ ጭቃ እንዳይሆን ግን ስጋት አይሏል።በውጭ ስንመለከተው የኢትዮጵያ ኤርትራን ጉዳይ ጉልሁ ማለት እንደምችለው ነበር ያን እርምጃ እኔ ያዬሁት የአቶ አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ሥር መዋል እና የአቶ ሙስጡፋ ዑመር ወደ ሥልጣን መምጣት የታምር ያህል ነበር የተመለከቱከት፤ ተከታታይ ጹሑፎችንም በአጽህኖት ጽፌ ነበር። ለዛውም ማንም ያን ጊዜ ከቁብ የቆጠረው ባነበረበት ጊዜ ነው እኔ ተደሞውን ያስኬድኩት።

አንድ ሰው የሰብዕዊ መብት ተሟጋች መሆኑ በተለይ በሉላዊ ዓለም ለመስራት መታደሉ የተለዬ ጸጋ ነው ያን ወደ ኢትዮጵያ ኢንቤስት ለማድረግ መታሰቡ ራሱ እንኳንስ እርምጃው ፍትሃት ነበር - ለእኔ። ደስታዬ ወሰን አልነበረውም። አትኩሮቴም ልዩ ነበር።

ለምሳሌ እኔ የክብርት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴን፤ የክብርት ዳኛ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳን፤ የክብርት ወ/ሮ ዳኛ ማዕዛ አሸናፊን ምድባ እንደ ተለመደው አለዬውም። ልዩ ስጦታ እድርጌ ነው እምመለከተው፤ ሰፊ የሆነ የማስተዋል የመሪነት ጥበብም መሆኑን ነው እኔ የምረዳው።

በጽኑ መሰረት ላይ የተገነባ ከሉላዊው ዓለም ጋር በሰባዕዊ መብት ተሟጋችነት መስራት እንዲሁ ከሰፌዴ ላይ ቆለ መቸርፈስ ዓይነት አይደለም። የአብይ ዘመን ጥበቡ የሰለሞን ምስብህክ ያህል ያዬሁበት የህሊናዬ ሚስጢር ነበር ምደባው። እጅግ በተመስጦ ሆኜ ነው እኔ እንዚህን ጉዳዮች እምመለከታቸው።

ሌላው ቀርቶ በዚህ ሰብዕዊ መብት በተከበረበት ዓለም እንኳን የሰባዕዊ መብት ተሟጋች የነበሩ የሶሻል አማካሪዎች ሲኖሮን እኔ እራሴ ዕድሉ ገጥሞኝ ስላዬሁት ልዩ ስጦታ ነው። ተጨማሪ ቅድስና አላቸው። በዚህ ዘርፍ በዘመነ አብይ ያለው የጥረቱ ስፋት መጠን የለውም። ጥረቱ ኩርኩድ አይደለም። ጥልቅ ነው። የተፍታታ ነው ... ዝግም አይደለም። 

እንዲህ እንደ ዋዛ አሉታዊ ኢጎ የሚሰለነቅጠው አይደለም። በፍጹም ሁኔታ አላዛሯ ኢትዮጵያ ከኖረችበት የሴራ፤ የሸር፤ የጠልፎ መጣል፤ የማሳደድ፤ የሥም ማጥፋት፤ የቡቃያ መንቀል ጋር ንክኪ የለውም እርምጃው የአቶ ሙስጡፋ ዑመር ምደባ። ቅን ነበር።
  
በሉላዊ ሰብዕዊነት የሰሩ ነፍሶች በመደበኛ ልዩ ሽልማቶች ናቸው። እነዚህ ሰዋውያን ተፈጥሮውያን ኢትዮጵያ ውስጥ በፖለቲካው ዓለም እንዲሳተፉ ሲደረግ ጣሙም ጠረኑም የተለዬ ነው። ለአዬሩም መድህን ነው። ልዩ የሰብዕዊነት ድንጋጌም ነው  ለእኔ።
በዚህ ስሌት ነበር እኔ አቶ ሙስጡፋ እና የአቶ ጀማል ዲሪዬ ምደባን እምመለከተው።

በመታደል - በመመረቅ - በመባረክ የተሰጠን የዘመን ሽልማት ነው። ለመሆኑ ስለሰው ማስብ እኛ ካቆምን ስንት ዘመናችን ነው? ሁላችንም ብንፈትሽ ወይ በማንፌስቶ፤ ወይ በእምነት ዶግማ፤ ወይ በዝና፤ ወይንም በዘመድ አዝማድ ብቻ ባንዱ ወረርሽን መንፈሳችን ተገዝቷል።

