ከጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ።

 

"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"

 
 
መምህር፤ መርጌታ፤ ጋዜጠኛ፤ ርቱዑ፤ ሩህሩህ፤ ጽኑ ወጣት። እሱን የሰጠን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን። ለእናቴ፤ ለክብርቴ፤ ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ቤተክህነት እንደ ልጅነቴ ይህን ባለ ቅብዓ ሽልማት ብትጠቀምበት። ዬተከበረ፤ ዬተደላደለ ቦታ በአማካሪነት ሰጥታ ትውልድ ፋናውን ይከተል ዘንድ ዕድል በሩን ብትከፍት እመኛለሁኝ። ተስፋ ዬእግዚአብሄር ነውና። ተስፋ አደርጋለሁ። እናት ቤተክርስትያኔ የእኔን የትቢያዋን ልጇን መሻት ብታደምጥ። ዛሬ ለደወለችው የደወል ንቅናቄ የዛሬ አራት ዓመት ጽፋዋለች፤ አስተምራዋለች። እናቴ የህልውና አደጋ ላይ ናት ንቁ፤ ትጉ የሚል ሳምንታዊ መርኃ ግብር በድወሏ ድምጽ ብቻ ታቀርብ ዘንድ አስቀድም፤ እጅግም ቀድማ ተናግራለች። ፖለቲከኞች ጥሞና አያውቁም። ላም እረኛ ምን አለ ጉዳያቸው አይደለም። ግን አልበረከቱም። አብሶ አቅምን ማኔጅ በማድረግ አልቦሽ ናቸው።
"ኹሉም ነገር የቀናት ጉዳይ ነው። የትኛውም የሴራ ፈትል የትኛውም የተንኮል ጉንጉን መበጣጠሱ አይቀርም!!!ምክንያቱም ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው።"
ተዋሕዶ ❤❤❤❤
ዬሆነ ሆኖ
"ዬሚጠላ ሰው ሲያልፍ ብትጠላው ጥቁር አትለብስም ግን ነጭ ለብሰህ አትታይም። "
ይገርማል። ዘመን የማይተካው ጋዜጠኛ ጋሼ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት በ2015 እኤአ ስናጣው ስለ እሱ በተሰራ ልዩ ዝግጅት በነጭ ሸሚዝ ያዬሁት አውራ ጋዜጠኛ ነበር። የአውራ ፓርቲ ልሳን። ብፁዑ ወቅዱስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ አባታችን ፃድቁ አቡነ መርቀርዮስ በሥጋ ሲለዩን እፎይ ያሉ የሚዲያ ሰወች ሙሽራ ይመስሉ ነበር። ነጭ ለብሰው ነበር ተግባራቸውን የከወኑት፤ ሌላም ሚዲያ ቆራጣ የዕንባ ጠብታ አልነበረም። ሠርግ የተጠራ ይመስል ነበር። ዛሬ እና ሰሞኑን ሁሎቹም ጥቁር ለብሰው አስተዋልኩኝ። ጵጵስና እኮ ሰማዕትነት የቤተ ክርስትያንም ጉልላት ነበር።
በውይይቱ ላይ በቤተ መንግሥቱ እና በቅዱስ ሲኖደስ የተደረጉ ውይይቶችን አስመልክቶ ሊሆኑ ይገባቸው ነበር ያለውን፤ ወደፊትም ይሁኑ ብሎ ዬተደራጀ የኃሳብ ፏፏቴ በብስለት አቅርቧል። ፀጋው፤ ማስተዋሉ ይመስጣል። ያስደምማል። አሳዳጊው ብሩክ ህሊናውም የለማ። የእኔ ቢሆን ብላችሁ የምትመኙት፤ የምትሳስለትም ሊቀ ትጉኃን። ተባረክ ዬእኔ አባት።
የመሰናዶው አዘጋጅ ልጅ ተክሌን ምሰሉን ይላል። ታድሜ ፍሬ ዝቄያለሁኝ። ተመስገንም ብያለሁኝ። አዳምጬ አልጠግበውም።የሰጣቸው አቅጣጫዋችን ቅድስታችንም፤ አማንያኑም ተጠቀሙበት።
ቅ/ሲኖዶስ ሰልፉን ያራዘመበት ምስጢር | በአባቶች አንድነት የመጣው ለውጥ | "ኦርቶዶክስን የካዱ ሚዲያዎች"
ብቻውን ሰማዕታትን ያሰበበትን ጊዜም ሊንክ እለጥፋለሁኝ። ውስጡን ታዩት ዘንድ።
"የምድራችን ዕውነት ይህ ነው" ከጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13/02/2023
ማስተዋልን የሰጠን አምላክ ይመስገን።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።