#በተስረከረከ እና #በተሳከረ

 #በተስረከረከ እና #በተሳከረ #ዓላማ እና #ግብ ለድል የሚበቃ፤ የበቃም በድል የተቋጬ ተጋድሎ አይኖርም። 

እጅግ በሃዘን ልባችን በሚሰነጥቅ ክስተት ዝምታችን ፍርኃት፤ ወይንም የፖለቲካ ሂደት ብልት ጠፍቶን፤ ወይንም የመሰዋዕትነት አናሳ ሁነት ኑሮብን አይደለም። #ሙግቱም ጠፍቶን አይደለም።

 ማራገፋን ኑረንበታል። ትወናውም ሳይገባን ቀርቶ አይደለም። መደበኛ ሥራችን ከዕንባ ጋር ነውና። በሚያረገርግ ምኞት አነሳሽነት የሚካሄድ ማንኛውም ክስተት ይሁን በዘባጣ ፍላጎት እና ፋክክር፤ ንጹኃንን በቋያ አንገርግቦ ከመማገድ ውጪ የሚያስገኜው ተረፈ ዕሴት የለም!!!!!! ህዝባችን በቅጽበታዊ፤ በተለዋዋጭ እና ባልሰከኑ ምኞቶች፦ አቅምን ባልመጠነ ፈሶ በሚለቅም፤ ተለቅሞ በሚፈስ ቅጥአንባሩ በጠፋ ትርምስ ባታሰቃዩት ትለመናላችሁ። 

አይገርማችሁም ውድ ማህበረ ቅንነት ማኒፌስቶ ወጣ በተባለ ማግሥት የአመራር ለውጥ ተደረገ? የአማራ ሕዝብ የእነሱ የመለማመጃ ዳንቴል?????!!!!! መጥኔ ለቅኑ የአማራ ህዝብ። ይህን ገመና ተሸክሞ ዛሬም ለሚማገደው።

 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/02/2025

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?