ለዚህም ነው ምርቃትን ለመቀበል አቅም ያነሰን። ለዚህም ነው እኔ ከሚለው ለሌላው ስለማሰብ የተሳነን።

እኔ እንደማስበው እኔ እንደምገምተው የሚሊዮኖች በሱማሌ መፈናቀል ይፈለግ ነበርን? የአብያተ ቤተክርስትያናት መንደድስ ይወደድ ነበርን? የሰው ስቃይ ለማዬት፤ ለማድመጥ ሩጫችን በምን ያህል ኪሎ ሜትር ነበር? ኢትዮጵያ ፍርስርስ ብላ ለማዬትስ ጥድፊያችን ምን ያህል ይሆን? ጊዜ ደጉ ነገን እያበጠረ ያሳያናል። በተለይ ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ያልጠሩ ነገሮች ምርቅነት ያሳስባል። ውዶቼ የዶሮ ቅማል ታውቃላችሁ፤ እውር እከክስ እንደዛ ነው ውስጥ ሆኖ አራጅ ሲሳናዳ ...  

ሱማሌ ወሳኝ የኢትዮጵያ ቀዬ ነው። ጁቡቲ፤ ሱማሌ ላንድ፤ ኬንያ በጎረቤት አገርነት አሉ። ጠ/ሚር አብይ አህመድ የመጀመሪያ የጉዟቸው አቦል ሱማሌ ክልል ነበር። ያን ብዙም ያስተዋለው አልነበረም። ከዛም በመቀጠል በጎረቤት አገሮች ያደረጉት ጉብኝት ከአገር ወስጡ ጋር አዛምደውና አዋደው ያደረጉት የተመስጦ ጉዞ በኦነጋውያን አክቲቢስቶች እንደ ሽርሽር የታዬ ነበር። ነገር ግን የብልህነት ጥልፍ ነበር። 

የአማራር ጥበብ ልቅና ነበር። ያን በማጣጣል፤ በማብጠልጠል የተጉት ብዙዎች ነበሩ። ሳይጠና እርምጃ ከመውሰድ አጥንቶ አላምጦ መዋጥ ይገባ ነበር። የማድመጥ አቅማቸው ልቅና፤ የመብሰል አቅማቸው ብጡልነት የጠ/ሚር አብይ አህመድ ከጥዋቱ ነበር አህዱ ያለው። ማስተዋልን ለሰጣቸው ሰዎች።  

ይህም ሆኖ አዲሱ ለውጥ ማፈራረስን አልተጠደፈበትም፤ የተጣደፈው ህሊናዊ ሁኔታዎችን ሁለ - አቅፍ በሆነ ሁኔታ ማጥናት፤ ማደራጀት፤ አቀናጅቶ በመምራት ነበር። የአገር ውስጡና የጎረቤት አገር ጉብኝት ውጭም አገር ውስጥም ያለው የነፃነት ፈላጊው ወገን ውስጡን እንዲፈትሽ፤ በአገሩ ጉዳይ ላይ አጠቃላይ መረጃ እንዲኖረው አድርጓል ጉብኝቱ አዎንታዊው ውይይቱም።

ሁልጊዜም እኔ እንደምናገረው ት/ቤት ነበር - ለሥርጉተ ሥላሴ። እኔ በዬሄዱበት ቦታ ሁሉ የተነሱ ጥያቄዎች እና የተሰነዘሩ ሃሳቦች ሁሉ በህሊናዬ ሰሌዳ ተጽፈዋል። እጅግ የሚመስጥ ተግባር ነበር የተከወነው በ100 ቀናት ውስጥ።

በአብዛኛው ጉዞ አቶ አህመድ ሸህዲን ነበሩ። ለሳቸውም መልካም አጋጣሚ ነበር። እንዲበቁ እገዛ ተደርጎላቸዋል። ህሊናቸው ከሻገተው የሴራ ፖለቲካ እንዲጸዱ ሰፊ አስተዋፆ ነበረው፤ አብረው ባደረጉት ጉዞ ሁሉ፤  የአሁኑ የሚ/ር ቦታ እራሱ በብዙ መልካም ዜናዎች እንዲበቅል ተደርጎ እንክብካቤ ተደርጎለት ድልዳል ተሰርቶለት ነበር።

ቀድሞ ነገር የቀደመውን በደል ይረሳ ዘንድ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከህዝብ ጋር አገናኝተዋቸዋል። በይፋም አወድሰዋቸዋል። በሰሜን አሜሪካው ጉዞ ከእንቁላል እና ከቲማቲም ዱላ ተርፈው በከፍተኛ ዕውቅና አንዲያገኙ ተደርጓል።

