#ነሽ #ሕይወት
ትብትቡ ጉዞ ይቃኝ ---- አለኝ።
ለሥምየለሽ ባላንጣሽ
ለአስመንጥሩ----- ጉደኛሽ
በጥቂቱ ---- በጨረፍታ
ለአንድአፍታ አወን!---- ለአንድአፍታ
በሙግት ትብትቡ ---------ይፍታታ ----
ስለወለላዋ --- ስለታታታ።
እንዲህ ልበል ለአያ እንቶኔ
#የምስጥ ጉዞ ምናኔ።
አድሪ ለእንቺ መከራ በእጥፍ ድርቡ #አድሪ
የተስፋሽ #እምል ቀባሪ።
አንችም ዝም ------
እስከመቼ ---- እኔም ዝም
እም!----- #ም ----- እምም።
መኖርሽ ሲመዘመዝ ~~~~ የምን ዝም???
ለአማራ እናት --- እባክህን በአማኑኤል ፋታ #ስጣት።
ሰርክ ለቋያ -----አትማግዳት
የፋንታዚህ መወራረጃ አታድርጋት።
ልቀቃት! -------== እባክህን???? ---- ልቀቃት!
የሰርክ የድርጅትህ ማገዶ አታድርጋት።
በስል ገብተህ ቅርጥም አድርገህ በላኽው --- ሩብ ዘመናችን
ተከዳ በእጅጉ መታመናችን።
እኮ! አያ እንቶኔ ----
የማከብርህ ወገኔ -----
የእኛን አቅም የመጠጥከው ይበቃል፦
በቃኝ! በቃኝ! የፋንታዚህ --- #ብልቃጥ፦
#አይጸጽትህ ~~~~አይወግርህ~~~~ አይፈልጥህ~~~~~
ያ_____ ሁሉ የደም ጎርፍ፦ ያማጡ ድቅድቅ፦ ዕለታት፦ የዋይታ #መኽርኽ።
ከእህህ ጋር የተጣቡ እነኛ የበላለዙ~~~~ ወራት
ከእምታ ጋር የደቀቁ ጠራጠሮ ~~~~ዓውዳ- ዓመታት
ክልትምትም ያሉ ማዲያት´ማ ----ሰዓታት
የጠቋቆሩ የጭንቅ ሳምንታት
በአንተ ምክንያት የተነጠቁ የሚሊዮን #ሳቃት
ልብ አልሰጡህ፤ አልመከሩህ፦ አልገሰፁህ የዕንባ #ንቅሳት፦
መከራዋን አበራክተህ በምፃት --- ገጀሞ አስገረፍካት፦
አሳደንካት ፦፦፦፦፦
አስነቀልካት፤
አስፈለስካት።
ለአሳር ዓይነት አስማገድካት
ተዋት! እሷን እባክህ?----- ተዋት!
ለአማራ እናት አንተ --- ማቅ ነህና ጥቁር ልብስ
ዝልግልግ
ትብስብስስስስስስ-------ስስስስስስስስ……………
ዝርጋዝርግ።
"ህግ ተላሳፊወችን ጠላሁ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19/02/2025
ሰዓት 03.05
ቢንተርቱር ሲዊዘርላንድ።
መታሰቢያነቱ ፈጽሞ ለማይታዘንላት፦ ማህጸኗ ሰርክ ቄራ ለሆነው ለአማራ እናት ይሁንልኝ።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