#የኮበሌ መንፈስ ያዘነበላቸው ሚዲያወች ቅኝት። ለእኔ - የአንካራው ሥምምነት።

 

#የኮበሌ መንፈስ ያዘነበላቸው ሚዲያወች ቅኝት።
ለእኔ - የአንካራው ሥምምነት።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።
 
"ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት የደረሱበት ሰነድ ምን ይዟል?"
 
ሙሉ 11ወር ያልነካካሁት አጀንዳ ነበር። የኢትዮጵያ እና የሱማሌ ላንድ የመግባቢያ ሰነድ #ግጥግጦሽ። እርግጥ ነው በዚህ ምክንያት የሱማሌ ላንድን ምርጫ ሂደት ከውስጤ ተከታትዬዋለሁኝ። በአንድም በሌላም የእምዬ ጉዳይ ስላለበት። ነባሩ መሪ በተፎካካሪያቸው ተሸንፈዋል። ስለዚህም አዲስ ሁኔታ ይኖራል እራሱ በሱማሌ ላንድ ፖለቲካ። ሱማሌ ላንዶች ጠቅላይ ሚር አብይ በጠረጉላቸው ጎዳና የዓለም ዓቀፍ ሚዲያ ሽፋን በስፋት አግኝተዋል። ስለዚህ + አትርፈዋል። ሰነዱ ሲቀደድ ደግሞ ከስረዋል - ይሆናል። ምን አልባት ዕውቅናውን #ሌላ #አገር ሊደፍረው ይችል ይሆናል። አሁን የሱማሌ ላንድ ህዝብ ግብረ መልሱ ምን ይሆናል ደስታቸውን ስለተነጠቁ??? የሱማሌ ህዝብስ ሲግረጨረጩ ስለባጁ?
 
የኢትዮጵያ ሚዲያወች አብይዝምን የሚደግፋ #ኮበሌ ኮበሌ የሚል ጠረን ያለው ዕርዕስ ሰጥተው እዬዘገቡት ነው። ግርም ብሎኛል። ዕውን ለኢትዮጵያ "ደህንነቱ አስተማማኝ የባህር በር" የአንካራው ስምምነት ያስገኝ ይሆን? ለመሆኑ ሱማሌ የረጋ መንግስታዊ ስርዓት አላትን? አስተማማኝነት ከአንድ አገር የደህንነት አቅም ጋር ስለሚለካካ። አስተማማኝ የመንግሥት ሥርዓት የካርቢያን አገሮች ሲዊዲን፤ ዴንማርክ ኖርወይ፤ ሲዊዘርላንድ ወዘተ ናቸው፤ አውሮፓ እንኳን አሁን በጭንቅም በጦርነትም ላይ ናቸው ነገረ ዩክሬንን ተከትሎ። ፖላንድ፤ ኢስቶንያ፤ ጀርመን ፈረንሳ…… 
 
#ግነቱ የሚተናነቅው ሃቅ ምን ሊል እንደሚችል ባላውቅም፦ 
 
«ደኅንነቱ የተረጋገጠ፣ አስተማማኝ የባሕር በር» EBC …… ኧረ በልክ።
«ሱማሌ በጭንቅ የፈረመችው ስምምነት» Arts TV ማን #አስገድዶቸው?
«በስኬት የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና ሶማሊያ ስምምነት» Fana TV ቅጽበታዊነት፤ እስኪ ነገን ጠብቁ፦ መጣደፋ ስለምን?
«ሱማሊያ እና ኢትዮጵያ ቀይ ባህራችን በእጃችን!» አቤቾ እንኳን "ወደብ ባለቤት" ሆነ እፍታ ዜናው ከእሱ ነበር ባለፈው። 
 
ለእኔ ግን ነጥብ ስሰጠው ያተረፋት ሱማሌ እና ቱርኪ ናቸው። አገሮችን ከፍጥጫ አውጥቶ ወደ ሰላማዊ ንግግር እንዲያዘነብሉ ማድረግ #ብልህነት ነው። ቀጣዩ ደግሞ የስምምነቱ ጭብጥ ይሆናል። መጨረሻው የስምምነቱ ገቢራዊ ዕውነት ይሆናል። ሰላምን የሚያመጣ፤ ስለሰላም አስተዋፆ ያለው እርምጃ ለእኔ ውስጤ ነው።
 
