#ክስተቱ ዓለም ዓቀፍ ንቅናቄ ቢፈጥር ተቋሙ ይጎዳል።
• የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቅስም ሰባሪው የአካል እክል የገጠማቸው የአገር ልጆች።
#ክስተቱ ዓለም ዓቀፍ ንቅናቄ ቢፈጥር ተቋሙ ይጎዳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል። ሰውነትን ሰርዟልና።
"ኃጢያትን የሚከድን ሰው ፍቅርን ይሻል፤ ነገርን
የሚደጋግም ግን የተማመኑትን ወዳጆችን ይለያያል"
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱)
#ምዕራፍ ፳።
#ከፋኝ። እጅግ ከፋኝ።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ስጽፍ የመጀመሪዬ ነው። የምሳሳለት፤ የምናፍቀው ተቋም ነው። ዛሬ ግን ያዳመጥኩት #ኮሶ ነበር። #አሳንጋላ ነው። ይህን ጹሑፍ ለመፃፍ የተገደድኩበት ሁኔታ #ሰብዕዊነት በኢትዮጵያ #በየነጥብ ጣቢያው ምን ያህል ቀራኒወ ላይ እንዳለ ስለአዳመጥኩ ነው።
ለዛውም አንድ የቀረን የጋራ ቤታችን፤ የወል የመንፈስ ማረፊያችን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ #ዜጋ ላይ የክት እና የዘወትር፤ የውስጥ እና የእዳሪ ልጅ፤ አንዱ በፍቅር ተከብሮ ሲስተናገድ ሌላው ደግሞ ይህን መሰል የተሰወረ #ጫና፤ ዲስክርምኔሽን ሲፈጸምበት ማድመጥ እጅግ ፈታኙ ገጠመኝ ነው - ለእኔ። ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ያለው፤ በአፍሪካ ተመራጩ የእኛ የምለው ቤታችን በዚህ ልክ #አግላይነት መራራ ገጠመኝ ነው።
በአካሉ እክል ላለበት እኮ የቅድሚያ ቅድሚ ሊሰጥ ሲገባ፤ እግርህን #ጥለህ ግባ ምን ዓይነት ጭካኔ፤ ምን ዓይነት #አረመኔነት እንደሆን አላውቅም። ለዛውም በሴት አስተናጋጅ። ርህርህርህና #ተፍቆ ጭካኔ እንዲህ አና ሲል ማየት እጅግ አሰቃቂ ገጠመኝ ነው።
ክስተቱ ዓለም ዓቀፍ #ንቅናቄ ሊያስነሳ ይችላል። ዓለም ዓቀፍ የሰብዕዊ መብት አስከባሪ አካላት ቢያዳምጡት ይህን #ገመና ከገብያ ውጭ የሚያደርጉ ሳንኮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካል ጉዳተኞችን የሚከታተል መዋቅር አለ።
አንድ ተቋም ተቋሙን ሲያደራጅ፤ ሲመራ ለዚህ መሰል የታወቀ ችግር #መርኃዊ መመሪያ ሊኖረው ይገባል። በጀርመን አንድ ሚ/ር ነበሩ በክራንች የሚሄዱ። ክቡርነታቸው እንግዳ ቢሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አላሳፍርም ሊል ነውን????
የዓይን ጉዳት የደረሰበት ወገን #መንጸርህን ትተህ ግባ ሊባል ይችላልን? ከዚህ አንፃር እነሱ ለቆሙበት መሬት አካላቸውን በጦርነት ያጡ ወገኖቻችን አየር መንገዱ የማስተናገድ አቅሙ እንዲህ ልፍስፍስ ነውን? የሰውን ልጅ ከላይ እስከታች #ተርትሮ - ገምሶም የማየት ጭካኔ። መሃከነ።
ከሆነው ነገር በላይ አንተ አልገባህም፤ ዕወቀው የሚል አሰቃቂ፤ #ቅስም ሰባሪ ድርጊት ለዛውም በገናናው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲህ በተደጋጋሚ ሲከሰት #ባሊህ ማለት አለመቻል መርኽ አልቦሽ ጉዞ አናርኪዝም ነው።
አናርኪዝም ደግሞ ከማፍረስ፤ ከመናድ፤ ከመበተን ውጪ ሌላ ተልዕኮ የለውም። የኢትዮጵያ ህዝብ በኑሮ አቅሙ በአውቶብስ መጓጓዝ አይችልም። ድፍን 8 ዓመታት ደፍሮ በአውቶብስ የሚሄድ ይታገታል፤ ይሰወራል፤ #ሰማዕትነት ይቀበላል። ስለሆነም ብዙ ሰው ከማይቀርበት ጉዳይ ሊገኝ አይችልም። ተለያይቷል ወገን ተወገኑ።
