ልጥፎች

የአዲሱ ለውጥ ትሩፋት።

ምስል
መንትዮሾቹ የተግባር ልዕልቶች በደግነት      ማዕዶት! „የፃድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ ሙሉቀን እስኪሆን ድረስ እዬተጨመረ ይበራል።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 30.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አዲሱ ለውጡ አደጋ ያመጣል የሚሉት የአባ ቆስቁስ የአቶ በረከትን የኑዛዜ መስቃ እንዲህ መናነቱን ተግባር ቁሞ ይመሰክራል። የአባ ቆስቁስ የአቶ በረከት ስምዖን ሙገት ቁሞቀርም መሆኑ እንዲህ ይታያል። ይህ ተግባር አላዛሯ ኢትዮጵያ የተፈጠረችበትን የደግነትን፤ የቸርነት ትውፊቷን አህዱ ብላ መጀመሯን ያሳያል። ሲጀመር ጀምሮ ለውጡ ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ነው በማለት ነበር ስሞግት የባጀሁት። አዲሱ የኢትዮጵያ መንገድ ይሄውና ዛሬም የበጎ ምግባርን ተግባር ተስፋን ሰንቆልናል ... ይህ ድርጀት መቄዶኒያ በራስ አነሳሽነት ከመንገድ ላይ የወደቁ አቅመ ደካሞችን በራስ ጊዜ፤ ጉልበት እና አቅም የተጀመረ ነው። መስራቹ ቅዱስ ብቻቸውን የጀመሩት ተቋም ዛሬ እንዲህ አፍርቶ ለወግ ለማዕረግ በቅቶ ለዚህ ቀን በቅቷል።  ቤተ መንግሥትም እንዲህ እንሆ ታደመበት። ወይ ጊዜ እንዲህ ትክሳለህ! ሁለት ዳጋጋውያን አንስቶች እራሳቸው ደካሞችን በማስተናገድ የተሰለፉበት ይህ የቸርነት መንገድ አዲሱ የለውጥ መንፈስ እንዲህ ቅንድስና፤ ብጽዕና ያለው መሆኑን ያመላክታል። ይህ የቸርነት ጉዞ ትንሽ ራቅ አድርጌ የዛሬ አምስት ዓመት የት ትደረስ ይሆን ብዬ ስጠይቀው „አይተሽ ፍረጂ ብሎኛል።“ እናንተም አይታችሁ ፍረዱት ልበል በተሰጠኝ መልስ መሰረትነት።  የኔ ውዶች የጹሁፌ ታዳሚዎች ትንሽ ገፋ አድርገሽ ወደ 10 ዓመትስ ስለምን አለወሰድሽውም ትሉኝ ይሆናል። 10 ዓመቱ ረዘመብኝ እና ነው በእኩሌታው

ቢያፍሩ ምን አለ አባ ቆስቁስ?

ምስል
አባ ቆስስቁስ አቤቶ  አቶ በረከት ስምዖን  ሥልጣናዊ ቅርፊት  ፍርክርክ ብትክትክ። „ምናምንቴ ሰው የበደለኛም ልጅ በጠማማ አፍ ይሄዳል፤ በዓይኑ ይጠቅሳል፤ በእግሩ ይናገራል፤ በጣቱ ያስተምራል፤ ጠማማነት ብልቡ አለ፤ ሁልጊዜም ክፋትን ያስባል፤ ጠብንም ይዘራል።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፮ ከቁጥር ፲፪ እስከ ፲፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ  30.08.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የሳጅን በረከት ሥጦታ - ለአማራ።   ·        ኑ ዛዜ። ቀድመው የተናዘዙት አቦይ ስብሃት ነጋ ነበሩ። የሰሞናቱ  የኑዛዜ ሁለተኛው ነው ። ባለ ኑዛዜው አቶ በረከት ስምዖን እና ማህበረ ኔትወርካቸው ነው። በጣም የሚያስደስተው እና ተስፋ የሚሰጠው ደግሞ አቶ በረከት ስምዖን በብአዴን ላይ ስሞታ አቅራቢ ሆነው መገኘታቸው ነው። ብትክትክ አሉ። አሁን ነው እኔ እርግጥም ብአዴን ራሱን ችሎ መቆም መጀመሩን የተደስትኩበት። ብራቦ! ብአዴን ብለናል ተዚህ ተኮሽ አይሏ ሲዊዚሻ። በሌላ በኩልም አባ ቆስቁስቁስ አቶ በረከት ስምዖን በአቶ ደመቀ መኮነን ያቀረቡት ክስም ቢሆን አቶ ደመቀ መኮነን ጥሩ ሰው መሆናቸውን ማወቅ አስችሎለኛል። ምክንያቱም አቶ በረከት ስምዖን የሚጠሉት ወይንም የሚያገሉት ወይንም የሚያሳድሙበት፤ ወይንም የሚያሳድዱት ሰው ጥሩ እና ቀና ሰውን ብቻ ነው። የሚበልጣቸውን ወይንም ሴራቸውን የሚያጋልጣቸውን።  ስለሆነም በጣም ለድጋፍ ዳታ ያበዛሁበት የአቶ ደመቀ መኮነን ነገር አቋሜን ጥርት ባለ መልኩ ደጋፊያቸው ሆኜ እንድቆም አስችሎኛል የሰሞናቱ የአቶ በረከት ስምዖን ኑዛዜ፤ ወቃሳ እና በዛቸው ላይ እንደለመደባቸው የከፈቱት ዘመቻ። ስለሆነም ከዛሬዋ ዕለት  ከእለተ ሃሙስ የቀን ቅዱስ 30.08.2018 ጀምሮ የአቶ ደመቀ መኮነን ደጋፊ

