#አንዱ #የእኛ #ግርማ - የዘመን ሁነኛ! የሚሊዮኖች ድምጽ ይጮኃል!

 

የሚሊዮኖች ድምጽ ይጮኃል! አዳኝን ገድሎ የውስጥ ሰላም ይሰደዳል። ለገዳዮች በከንቱ የፈሰሰው የፈው የደም ጠብታ ሁልጊዜም ይጮኃል! እዮራዊ ርትህ ይሻልና!
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
 
 
 
 
 
 
#አንዱ #የእኛ #ግርማ - የዘመን ሁነኛ!
 
ዕንባ~~~~ ባባ
በዕንባ~~~~ ዘንባባ
ስለራሱ~~~ አነባ።
በባሩድ~~~ ድብደባ
በጭካኔ~~~ ደባ
ዕንባ~~~ ባባ
ስለራሱ አነባ።
የሰውነት~~~~ ዓርማ
ነበር~~~ ለእማማ
#አንዱ የእኛ ግርማ
የዘመን ሁነኛ!
ቡቃያ~~~ ሲነቀል~~~ሲነቀል
ዋይታ~~~ ሲበቃቀል~~~
እህህህ~~~#ህህ ሲተከል --- ሲተከል፦
ንፁኃኑ በግፍ እንዲህም ሲገድል
ዕንባ ይኽው ባባ
ስለራሱ - አነባ።
የበቀሉ ብቅል #ከ-አረሙ ከርፍቷል
ትውልድ በምንጣሮ መጠጊያ ተነጥቋል።
ዘረፋ - ዘረፋ -- የትንታግ ዘረፋ~~~~
የእስትንፋስ ዘረፋ~~~ የመኖር ዘረፋ ---
ዘረፋ~~~~ዘረፋ የዕድሜ ----
ዘረፋ --- የትውልድ ዘረፋ ~~~
06/02/2025
12.00 ሰዓት።
ቢንተርቱር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08/02/2025

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?