ዘመነ - የመቃብር ሥፍራ፤


እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡ።
ዘመነ - የመቃብር ሥፍራ፤
እዬሞትክ ጠብቀኝ/ ጠብቂኝ
የአብይዝም 50በ60 ያረጠ ፖለቲካ።

„እኛ ከጨለማ የተነሳ በሥርዓት መናገር
 አንችልምና፤ የምንለውን አስታውቁን።“
(መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 37 ቁጥር 19)

ሥርጉተ©ሥላሴ
Seregute©Selassie
24.01.2020
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ

መኖርን የነጠቀው የመቃብር ሥፍራ ዘመን ይሁነኝ ተብሎ በቀኝ በግራ ገመናው እንዳይጋለጥ እንክብካቤ እዬተደረገለት ነው። አራስ ቤት ወይንስ ጫጉላ ጊዜ እንበለው ይሆን? በቀዳዳው ሁሉ እንደፍናለን ብለው ተደማሪ ነፍሶች ታከቱ።

ብዕሩም ብራናውም፤ ማይኩም መድረኩም „ተስፋ አለን“ እያሉ እልልታውን ያስከንዱታል። ፍልሰፍናውንም ቅብጥ እና ቅልጥ ያደርጉታል። አላዛሯ ኢትዮጵያ ሠርግ ላይ ወይንም ቅልቅል ላይ ወይንም መልስ ላይ ወይንም ግጥግጥ ላይ ያለች ይመስላቸዋል። ከንቱነት!

ግን ህሊና እግር ወይንስ እግር ህሊና ቦታ ተለዋውጡ ይሆን? የእኔ እህት ብትሆን? የእኔ ወንድም ቢሆን? የእኔ ልጅ ብትሆን? የእኔ ልጅ ቢሆን ተብሎ እንዴት አይታሰብም? እንደ እኔ ይህ ሰሞን አኮ ብሄራዊ የሃዘን ቀን ሆኖ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ የሚወለበለብበት ጊዜ ነበር። ሌሎችም የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መኖር ነበረበት ይላሉ። እነዛ ቀንበጥ እና ሸባላ ልጆቻችን የት እንደ ደረሱ? ምንስ እንደሆኑ እኛ እማናውቀው ነገር የለም።

ምን እንደሆኑ ቤተሰብ የሚያውቀው ነገር የለም። ምን ሁኔታ እንደ ተፈጠረ ወላጆች አያውቁም። ወላጆች ልጆቻቸውን ማጣታቸው አልበቃ ብለው ህሊናቸው ደግሞ ይቀጣል፤ ይቀጠቀጣል። አማራነት ግማድ ነው!

ዘመዶች ሆኑ እንደ ትውፊታችን ጎረቤቶች፤ ህሊና ያላቸው መምህራን ጭንቅ ላይ ናቸው። አላዛሯም ኢትዮጵያ አፍ አውጥታ አትናገረው እንጂ ለቅሶ ላይ ናት። ይህ ዲስኩር ስንቁ ለሆነ ነፍስ፤ ወይንም ጭካኔን እዬቀባባ በማቆላመጥ ላይ ላለ ዘመናይ ብዕር ምኑም አይደለም።

ምን አለ የማያገባቸው ከሆነ፤ የማይመለከታቸውም ከሆነ ድምፃቸውን አጥፍተው ዝም ቢሉ? ቃሬዛ ላይ ላለ ብአዴን እነሱ ጥብቅና ቁመው ቀለሙም አያልቅም ሲለቀልቁ ውለው ከሚያድሩ። መጥኔ!