እኛም ለውጡን እስከጠቀሙ ድረስ እሰኪ ይሁን ብለን ከትችትም፤ ከጉሳማም ተቆጥበን ነው የቆዬነው። እንጂ መራራ እኮ ነው በዛ የጨለማ ዘመን የተፈጸመው ጸያፍ ተግባር ሁሉ። እግዚአብሄር በአምሳሉ በፈጠረው ፍጡር ላይ እንደ እንሰሳ ሙከራ ሲደረግበት መኖሩ ራሱ በቂ ነው ሌላ ገመና ሳይታከል።

የሆነ ሆኖ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ጀማል ዲሪ እንደሚነግሩን ከሆነ ሊፈነዳ የተቃረበ ጨጎጎታማ ደማና ሱማሌ ላይ እንዳለ ነው የሚደመጠው። ልዑል እግዚአብሄር እኮ ምልክት ሰጥቷል። ከሰማይ እሳት አውርዷል። ምድር በደቂቃዎች ልተወድም ልትጠፋ ትችላለች እንሱ ለምሳ ሲያስቡ ለቁርስ እዮር ሊዳኝ ይችላል።

አቶ አህመድ ሸህዲን በውነቱ ለእግዚአብሄርን /ለአላህ ምስጋና ማቅረብ ይገባቸዋል። ለዚህ ዘመን ገመናቸው ተክደኖ ባለሟል መሆን መቻላቸው ቢታደሉ እንጂ ሌሎች ይህን አላገኙም። በዛ ላይ ወጣት በመሆናቸው በቀደመው የሴራ ፖለቲካ መነከራቸው በራሱ አንገትን ቀና አድርጎ የሚያስኬድ አይደለም። ያሳፍራል።

በኦነጋውያን በኩል አክቲቢስቶች አንዱ ቀጣናቸው ሲዳማ፤ ሌላው ሱማሌ ነበር። የሱማሌው ችግር አፈታት እንሱ ካሰቡት ውጭ ስለነበር ዱብ ዕዳ ነው የሆነባቸው። በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን ከህወሃት ባለነስ አይሹትም። ሚደያቸው OMN ሰፊ ተግባር ሰርቶበታል። ቀውስን በማነሳሰት፤ በመቆስቆስ።

በዛ ላይ የሱማሌ አክቲቢስቶች ይህን ያህል ዕውቅና ማግኘታቸው የህሊና ረመጥ ነው። እነሱ ደግሞ ከማይክ ውጭ የመወሰን አቅም ባለው ፖለቲካዊ አቋም ላይ አይደሉም
ስለምን? ዶር ለማ መገርሳን ሆነ ዶር አብይ አህመድን ለመተካት ሩቅ ነው። እንኳንስ ኦሮምያ ብቻውን ኢትዮጵያን ይህን የመሰለ የጸዳ ህሊና፤ የክህሎት እጬጌዎች ለማግኘት ባነሰ ግምት 50 ዓመት ይፈጅባታል። ከሚተሳበው በላይ፤ ከሚተረጎመው በላይ ልዩ ናቸው።

ትህትናቸው ራሱ በቂ ነው። የኦሮሞ ሊሂቃን፤ የኦሮሞ አክቲቢስቶች ከአቶ ሌንጮ ለታ ውጭ ያለባቸው ችግር ባልተሰበ፤ ባልታቀደ ሁኔታ መንጨበራቁን ማዕበል ጸጥ ያደረግ የአቅም ልቅና እዛው መንደር መውጣቱ የህሊናቸው ሪህ ነው የሆነው። እሚነሱ የሚወድቁትም በዚህ ነው፤ በገደምዳሜ፤ በቅኔ ፍዳቸውን እያዬ ያሉት አቅሙ የሚደፈርም - የሚተችም ባለመሆኑ ነው።

አሁን ሚዲያ ላይ የሚንጎባለሉት ሁሉ አምቀው የያዙት ሚስጢር ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ በመላ ኢትዮጵውያን ዘንድ ቅቡል በመሆናቸው ነው።

እንዴት አንደምንወዳቸው ልባችን ተከፍቶ ቢዩት ምን ሊሉ እንደሚችሉ አላውቅም። ይህ ነው እያርመጠመጣቸው ያለው እከሌ ተከሌ ሳይባል። በሱማሌ የተለዬ እና ያልተለመደ ምደባም ትክን ነው ያሉት የኦሮሞ አክቲቢስቶች። 

ስለሆነም አያርፉለትም በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ያን የልቅና ጥበብ ለመጎርጎር። ይህን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ልብ ሊሉት ይገባል። ማስተዋላች ከዚህ ላይ ሥራውን መስራት ይነርበታል፤ ቀኝ እጃቸውን ማጣት አይኖርባቸውምም።

