ስለምን ይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ #አጽናኝነትን እንደ ጦር የሚፈራው?
ስለምን ይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ #አጽናኝነትን እንደ ጦር የሚፈራው?
ለምንስ ይሆን #አይዟችሁ #ባይነት እንደ ወንጀል የሚታዬው?
በኢትዮጵያ ፖለቲካ #ሰዋዊነት #አደጋ ውስጥ ነው።
ይህ አካሄድ ጨካኞች፦ በጭካኔያቸው ጀግንነት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው።
የኢትዮጵያ ፖለቲካም ለጨካኞች ሽፋን ስለሰጠ የፖለቲካው አውራ መሪ እኔ ነኝ፤ ሥራም ሠርቻለሁ ይላል።
ፖለቲካ ሠሪው #ሰው ነው። ፖለቲካ የሚሠራውም #ለሰው እና #ለተፈጥሮ ነው።
ስለሆነም #ሰውኛነት ቢያስመሰግን፤ ቢያስከብር እንጂ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህግ #መሳደጂያ ሊሆን አይገባም።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሰውኛ ማዕቀፍ ውስጥ #ያፈነገጠ ነው።
ይህን ማረቅ እና ማሰተካከል ይገባል። #ሃግ ሊባል ይገባል። የኢትዮጵያ ህዝብ በተፈጥሮው አዛኝ፤ ሩህሩህ፤ ደግ እና አጽናኝ ነው።
ሃዘኑን በወል በህብራዊነት አስከብሮ የኖረ ህዝብ ነው።
ይህን #ጸጋውን #የሚገፍ #አሳቻ ዘመን ላይ ነውና በጥሞና የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያስብበት ይገባል። ገዢወቹንም ሊያርማቸው፤ ሊገስፃቸው፤ ሊቆጣቸው ይገባል።
ሥርጉትሻ2025/03/26
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