በእኔ ነጥብ አሰጣጥ በዚህ የአንካራ ስምምነት ሙሉለሙሉ ኪሳራ ይኖራል ብዬ አላስብም። ነገር ግን ውል፤ ድርድር፤ ስምምነት #ቃልን #ከመጠበቅ ጋር የተዋህደ ነው። #መታመን#ማመን። ይህን የኢትዮጵያ መንግሥት አሳክቷል ብዬ አላስብም። በአለም አቀፋ የዲፕሎማሲ አቅም እና አቋም እምነት ማጣት የውስጥ ህመም ይመስለኛል። በሌላ በኩል ዕድሜ ዘመናቸውን የሱማሌ ላንድ ህዝብ #ቃል አባይ ነው የኢትዮጵያ መንግስት በማለት እስከ ልጅ ልጆቻቸው የሚያወርሱት የትውፊት ስንቅ ይሆናቸዋል። ይህ ደግሞ ለቀንዱ ትውልድ የወደፊት ትስስር ጥሩ #ምልክት አይመስለኝም። 
 
ከመግባቢያ ሰነዱ ጋርም ሱማሌ የሚኖሩ ወገኖቻቸን ጥቃት እንደተፈፀመባቸው አድምጫለሁኝ። #ተኩረፍርፎ የተሰናበተው የመግባቢያ ሰነዱ ጉዳይ ከፋኖ ንቅናቄ ጋር የመጣ ሂደት ነበር። #የፋኖ #ተጋድሎ #ጎልቶ ሲወጣ ያን ለማርገብ ተብሎ የተከወነ ነው። አባቶቻችን ብልሆች ነበሩ እና "ከህዳር ዝናብ እና ከኮበሌ መሪ ያድናችሁ" ይሉ ነበር።
 
በኢትዮጵያ የሥልጣን ሂደት የምናዬወም አፍላዊ፤ እንደ ሳሙና አረፋ የሚኩረፈረፍ #የጓጎለ ጉዳይ ነው የሚገጥመው። በአባይ ጉዳይ ተነስቶ የነበረውን ወጀብ መልክ ያሳያዙት የዛሬን አያድርገው እና #ኢትዮ 360ወች ነበሩ። ዲያስፖራው ሆነ የአብይዝም መንግስት ዘግይተው ነበር የነቁት። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የውጭ ጉዳይ ሚር ነበሩ። ብዙውን ነገር ሞግተው ቀርፀውታልም ይባላል። 
 
እንጂ ጠቅላይ ሚር አብይ ድፍርስርስ አድርገውት ነበር። በድፍርስርሱ አትራፊነታቸውን የሚያውቁት እሳቸው ናቸው። ድብልቅልቅ ሲል የሚወዱም ይመስለኛል። ድብልቅልቅ የሚነሽጣቸው ይመስለኛል። ፋኖ እውቅናው ሲጎላ ያን ለማደብዘዝ ነው ከዛ ስምምነት ዘው ያሉት። በየትኛውም አገር አልተወደደላቸውም ነበር። ወደብ ለኢትዮጵያ፤ የባህር በር ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል። ነገር ግን ፍላጎትን አስክኖ ዊዝደምን እንዲውጥ ማድረግ ያስፈልግ ነበር። 
 
የሆነ ሆኖ አሁን አንካራ ላይ #በሱማሌ #አሸናፊነት ለጊዜው ጉዳዩ መልክ ለመያዝ አቅጣጫ እያሳዬ ነው። መጨረሻው ምን እንደሚሆን አይታወቅም። ሃዘንንም፤ ደስታንም በልኩ መያዝ ያስፈልጋል።
 