ሌላው ብዙም ሲነሳ ያልተደመጠው የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ እና ልቅናው የሚመሰጠው አቅም የአቶ ሙስጡፋ ኡመር ጉዳይ የግራ ፖለቲካ የችግር ምንጭ አማራ ጠልነትን ፊት ለፊት ወጥተው ሞግተዋል።

ይህ ደግሞ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የኦሮሞ ሊሂቃን የሚታመሰቡት ዋነኛ አጅንዳቸው ብቻ ሳይሆን እነሱ ያልወለዱትን፤ ያላሳደጉትን የደሃ ልጅ በዬዘመኑ ለውጥ መጣ በተባለ ቁጥር ሲማግዱ የኖርበት የፖለቲካ ቁማር መለመላውን መቅረቱ፤ አጅንዳ አልባ ማድረጉ የሚታወቅ ነው። ለዚህም ነው ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድም የተጠመዱት። የኦዴፓ የውስጥ ለውስጥ የተወሰኑት ወገኖች የሸጎሬ ጉዞም ይህን ያሰበ ነው።

ሌላው እኒህ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ሙስጡፋ ኡመር በቀጣይነት በዞግ ፖለቲካ አያምኑም። ይህም ሌላው ዱብ እዳ ነው ለ66ቱ ፖለቲከኞች። ምክንያቱም የዜግነት ፖለቲካ በሸሪፎ ነው የሚተረጎመው። አንደበት ሌላ ነው፤ መሬት ላይ ያለው ዕውነት ግራጫማ ነው።

ይህን ለማስታራቅ የቆረጠ ትንበያ እኒህ ብልህ ሰው አላቸው። ይህ ቀጥተኛ አቋማቸው ደግሞ የማግስትን ፈተና ለመፍታት ጠ/ሚር አብይ አህመድ የያዙትን ጉዞ በምህንድስና የሚያግዝ ባይታሚን ነው። እራሱ አማራን ማቅረብ መቻላቸው የኦሮሞ አክቲቢስቶች ሆነ ሊሂቃኑ የውሃ ላይ ኩበት ያደርጋቸዋል። ወደዛ ሊደረግ የነበረውን ጉዞም የተከለከለው በዚህ ምክንያት ነው።

ግን ባያውቁት ነው እንጂ አቶ ሙስጡፋ ዑመር የህሊናችን ቤተኛ ናቸው። ምክንያቱም ከራስ በላይ ምንም፤ ማንምም ስሌለ። እኛም ያቀረበ እናቀርበዋለን፤ ያላቀረብን ደግሞ በመጣህበት ነው። ቀልድ የለም። ሁሉም የራሱ ጌታ ነውና። እድሜ ለጎንደሩ የአማራ ይህልውና የማንነት አብዮት ልብ ገዝቶ በነፍስ ወከፍ ሸልሞናል። ጎጃም ቅኔውም አስተምሮናል። 

ሌላው ብቃት እና አቅም ከዬትኛውም ከቆዬ የኦሮሞ ሊሂቃን ሆነ አክቲብስት ጋር ሲነጻጸር የአቶ ሙስጡፋ አቅም ለማንኛውም ብሄራዊ የሃላፊነት እርከን ብቁ ነው። እኛ አፋችን ሞልተን እንመሰክርላቸዋለን። ይህንንም ደፍረን እንናገራዋለን። ብቁ ናቸው። ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸው ሙሉ ሰብዕና፤ ምራቁን የዋጠ ክህሎት አላቸው። ይህ ደግሞ ለማይክ ዳንኪረኛ ሌላው የዱብ ዕዳ ጫን ተደል መከራ ነው።

በተጨማሪም በሴራ እና በክትር ፖለቲካ እኒህ ደግ ሰው ስላልነበሩበት የዝርፊያ፤ የውንብድና፤ የሸር እና የደባ ማህበርተኛ አለመሆናቸው በራሱ ሌላው የህሊና ሪህ ነው ለአሉታዊ እጎይስቱ።

እኒህ ቅን አንዱን ሳር በመዘዙ ቁጥር ማህበርተኛው ሁሉ ይንጫጫል። ኦህዴድ ላይ ደጋፊ አቶ አህምድ ሸህዲን እንዳላቸው ነው ቃለ ምልልስ ያዳምጥኩት፤ ብአዴን ላይም አይጠፋም። እሾኽ ሁሉ ቦታ አለና።

በምዝበራ ባይሳታፍ እንኳን የጠ/ሚር አብይ አቅም ያብከነከነው፤ እርር ኩምትር ጭምትርትር ያደረገው መንፈስ በማናቸውም ሁኔታ አስተውላለሁኝ። ምክንያቱም አቅሙ የሚገፋ፤ የሚገፈተር፤ ጠቅለል ተደርጎ ቆሻሻ ውስጥ የሚጨመር ሊሆን አልቻለም።