በአውሮፕላን ለመሄድ አቅም ያለው ብቻ ነው መጓጓዝ የሚችለው። ይህም ሆኑ በዚህ ልክ አካል እክል የገጠማቸው ወገኖቻችን ተለይተው ተደጋጋሚ በደል ሲደር ከማየት በላይ መራራ ጉዳይ የለም። አሳዛኝ ክስተት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ይቅርታ ለተጎጂው ብቻ ሳይሆን በመላ ዓለም ላይ ላሉ የአካል ጉዳተኞች ሁሉ ሊጠይቅ ይገባል። ሰውነትን #ሰርዟል እና።
በቀል ይሁን ቂም፤ ጥላቻ ይሁን ጭካኔ የላይኛው ይፈትሸው። በደርግ ጊዜ እኮ የጀግኖች አንባ ነበር። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የአካል ጉዳተኞች አትሌቲክስ አለ። ይህን ሁሉ ግሎባል ሰባዕዊነት የጣሰ ተግባር ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፈጸመው።
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ባለቤት የላቸውም። ፌስቡክ እንደ ጀመርኩኝ ባለቤት የሌላቸው ማንነቶች እሠራበት ነበር። ቁራሽ እንጀራ የሚል የተግባር አቅጣጫ ነበረኝ።
//// የእግረኛው ነገር።
እርግጥ ነው እግረኛው ሚዲያ የማይነኩ ጉዳዮችን ይነካካል። ይደፍራል። ይህ ደግሞ ብዙ ፈተና አዝሎ ይመጣል። የግንባር ስጋነት ለህሊና ማደር ቢሆንም "ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም።" የድንግሉ፤ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ዶግማ ገንዘብ ማድረግ ይገባል። ይህ የግል ዕይታዬ ነው።
#ደስ ያለኝ ነገር።
በስንት ዘመኔ እንዲህ የናፈቀኝን ቃና --- ለዛ --- ወግ --- ገራገርነት ------:የእናታዊነት ተፈጥሯዊ ሚስጢር አየሁ። አዳመጥኩኝ። የጎንደር እናቶችን በአንድም በሌላም ጎድተናቸዋል። ድምፃችን ነፍገናቸዋል። ዓይናችን ---- መንፈሳችን ---- ሁለመናችን ----- #ውል እንዳላቸው መራራ ስንብት ይሆናል። እንዳዘኑ ----- እንደተከዙ።
በዚህ ውስጥ እኔም አለሁኝ። በዚህ ታሪክ ውስጥ እሙኃይቱ እናቴም አለች። እንግልትት --- እንዳደረኳት በናፍቆት ቀጥቼ፤ እኔም ተቀጥቼ ተለያዬን። የማይለመድ። የማይቻል ግን ሆነ።
ቢዘገይም እግረኛው ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ከእናቱ ጋር ጎንደር ድረስ ሄዶ ተገናኙ። የውስጥ የሆነ፤ ተፈጥሯዊ የሆነ፤ ቅናዊ የሆነ #ትዕይንት ነበር። በመሃል የአየር መንገዱ መከራ መጣ እና ውስጤ የተሰማኝን ደስታ ቀማኝ። ከፋፍሎ ቢያቀርበው ጥሩ ነበር። ኃሞት እና ማር ሲቀየጥ መራራው አመዘነ እና እጅግ ከፋኝ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰብዓዊነትን ልክ #በመድፍጠጡ ከፍቶኛል።
ሲቃ ነበረኝ። በመገናኜታቸው ውብ ተፈጥሮን አየሁኝ። ፈጣሪ አምላክ ይህን ጊዜ ፈጥሮ ዓይን ለዓይን መገናኜት ከመታደል በላይ ነው። የእግረኛው ሚዲያ አዘጋጅ እና ባለቤት ጊዜዋን መሻማት ይገባዋል። ክብርት እናቱ አልጠገቡትም። ስለዚህ ወደ እሱ ወስዶ ሊክሳቸው ይገባል። ድምፃቸውን ሳይሰማም መተኛት አይኖርበት።
እግዚአብሄር ለእሱ ያደረገው ታላቅ ነገር ነው። ክሶታል። እናቱን በአካል በህይወት እያሉ አግኝቷል። ለሳቸውም ሲልም መጠራቅቅ ከበዛባቸው ጉዳዮች ትንሽ እራሱን ቢዘገይ ጥሩ ይሆናል። እህታዊ ዕይታዬ ነው።
እንዴት ሰነበታችሁልኝ ክብረቶቼ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
አሜን።
ልስልስ ያለ ሰላማዊ ሌሊት እመኛለሁ ለሁላችን። ደህና እደሩልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
14/10/2026.
ክብር ለሰው ልጆች ሁሉ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