የቅልጣን ፖለቲካ አራማጆች ማይኩንም ብራናውም ተመቼን ብለው ቅብጥ እና ቅልጥ ይሉበታል። ለእነሱ ስለ ዘነበላቸው የሌላው ስቃይ ስቃያቸው አይደለም። „በሰው ቁስል እንጨት ቢሰዱበት“ ዓይነት።

ለእነሱ እንክብካቤውም ዝቀሽ ነው። እገዳ የለም፤ ጫና የለም፤ ዲስክርምኔሽን የለም በሰፊው በተንጣለለው ሜዳ እና ብራና ዝንጥ ያለውን ቅብጠታቸውን ለቀቅ ያደርጉልናል።
አሁን ደግሞ የይቱቡ ሚዲያዎች አሉ ቀብ አድርገው በድምጽ አስውበው ያቆላምጡላቸዋል። 

እንደዚህ ዘመን ዕንባ ላይ ተሁኖ ድልቂያ አይቼ አላውቅም። የጸጸቱ ቋያ ነገ ተነገ ወዲያ ከተቻለ። እረመጥ ላይ ትውልድ ይቀቀላል እነሱ ደግሞ በቅልጣን ፈሰስ ይላሉ። ለአንድ የዩንቨርስቲ መምህር ይህ መከራ ቅርብ ያልሆነ ለማን ቅርቡ ሊሆን ይሆን?! አብረን እናምጥ!

እኔ ነፍሱን ይማረውና አባቴ መምህር ነበር። ታላቅ እህቴም መምህርት ናት። የእነሱን ወርሼ ነው ትውልዱ አጀንዳዬ የሆነው። ተጽዕኖ አሳደሩብኝ። ለመምህራን ይህ የመቃብር ሥፍራ ዘመን ምቹ እንዴት ሊሆንላቸው ቻለ ይሆን? የዕውቀት ወራሽ ልጆቻቸው እኮ መከራ ላይ ናቸው ያሉት?

ለመሆኑ በዬትኛውም ደረጃ ለሚያስተምር መምህራን ከትውልዱ ሌላ ምን የመኖር ጣዕም አለው?! ልጆቻቸው እኮ ናቸው በታፈነ፤ በታመቀ ስቃይ ጉድጓድ ውስጥ ላይ ያሉት።
ከ30 ሺህ በላይ የዩንቨርስቲ ተማሪ በዘር ሐረጉ ብቻ ተነጥሎ ከተስፋው ሲፈናቀል አጀንዳቸው አይደለም። ባለጊዜን ሲያወድሱ እና ሲቀድሱ ይስተዋላሉ። ወይንም ሽፋን መከዳ ሲጠልፉ። ዘመነ - ቅርፊት።

እነዚያ ምንዱባን አገር ቢኖራቸው የትውልድ ነበር አመክንዮው። ነገር ግን ቀለም መለቅለቅ እንደ ልጆች ጨዋታ ደስታ የሚሰጠው ፍንክንክ፤ ፍልቅልቅ የሚያደርገው መንግሥት ነው ያለው። ጉዳዩ የህሊና ጉዳይ ነበር። አንድ አገር መንግሥት ካለው ከትውልዱ ሌላ ምን አጀንዳ ሊኖረው ይችል ነበር? 

ለጸሐፍትስ፤ ለሚዲያ ሰዎችስ፤ ለተናጋሪ ሰዎች፤ ለጥበብ ሰዎች፤ ለሃይማኖት አባቶችስ፤ ለመምህራንስ፤ ስለ ሰባአዊ መብት ግድ ይለናል ለሚሉትስ፤ ከትውልድ በላይ ምን አጀንዳ ሊኖራቸው ይሆን? ያልታደለች አገር። ያልታደለም ትውልድ።

ለአንድ ሰው የሰብዕና ግንባታ ሲባል ብቻ ሁሉም አፉን ሸብቦ ሌላውን በማዘናጊያ መጣጥፍ እና በአድርባይ ንግግር ልብ ያወልቃል። ወይንም በፍልስፍና ዲስኩር ፍዳችን ያስከፍላል። ዘመናይነት። ለቅሶ ላይ ላለ // ዋይታ ላይ ላለች አንዲት ፍደኛ አገር ዘመናይነት መታደል ይሆን? አይገባኝም። እንዲገባኝም አልፈቅድም።  