 ጥበቡም ልቅናው ሆነ የማስተዋል ጥርስ እና ከከናፍሩ ልዩ ነው። ያሳሳል፤ ያራካል፤ ያጓጓል፤ ይመሰጣል፤ ያወያያል። ዘመኑ መጸሐፍ ነው። ድክመት የለበትም ማለቴ አይደለም። ድክመትም ስህትም ሰውኛ ነው። ትችትም አይቀርም ሲያሻን እንሰልቀዋለን። 

አላዛሯ ኢትዮጵያ አሁን መምረጥ ይኖርበታል። መዝባሪዎችን/ ካህዲዎችን/ አሸባሪዎችን/ መሰሪዎችን/ በቃላቸው የማይገኙትን/ አደራ በሊታዎችን ወይንስ ለስብዕዊ መብት ንጹህ ተቆርቋሪ ንዑዳንን? ለእኔ ከአስር ሴረኛ አንድ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ሚሊዮን ነው። ቁርጡ እንቅጩ ሊነገራቸው ይገባል ለአቶ አህመድ ሽህዲን።

አትኩሮት የሚሻው ጉዳይ ነገር ቱርክ ነው። የአህመድ ግራኝ ገፊ ሃይልም ቱርክ ነበረ። ህልም አለው ቱርክ። ዛሬም ባለው ሉላዊ ፖለቲካ ቱርክ ያለው ድርሻ ይታወቃል። በ2015 አንድ የቱርክ ኩርድሽ ሲነገርኝ በመላ ዓለም ገንዘብ መስኪድ ላይ በመርጨት ቱርክን የሚያክል የለም ብሎኛል። 

ሽማግሌዎች በከረጢት ይዘው ነው ብር የሚጠበቁት መስኪድ አካባቢ ነበር ያለኝ። ገንዘቡ በሽማግሌዎች ለደካሞች ይሰጥና ከዛ በኋላ ሌላ ግዳጅ ይሰጣል ብሎ ነበር ያጫወተኝ። አንድ ጊዜ ገንዘብ የወሰደ ሊስተኛ አይለቀቀም፤ መረብ ውስጥ ይገባል በማለት ነበር በጥልቀት ያስረዳኝ።

ይህ መላ አውሮፓ፤ እስያ እና አፍሪካ ሁሉ መሰል ተግባር አንደሚፈጸም ነበር ያጫወተኝ። ስለዚህ እንዲህ በቀላል ሁኔታ ሊታይ አይገባውም ለማለት ነው። ነገረ ቱርክ መቼውንም ቢሆን የዛን አካባቢ ሁኔታ ቸል ይለዋል ተብሎ አይተሰብም። ስለሆነም በጥበብ ብቻ ሳይሆን በማስተዋልም ጭምር ሊታይ ይገባዋል።

በተረፈ ቅኑ አቶ ሙስጡፋ ዑመር እና ግልጹ አቶ ጀማል ዲርዬ ስለህይወታቸውም መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል። የምግብ ብክለት፤ የመኪና አደጋ፤ የፈንጅ አደጋ፤ የእሳት ቃጠሎም። ስለዚህም ጠንቃቃ መሆን ይጠብቅባቸዋል።

አላዛሯ ኢትዮጵያ አቶ ሙስጡፋ ዑመርን ካጣች በክራንች ትሄዳለች። ከ10 አቶ አህመድ ሸህዲን አንድ አቶ ሙስጡፋ ዑመር ይበልጣሉ። ስለምን? ከሃጢያት ጋር ንክክኪ ስሌላቸው፤ ብቁም ስለሆኑ፤ የሥልጣን እና የዝናም ጥመኛ ባለመሆናቸው፤ ኢትዮጵያን ውስጣቸው በማድረጋቸው።

ስለዚህም ቅኖች ንጹሃን ድጋፋችሁን በማናቸውም ሁኔታ መስጠት ሲገባ ጠ/ሚር አብይ አህመድም ይህን ዳጥ አንዘላልጦቸው ያልተገባ ውሳኔ እንዳይወሱን ፈጣሪ ይርዳቸው። ከተቻለ ሁለቱንም አቻችሎ ካልተቻለ ግን ማንም ሊተካቸው የማይችለውን አቶ ሙስጡፋ ኡመርን በሙሉ አቅም እና ድጋፍ እንዲሁም በማያ- ስበረግግ ተሰፋ ማስቀጠል የግድ ነው።