እርግጥ ነው የአብይዝም #የሞራል #ጠባቂ ሚዲያወች፦ ይህን የቃል እጥፋት ወይንም ውልቃት ወጌሻ ለመሆን ጥድፊያ ላይ ናቸው። ላወቀበት ሚዲያ ባለ ብዙ አቅም ነው። አብሮ ማረግረግም፤ አብሮ መውረግረግም ግዴታ አይደለም። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ምን አትረፈች? ምን ከሰረች አጀንዳቸው አይደለም የአብይዝም ፕሮፖጋንዳ #ወጌሻወች
የአብይዝም ሥርዓት አልተመቸንም የሚሉትም የአብይዝም ኪሳራ እና ትርፍ #ለኢትዮጵያ ምን አስገኜ፤ ወይንስ ምን አሳጣ የሚለውን ቅን እና ቀና አወንታዊ ዕይታን ሲያራምዱ የማላያቸው ሚዲያወችም አሉ። 
 
"#ፋኖን ኤርትራ ፈጠረችው" ሲባል የቀዘቀዘ፤ የበረደው ምስል ነበር ያዬሁት። ለዛውም ኤርትራ የአማራን ህዝብ መንፈስ ገርታ ፋኖን ልትፈጥር??? የትናንቷ ኤርትራ የጥንት የጥዋቱን የአባት አደሩን #ዘመን ጠገቡን ፋኖ ፈጣሪ??? ድፍረቱ ይገርመኛል። "ኢትዮጵያ አቅም" የላትም ሲባልም ዝም። ብቻ የእኛ ፍላጎት እና ራዕይ ሁልጊዜ ግራ እንደተጋባ ነው። ነገረ ኢትዮጵያ ከማናችንም በላይ፤ በላይ #ልዕለ ነው። 
 
ኢትዮጵያ በመሪወቿ ብቻ ልትለካ አይገባም። ኢትዮጵያ በፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ብቻ አትለካም። ኢትዮጵያ የራሷ ድንቅ ዕፁብ ድንቅ #ማንነት አላት። ለዛ ጥልቅ እና ምጡቅ ማንነቷ ዘብ አደር መሆን ከእያንዳንዳችን በግል፤ ከሁላችንም በጋራ የሚጠበቅ ድርሻ ነው። ጠቆረችም ከሳችም፤ አጌጠችም ተዋበችም እናት እናት ናት። 
 
እናትን ከማያስከፋ ድርጊት መቆጠብ ይገባል። ብዙ ነገር ነው እኔ እምታዘበው። እናት ሸቀጥ አይደለችም የምትሸጥ የምትለወጥ - በምንም ፈታኝ ሁኔታ እንኳን ቢሆን። ለሌላ አገር ጥብቅና መቆም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊኮሰኩስ ይገባል። እናት ከፍ እና ዝቅ ስትደረግ፤ ታሪክህ ለሌላ ሲሸለም ሊያንቅህ ይገባል። 
 
የሆነ ሆኖ ……… በአንካራው ሰነድ ……… ለለቱ ነገ ምን ይዞ እንደሚመጣ ባይታወቅም።
ቱርክ A+
• ኢትዮጵያ + -
• ሱማሌ A
• ሱማሌ ላንድ - +
«ደኅንነቱ የተረጋገጠ፣ አስተማማኝ የባሕር በር ሰላማዊ በሆነና ጎረቤቶቻችንን ተጠቃሚ በሚያደርግ መንገድ ማግኘት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)»
«ሱማሌ በጭንቅ የፈረመችው ስምምነት»
«የአንካራው ሥምምነት እና የያዛቸው ወሳኝ ጉዳዮች | ትንታኔ ዜና ‪@ArtsTvWorld‬ #indepthanalysis «
Arts Tv World
«በስኬት የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና ሶማሊያ ስምምነት»
Haq ena saq
«ሱማሊያ እና ኢትዮጵያ ቀይ ባህራችን በእጃችን! / ዘመነ እና እስክንድር ሊጋደሉ ነው የጽንፈኝነት መጨረሻ / የነጻነት ትግል ወይስ ዝርፊያ»
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
12/12/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።