ዘመናይነታቸውን ጨርሰን እንድናዳመጠው ወይንም ጨርሰን እንድናነበው ግን ውስጣችን ያለው የታመቀ ሃዘን አሻም ይላል። ይህን ዘመናይነታቸውን ወይ ቁርጣችን አውቀን ዕንባችን ስናፈስ ወይ ደግሞ መንግሥትም ሀገርም የለንም ብለን ስንደመደም ብቻ ይሆናል ትዕግስቱ ኑሮን ዘመናይነታቸውን አጀንዳችን ልናደርገው የምንችለው? አሁን ግን ቢተውን።

እነ ቁንጮ የሉም ስንል አለን አዳራሽ ስናድስ፤ ሥራ በዝቶብን ነው እንሰማለን፤ አሉ ስንል ደግሞ የሰው ልጅ ከዶሮም አንሶ እንደ ወጣ ሲቀር ከመጤፍ አይቆጥሩትም። ሲያስፈልግ በጅምላ ይረሸናል፤ ሲያስፈልግ በወል ይታገታል፤ ሲያስፈልግ በጋርዮሽ ይደፈራል፤ ሲያስፈልግ ተገድሎ ይቃጠላል፤ ሲያሰኝ ተገድሎ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ ግፍ ይሰራል። 

ይህ ለእነ ማህበረ ዘመናይ ሰርጋ እና መልስ የሙሽርነት ሚዜነት ማሳዬ ነው። የሰውም ግፍ አለው። ዛሬ ሌላም ዜና አለ። ሁለት ነጋዴ ወንድማማቾችም እንደላፉ እዬተደመጠ ነው። „የአማራ እናት ዛሬም ከወደ ቴፒ ሌላ ተጨማሪ ሰቆቃ ገጠማት። እነኚህ ሁለት ወንድማማቾች አማራ በመሆናቸው ብቻ በኦሮሞ ፅንፈኞች በአሰቃቂ ሁኔታ ታርደው ተገለዋል። „The Deq Informer
1.አንተነህ እንየው
2.
ጌታቸው
እንየው“


ያው ኢ- ሰባአዊነት ፉክክር ነው። ታቅዶም ነው የሚከወነው። ኦሮምያ ላይ አንድ አዲስ ክስተት ካለ አማራ ላይ አቻው እንዲፈጸም ያደርጋል ሲኦሉ መንፈስ። ከትናት በስትያ በአርማጭሆ ሶስት ተጨማሪ ልጆች በድጋሚ መታገታቸውን ኢትዮ 360 ዘገባ አዳማጫለሁኝ።

ከዚህ በተጨማሪ ሁለት ወሩን ሊደፍን ያለው የደንቢ ደሎ የበቀል ማወራረጃ ልጆች ጉዳይ የውሽማ ሞት ሆኖ ታሽጓል። ይህ ድምጽ እንዳይሆን ነው የምርኮኛ የብራናውም የማይኩም ሸር ጉድ ዳሰኛነትም። ለግርባው ብአዴን ሌላ የሙሽርነት ሎ የሚሰናዳለት ይህ ሁሉ ዕንባ ሞልቶ እዬፈሰሰ ባለበት ወቅት ነው። ልሽቀት። 

እጅግ በጣም ብዙ አማራ ነክ ድርጅቶች አገር ውስጥም ውጭ አገርም አሉ። አንዳቸውም ጠንካራ ሥራ ሲሰሩ አይታዩም። ደመመን የተጫነው ነገር። አንድም የውጭ የሰባአዊ መብት ተቋማት ሲያወግዙ አይደመጡም። አልደረሰም አይሉም መረጃው አላቸው። በዬቦታው ያለውን ቀዳዳ ሁሉ የሚደፍን ሳተና አፋኝ መንፈስ አለ አራት ኪሎ ላይ። ይህን ጥሶ ለመውጣት አቅም የለም። ዕንባ ለማዋጣት እንኳን አልተቻለም።

ይህን የመቃብር ሥፍራ ዘመን እንዲህ ልብስን፤ ጸጉርን፤ እያስተካከሉ ብቻ የምንወጣው ከሆነ ይታያል። „ተረኝነት፤ ፈረቃ፤ ካለፈው የቀጠለ ወይንም ከህዋህት ጋር ተመሳሳይ“  የሚለው ዱካ አመክንዮ ያልበሰለ የፖለቲካ ግንዛቤ ነው እኔ እማዳምጠው። መነሻውም መድረሻው የግቡ አልተደረሰበትም። በአዝለኝ ወይንም በአቃላይ ፖለቲካ አቅም ይባክናል።