ችግሩ አቶ ሙስጡፋ ዑመር የፖለቲካ ድርጁቱ የሶዴፓ አባል አይደሉም። በአንድ የፖለቲካ ድርጅት የቀጥታ ምደባም አለ። በምደባም በቀጥታ አባል የመሆን ልዩ መስመር ስለሚኖር ሙሉ ኮንፊደንስ እንዲኖራቸው ለማድረግ ይህንም ጉዳይ አንድ እርምጃ ወደፊት ገፋ ቢደረግ መልካም ነው። ይህን እኮ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ወደ ብአዴን የተመደቡበትን ጉዳይ ማዬት የሚቻል ይመስለኛል።

እርግጥ ነው የምክር ቤቱን አባል ከሆኑ በኋዋላ በድምጽ ብልጫ ሊረቱ ይችላሉ። ነገር ግን ጥራት ከተፈለገ እሳቸው ሪኮመንድ የሚያድረጓቸውን ሰዎች የማድመጥ እና በዛም ላይ መጽናት ለመካከለኛው አፍሪካም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ የሱማሌ ጉዳይ ወሳኝ ይሆናል።

ደግሞስ ለአንድ አገር ህዝብ ከሰባዕዊ መብት ተሟጋች መሪ በላይ ምን ሊታለም ነው። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ይህ የሰማይ ስጦታ ነው። ስለታደልን ነው ይህን እድል ያገኘነው። ሉላዊ ዓለም ለለውጡ የሚሰጠው አትኩሮት በዚህ መሰረታዊ አምክንዮ ላይ የበቀለ ነው።  

በሌላ በኩል አቶ አህመድ ሸህዲን እስካሁን ላበረከቱት መልካም ነገርም ቢሆን የተገባውን አክብሮት መስጠት ይገባል። መነገዳቸውን አስተካክለው ለመቀጠል ያለው ተስፋ ግን ጎንደሬዎች እንደሚሉ „ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ ነው“ ከዚህ በኋላ ለለወጡ መገድ ኤክስፓዬርድ ያደሩጉ ይመስለኛል። አንባሳዳር ቢሆኑ ይሻላል በካቢኔም ሌላ ተጨማሪ ባለድምጽ ከሚሆኑ ከሚያምሱና ከሚያተራምሱ።

በመንፈስ አቅም አግኝተው ጎልበትው ለመውጣት በዚህ ፈተኛ ወቅት ይህን የመሰለ ጋሬጣ መወጠናቸው የአላዛሯ ኢትዮጵያ አንዱ ሾተላይ ሆነው ነው የማያቸው። እንዴት እንደገና ለራሳቸው ኢጎ ሲሉ የአላዛሯን ኢትዮጵያ ተስፋ ለመቅበር ይወስናሉ?

ብቻ አሁን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ይህን ከብሄራዊ ኩዴታ ባልተለዬ መልክ ተመልከተው ወደ አወንታዊ መንፈስ እንዲመሩ እግዚአብሄር ይርዳቸው። ሁለቱም ዶር ለማ መገርሳም ሆነ ዶር አብይ አህመድ የሚፈተኑበት ትልቁ የእርምጃ ዋልታ ይመስለኛል ይህ ጉዳይ።
ብአዴን በሚመለከት እዬተረታ እንዳለ ነው እኔ የሚሰማኝ። 

አቅመ ቢስነቱ ነው ጎልቶ የሚታዬኝ፤ ሌላው ቀርቶ በዘመነ ህወሃት በብአዴን ሥም የነበሩት አንባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ተጋሩ አሁን በሳቸው ትክ ደግሞ የአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አንባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ እንደሆኑ አዳምጫለሁኝ። 

አቶ ፍጹም አረጋ ረጋ ያሉ እና የአብይን መንፈስ ከውስጣቸው የተቀበሉ ይመስሉኛል። የዶር አብይን ፎቷቸውን ከደረታቸው ለጥፈው አይቻለሁኝ። ብዙም ችግር ይኖርባቸዋል ብዬ አላስብም እንደማለት።

ነገር ግን የአቶ ፍጹም አረጋ የአሜሪካ ባለሙሉ ስልጣን አንባሳደር መሆን ከከምሴ ኦሮሞ ምን አልባት ብአዴን ላይ የኦዴፓ ሰው በመጥፋቱ መሰለኝ እንዲህ ፍጥጥ ያለ እርምጃ ኦዴፓ የወሰደው፤ በዚህ ሂደት ግን አማራ መቼ ነው የሚታመነው ማለቴ አለቀረም። ትንሽ ጎሻ ደመን አለብኝ።