እንሆነት ... ዴሞክራሲ

ምስል
ወትሮም። „የእግዚአብሄር ባርያዎች እግዚአብሄርን ያመሰግኑታል። እርሱ የተመሰገነ ነው። ለዘለአለም የተመሰገነ ነው።“ ተረፈ ዳንኤል ቁጥር ፷፩ ከሥርጉተ © ሥላሴ 29.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የመፍትሄው መንገድ ወትሮም አንድ ነው። ከግራ ዝንባሌ ጋር መፈታት። ራስን ማሸነፍ። ነገር ግን ግራ ሁልጊዜም ግራ ነው። የአላዛሯ ኢትዮጵያ የህልውናው ችግር ይሄው ነው። እራሱን ችሎ እኮ የአላዛሯ ኢትዮጵያ የህልውናዋ የማንነቷ ታጋድሎ ያስፈልግ ነበር እኮ።  የዚህ ዝንባሌ አለው ተብሎ ነው እኮ ነው የአማራ የህልውና የማንነት ታገድሎም የተፈራው፤ የተገለለው፤ ዕውቅና ሳያገኝ ተድብስብሶ እንዲቀር የተፈለገው። ምክንያቱም ጨቋኝ እና ተጨቋኝን ፈጥሮ ኢትዮጵያን ለማመስ ዋነኛው ፒላሩ ይሄው ነበር እና። ይልቅ ቀቀድሞው ጠ/ ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ዚንባቢዎ ሰሞኑን ለውጪ ሚዲያ በሰጡት ቃለ ምልልስ የአማራን ተጋድሎ አውስተው ነበር። ተመስገንም ብያለሁኝ።  የሆነ ሆኖ ወትሮም ቢሆን ይሄው ነው የ43 ዓመቱ ለፍትህ እና ለነፃነት፤ ለህግ የበላይነት እና ለሃሳብ ልዕልና ተጋድሎ መደረጉ አንዱን በዳይ ሌላውን ደግሞ በዳይ በማድረግ ነበር። ሊዘህም ነው የ አማራን የህልውና የማንነት ተጋድሎ ያን ህዝበ ጠቀም ለማድረግ ያለው ቀናነት ዘሞ እንዲቀር የተደረገውም ሥሩ ያ ነው።  አሁንም በግራ በቀኝ ያሉት ወጀቦች የዛ ቅሪት አካል ናቸው። ሥር ነቀል ለውጥ ከኢህአድግ መራሹ ይታለማል? ይገርም ነው ዘንድሮ፤ እራሱን ኢህአዴግ ያክስምልን በራሱ ሜዳ ተጫውቶ? እንዴት ይደንቃል ይሄ ጥንዝል ፍልስፍና።  ለውጡን የሚመራው ኢህአዴግ ሆኖ ማለት ነው። ኢህአዴግን አንይህ ብሎ ነገር አዋጪ አይደለም።  በዚህ ዙሪያ አሉታዊ ሃሳቦችን እ

አላዛሯን ኢትዮጵያ የእኔ የማለት።

ምስል
የመቻቻል እጬጌዊቷ፤ ሉላዊቷ እናት ጠ/ ሚር አንጌላ ሜርክል  ለኢትዮጵያ! „አቤቱ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቁጥራቸውም እንደ ምን በዛ! ብቆጥራቸው ከአሽዋ ይልቅ ይባዛሉ፤ ተነሳሁም፤ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፰ ቁጥር ፲፯ እስከ ፲፰  ከሥርጉተ©ሥላሴ  28.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·         የልብ አድርስ ዜና። ውዶቼ የማከብራችሁ ትንሽ የልብ አድርስ ዜና አለችኝ። ያው የጹሑፌ ታዳሚዎች እንደምታውቁት እኔ በጀርመኗ መራሂተ መንግሥት በጠ/ ሚር  አንጌላ ሜርክል ልዩ የሆነ ተመስጦ አለኝ።  የ21ኛውም ምዕተ ዓመትም የሉላዊ የመቻቻል እናት ናቸውና። ሶርያ ያን ጊዜ እንደዛ በሁለገብ ችግር ስትናጥ፤ ስደተኛ እንደ ጎርፍ አውሮፓን ሲያጥለቀልቅ በነበረበት ወቅት ከስደቱ ግዝፈት አንፃር ሁኔታው ለአውሮፓው ህብረት ከአቅም በላይ ሆኖ ነበር። በዛ ላይ የሽብርተኝነት አደጋው ደግሞ መጠነ ሰፊ ነበር። ብዙም ተከታታይ አደጋ ነበር በፈረንሳይ እና በቤልጄየም። በሌሎች አውሮፓ አገሮችም ስጋቱ ይህ ነው አይባልም ነበር።  ስለሆነም የአውሮፓ ህብረት አገሮች የሚችሉትን ሁሉ አድርገው፤ ሸክሙ ሲባዛ በበቃኝ ፊታቸውን ሲያዞሩ እንሂ የዓለማችን ድንቅ ጽድቅ ግን ሁሉንም ነገር ተቋቁመው ያን የመከራ ጊዜ ተጋፈጡ። የርህርህና ጉልላቷ ዶር አንጌላ ሜርክል በሚመሩት በፓርቲያቸው በCDU አባላት፤ በደጋፊዎቻቸው፤ በአጋር እህት ድርጅቶች ሳይቅር ተዘርዝሮ የማያልቅ ፈተና ውስጥ ነበሩ። ተጨማሪ አዲስ የናዚ መንፈስ አራማጅ ፓርቲ አስከ መፈጠር የተደረሰበት ጉዳይ የስደተኛው መጠን ያለፈ ብዛት እና የነበረውም የህግ ጥሰት ቀወስ አስፈሪነት ነበር። ሴት ል