ለዚህ ደግሞ የአብይዝም ምልምሎች ቀን ከሌት ያደነቁሩናል። ሞጋች አቅም ሲወጣ ባለ ብዕር፤ ባለ ማይክ ይሰለፍ እና ግርዶሽ ይሰራል። አቅማችን ምን ሆነ ሲባል ለረጅም ጊዜ ውሃ ሲሄድበት የባጀ ኬሻ ምስጋን ይንሳው። አነሳዋለሁ ብትሉት ከእጃችሁ ላይ ይረግፋል። እንደዛ ነው ብትክት ያልነው። ውርዴትም - ውርዴም።

አብይዝም የሚለው እዬሞትክ ጠብቀኝ // እዬሞትሽ ጠብቂኝ ነው። እኔ ተልዕኮዬን እስከ አጠናቅቅ የህሊና ነቀላ እና ተከላውን ኦፕራሲዎኑን እስክጨረስ እዬሞትክ ጠብቀኝ// እዬሞትሽ ጠብቂኝ ይልሃል/ ይልሻል። ሌላው ደግሞ የእግር ሚዜ ሆኖ የላዩን ታች፤ የታቹን ላይ ያመሰቃቅል እና መንፈስን እያወከ፤ እዬበተነ ማህል መንገድ ላይ ይገትርል።

በማሃል ባለቤት የሌላቸው ነፍሶች አሳራቸውን ያያሉ። በተለይም የአማራ ህዝብ እና የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች። የትውልዱም መንፈስ እንደ ለመደበት ይባክናል። ሌላው ደግሞ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለተፅዕኖ ፈጣሪ ፎቶውን ለጥፎ ትዕይንት ያሳይኃል። የአዚሙ ዓይነት ቡፌ ነው።

·       ክወና

በመጨረሻ አንድ ነገር ልበል እና የወግ ገበታዬን ልከውን። የትናንት የኢትዮ 360 ዝግጅት ልብ ይነካ ነበር። ዛሬ ነው ያዳመጥኩት ትናንት ባለመቻል አላደመጥኩትም ነበር። በተለይ የእናት ጋዜጠኛ ወ/ሮ እዬሩሳሌም ተ/ ጻድቅ ውስጧን ማዬት ቻልኩኝ። እግዚአብሄርንም አመሰገንኩኝ። ፕሮግራም እዬመራች ዕንባውን መቆጣጠር አልቻለችም ነበር። አብነት ነው።

ሴቶች አንድ ቦታ ሲመደቡ ድርብ ኃላፊነት ይዘው መሆኑን አመሳጥራልናለች። ያጣነውን ዕድል አብሥራልናለች። ድርጅቷም ዕድለኛ ነው። በጠቅላላ ዝግጅቱ ብሄራዊ ኃላፊነት የተሰማው ነበር።

በሌላ በኩል ዛሬ የአባይ ሚዲያ ሦስት ጋዜጠኞች ፊት-ለፈት ወጥተው የድምጽ አልባዎችን ድምጽ ሆነው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አይቻለሁኝ። ስለሆነም ለሁለቱ ሚዲያ ባልደረባዎች ያለኝን የተስፋ አክብሮት እገልጻለሁኝ።

ትህትናዊ ምስጋና ላደርግላቸው እፈልጋለሁኝ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። የእኔ ድንግል ትጠብቃችሁ። አሜን። „የሚያዝኑ ብጹዕን ናቸው፤ ያዘኑትንም የሚያጽናኑም ብጹዕን ናቸው“   

 ልዑል እግዚአብሄር በቃችሁ ይበለን! ቸር ወሬም ያሰማን። አሜን። 
ህይታቸው ላለፈው ወንድሞቻችን ነፍሳቸውን በገነት ያኑር ፈጣሪ።
ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናት ይስጥልን አምላካችን። አሜን።  

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።