ወትሮም ለአማራ ላለመስጠት ነበር ከብአዴን ተጋሩ ተፈልጎ የአሜሪካን አንባሳደርነት የተሰጠው፤ አሁን መሰሉ የዚያ ግልባጭ ነው የተከወነው፤ ሌላው ቀርቶ አሁን ባለው የሉላዊ የኢኮኖሚ ጉባኤ ከአዲሱ  የአንባሳደርነት ቦታ እንዳለቸው ተነግሮ አቶ ፍጹም አረጋ ስለምን ሲዊዘርላንድ ላይ እንዲገኙ እንደ ተደረገ ሁሉ አይገባኝም፤ የገባኝ ትልቁ ነገር ብአዴን የመወሰን አቅሙ ቁልቁል ስለመሆኑ …

ጉዳዩ አይደለም ብአዴን መልቀቅ ነው ደጉ - ሩህሩሁ - ግዴለሹ ሥልጣን የማይስፈልገው ተነብርክኮ አድርጉልኝ እያለ ተጠዋሪው እና ተጠማኙ አይዋ ብአዴን …  ሽልማትስ ለእሱ ነበር¡ ሥልጣን የማይፈልግ ቸር የፖለተካ ድርጅት ፕላኔታችን አልፈጠረችም ከብአዴን በስተቀር።

ብቻ አሁን በኢትዮጵያ መንግሥት ጥንቃቄ የሚያስፍለጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። በወያኔ ሃርነት ትግራይ መንገድ ብዙም አያዋጣም። ምክንያቱም አንድ ጊዜ መንፈስ ከተናደ መመለስ ጋዳ ሰለሚሆን። ህዝብ ከለገመ ደግሞ ምህንድስናው ጨለማ ነው የሚሆነው። ወይንም ተሻለ ቢባል ግራጫማ።

ሌላው ኩዴታ ሆይ! እባክህን ገላግለን የሚሉ ብዙሃን ደግሞ መኖራቸው ልብ ሊባል ይገባል። በተገኘው አጋጣሚ ሱባኤ ላይ ያሉ የኩዴታ መንፈስ ጠረን ሲያሸቱ የሚውሉ ተስፈኞችም አያርፉም። ቀዳዳ በመፍጠር፤ ትርትር በማበጀት።

ስለሆነም ኦዴፓ ብአዴንን መጫኑን በልክ ቢያደርገው መልካም ነው። በዚያ ዙሪያ ዲታ መንፈሶች አሉ ለለውጡ ማገር የሆኑ። እነሱንም ማሰብ ይገባል። በዚህ ባልጠናው ጥንስስ ዘመን በሁለገብ ጥንቃቄ ማድረግ በጥበብ ቢሆን ይገባል።

ዕውነት ለመናገር የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩን የያዘው ኦዴፓ ብዙም አንበሳደር ላይ ባይጋፋ እና ባይሯሯጥ ለሥልጣን መልካም ነበር፤ ብልህነት ይበጃል። የማያዩ የሚመስሉ ዓይኖች ሁሉ ያያሉ፤ የማያዳምጡ የሚመስሉ ጆሮዎች ሁሉ ዛሬ ላይ ያዳምጣሉ። 

በቀደመው ቢሆን ጉዳያችን አይደለም። የፈለገው ቦታ እኛን አይመከተም። ኢትዮጵያዊ ዜጋ ናችሁ ተብለን ስለማናውቅ። ባይተዋር ነበርን። አሁን እኔ እዚህ ሲዊዝ አንባሳደር ማን ይሁን አይሁን፤ ጽ/ቤቱ የት ይሁን አይሁን አጀንዳዬ ሆኖ አያውቅም። አሁንም ቢሆን። ትዝም አይለኝ። ያው አጠቃላይ ሁኔታውን በተደሞ ስመለከተው ክፍትት እንዳይኖር ጥንቃቄ ግድ ይላል ያው ሥርጉትሻ ለማውያን አይደለች።
  
አሁን ነፍስ ያለው መንግሥት አለ ስለምንል ሚዛኑን የጠበቀ ብቻ ሳይሆን ያፈጠጠ ነገር ባይኖር ምርጫዬ ነው። ይናዳል። መንፈስን ለመገንባት ብዙ ተደክሟል። እርግጥ ረቂቅ ነው። በስውር ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሏል። በሽታ ላይ የወደቁ ዜጎች እንዳሉም ማሰብ ይገባል።

መታወቅ ያለበትዝም ተብለው የሚታለፉት ነገሮች ሲበዙ ስለሚገለሙ። መግልማቱ ደግሞ ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ስለሚሰደድ … የአሜሪካ የ አንባሰደርነት ቦታ ምደባ ሚዘናዊ አይደለም የአብይን ዘመን በፍጹም ሁኔታ ተጋላጭ አድርጎታል።

