ከፀሐፊ አቶ አሳዬ ደርቤ ያገኜሁት ነው።
"ለኦርቶዶክስ ልጆች የተዘጋጀውና አዋሽ አርባ አካባቢ የሚገኘው ምድራዊ ሲዖል!..
እነ ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ክልል የታፈሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የታሠሩት አዋሽ አርባ የማጎሪያ ጣቢያ መሆኑን ስሰማ የሚከተለውን ታሪክ ላጋራችሁ ወደድኩ።
አባ ሳሙዔል እስር ቤት ሳለሁ በአዋሽ አርባ የማጎሪያ ጣቢያ ታስረው የከረሙ ከአምስት መቶ በላይ ዜጎችን አግኝቼ ነበር። እኒህንም ዜጎች "ስለ አዋሽ አርባ አውሩኝ እስኪ" ስላቸው ቶርች የተደረገ ሰውነታቸውን እያሻሹ እንዲህ የሚል ተመሳሳይ ማብራሪያ ነበር የሚነግሩኝ።
" አዋሽ አርባ የማጎሪያ ጣቢያ ማለት
➔የማታውቀውንና ያልሰራኸውን ወንጀል አጋልጥ" የሚሉ መለዮ ለባሾች ማዕከላዊን የሚያስንቅ አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈጽሙበት፤
➔እንደ ኢሰመኮ እና ኢሰመጎ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከእነ መኖሩም የማያውቁት፤
➔ቤተሰብ ቀርቶ ሲቪል የለበሰ ሰው የማይታይበት፤
➔ፍርድ ቤት ሳትቀርብ ከሶስት ወር በላይ ታስረህ የምትቆይበት፤
➔በ24 ሰዓት ውስጥ አንድ ዳቦና አንድ ኩባያ ውሃ ብቻ በሬሽን መልክ የምታገኝበት፤
➔የመጸዳጃ ቤት ጥያቄ ስታቀርብ "ፌስታል ላይ ተጠቀም" የሚል መልስ የምታገኝበት፤
➔ከጸሎት ውጭ ምንም አይነት የሕክምና አገልግሎት የሌለበት፤
እናም እልኻለሁ....
ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ አካባቢ የታፈሱ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የሚጓጓዙት ወደዚያ ምድራዊ ሲዖል ነውና ይሄንን መረጃ ሼር በማድረግ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲደርሱላቸው እናድርግ።"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