በመጨርሻ … አቶ ሙስጡፋ ዑመር ጠ/ሚሩ ለማግኘት ምንም ዓይነት ማዕቀብ ሊጣልባቸው አይገባም።  ደጅ መጥናትም የለባቸውም። ድምጻችን ስለመሆናቸው አብክሬ መግለጽ እወዳለሁኝ።

ለዚህ መሰል ነፃነት ነው ሁለመናችን የገበርነው። የሰብዕዊ መብት ተሟጋች መሪውን በቀጥታ የማግኘት መብት አለው። እኔ እኮ ጽፌ አንድም የከሸፈ ማምልከቻ የለም በውጭ አገር ባሉ መሪዎች። እና በእኛ መንግሥት የራሱ መንፈስ፤ ለምኖ አሳምኖ ያመጣውን ነፍስ እንዲህ ጥግ አጥቶ የሚንገላታበት ምንም ምክንያት የለም።

ለዘራፊ፤ ለገዳይ፤ ለአሳዳጅ በጀት ተመድቦ፤ ክብር እና ልዕለና ተስጥቶ በስደት ሲንከራተት ለነበረ አንድ ነፍስ መሆን ያልቻለች ኢትዮጵያ? አንድ አቶ ሙስጡፋን ማስተናገድ እንዴት የጠ/ሚር ጽ/ቤት ይሳነዋል? ማህጸን ደም ያነባል። ለሰብዐዊ መብት ተሟጋች የፕሮቶኮል ክትር? ያሳፍረኛል …. ሳስበው እራሱ …

ሌላው በህብር ራዲዮ እና በቢቢኤን የዘወትር ታዳሚ የነበሩት የረጉት እና የሰከኑት አቶ ጀማል ዴሪዬ ቢሆኑ የሞቀውን የጀርመን ኑሯቸውን ትተው መሄዳቸው ሊያሰከብራቸው ሲገባ ሊያዝኑ አይገባም።

እጅግ የሚመስጡኝ ብቁ ታታሪ ናቸው እኔ ሳዳማጣቸው። ከሁሉ በላይ በዛ በትርምሱ ዘመን ጥርት ያለ አቋም ነበራቸው ለዘመነ አብይ መንፈስ። ቅን የሆኑ ነፍሶች ቅኖችን ሲያገኝ ጋሻ እና መከታ መሆን ይገባቸዋል። 

ዶር ለማ መገርሳም ሆኑ ዶር አብይ አህመድ ለእነዚህ ነፍሶች በቂ አትኩሮት፤ በቂ ዕውቅና ብቻ ሳይሆን በበቂ ሁኔታ ድጋፍ ሊያድርጉላቸው ይገባል ባይ ነኝ። ሊያደምጧቸው ይገባል።

አውታሮቻችን ናቸውና። ሌላው አትኩሮት የሚያስፈልገው ጂጅጋ ከተናደ ድሬ ላይም ሌላ ፈንጅ ይኖራል … አሁንም የሚደመጠው መልካም ዜና አይደለምና።

አንድ ነገረ ግን ዶር አብይ የሰው ነገር የነገረ ሰሪ ነገር ይገባቸዋል፤ ያዳምጣሉን? ይህ ከሆነ መቼም ተስፋዬ ክው ብሎ ነው የሚደርቀው፤ ስንታጨድ ስንወቃ ስንገረገብ የኖርነው እኮ በዚህ መሰሉ ጉዳይ ነው ... 

ብቻ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን ብያለሁኝ፤ እራሳቸውም አቶ ሙስጡፋን አግኝተው ማድመጥ ሲገባቸው በስማ በለው ከሆነ ነገርዬውን እያስኬዱት ያለው እኔው ከውስጤ አዝንባቸዋለሁኝ።  ጊዜ ሳይጠፋ እነ አባ ቅንዬን አቶ ሙስጡፋን እና አማካሪያቸውን አግኝተው ሁኔታውን መረዳት ይኖርባቸዋል። ጊዜ ማጥፋት አይኖርባቸውም ወደ አገር ሲመለሱ። ለነገሩ በሰላም ጉዳያቸውን ፈጽመው አገር መግባታቸውም ያሳስበኛል። ጭንቀታም ነኝ እና።

Ethiopia: “ፕሬዝደንቱን ከስልጣንን ለማስወገድ የተደረጉ ተጨባጭ ማስረጃዎች አሉ!”
Published on Jan 22, 2019

Ethiopia:አዲሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር SBS ራዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው!


                                               የኔዎቹ ኑሩልኝ።

                                                 መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።