አላዛሯን ኢትዮጵያ የእኔ የማለት።
የመቻቻል እጬጌዊቷ፤ ሉላዊቷ እናት
ጠ/ ሚር አንጌላ ሜርክል ለኢትዮጵያ!
„አቤቱ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደምን እጅግ የተከበሩ
ናቸው!
ቁጥራቸውም እንደ ምን በዛ!
ብቆጥራቸው ከአሽዋ ይልቅ ይባዛሉ፤
ተነሳሁም፤ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ።“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፰ ቁጥር ፲፯ እስከ ፲፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
28.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
- · የልብ አድርስ ዜና።
ውዶቼ የማከብራችሁ ትንሽ የልብ አድርስ ዜና አለችኝ።
ያው የጹሑፌ ታዳሚዎች እንደምታውቁት እኔ በጀርመኗ መራሂተ መንግሥት በጠ/ ሚር አንጌላ ሜርክል ልዩ የሆነ ተመስጦ አለኝ።
የ21ኛውም ምዕተ ዓመትም የሉላዊ የመቻቻል እናት ናቸውና።
ሶርያ ያን ጊዜ እንደዛ በሁለገብ ችግር ስትናጥ፤ ስደተኛ
እንደ ጎርፍ አውሮፓን ሲያጥለቀልቅ በነበረበት ወቅት ከስደቱ ግዝፈት አንፃር ሁኔታው ለአውሮፓው ህብረት ከአቅም በላይ ሆኖ ነበር። በዛ ላይ የሽብርተኝነት አደጋው ደግሞ መጠነ ሰፊ ነበር። ብዙም ተከታታይ አደጋ ነበር በፈረንሳይ እና በቤልጄየም። በሌሎች አውሮፓ አገሮችም ስጋቱ ይህ ነው አይባልም ነበር።
ስለሆነም የአውሮፓ ህብረት አገሮች የሚችሉትን ሁሉ አድርገው፤
ሸክሙ ሲባዛ በበቃኝ ፊታቸውን ሲያዞሩ እንሂ የዓለማችን ድንቅ ጽድቅ ግን ሁሉንም ነገር ተቋቁመው ያን የመከራ ጊዜ ተጋፈጡ።
የርህርህና ጉልላቷ ዶር አንጌላ ሜርክል በሚመሩት
በፓርቲያቸው በCDU አባላት፤ በደጋፊዎቻቸው፤ በአጋር እህት ድርጅቶች ሳይቅር ተዘርዝሮ የማያልቅ ፈተና ውስጥ ነበሩ።
ተጨማሪ አዲስ የናዚ መንፈስ አራማጅ ፓርቲ አስከ
መፈጠር የተደረሰበት ጉዳይ የስደተኛው መጠን ያለፈ ብዛት እና የነበረውም የህግ ጥሰት ቀወስ አስፈሪነት ነበር። ሴት ልጆች በአደባባይ እስከ መድፈር የደረሰ አደጋ ሁሉ ነበር። እኒህ ብርቱ የአውሮፓ
አንጎል የሆኑ አንስት፤ ጽኑ ደፋር ፖለቲከኛ ግን ፈተናውን ሁሉ ረተው ዛሬን ሰጡን። ጀግና!
የሶርያ ህዝብ ስደት የህፃናቱ ጉዳይ እጅግ አሳዛኝ
ነበር። የነፍሰጡር ሴት ስደተኞች ደግሞ መፈጠርን ይፈትን ነበር። አደጋውም እጅግ ሰቅጣጭ ነበር። ስደተኛው መንገድ ላይ እያለ „የት ነሽ አንጌላ“
ሲል እንባ በእንባ እሆን ነበር።
ክብርት ዶር አንጌላ ሜርክል ያን የመከራ ማዕበል
ፊት ለፊት ወጥተው በመጋፈጥ የዓለም እናትነታቸውን ያስመሰከሩ፤ ዘወትር በመልካም ተግባራቸው የሚወሱ ልዩ አብነት ናቸው። ብርሃናቸውም
የማይጠፋ የድንቆች ሁሉ ተምሳሌት ናቸው። ብልጹግ የሆኑም የተግባር ልዕልትም ናቸው።
ክብርት ዶር አንጌላ ሜርክል ፈተናዎቻቸውን የሚፈቱባቸው መስመሮች
እና የከባዱን የጀርመን የሊሂቀ ሊሂቃኑንቃኑን የሃሳብ አቅም ሞግተው በማቻቻል እረገድም ብቃታቸው የሴቶችን የፖለቲካ አቅም፤ የሴቶችን
የማድረግ አቅም በግሎባል ደረጃ ያነጠሩ ባለብሩህ ጭንቅላት የፍቅራዊነት ንግሥት ናቸው። ለ አውሮፓው ህብረት ደግሞ የጀርባ አጥንት ናቸው።
እርግጥ ነው በለፈው ምርጫ ጊዜ ስጋት ከነበረባቸው
ሰዎች አንዷ እኔ ነበርኩኝ። ፉክክሩ ጠንካራ የነበረ ቢሆንም ሲያሽንፉ ቤቴ ሁሉ መብራት ነበር። ለተገፉ እናቶች፤ መጠጊያ ላጡ ሴቶች፤
ለህፃናት ልዩ አቅም ናቸው። ሥጦታችንም ናቸው።
ለሰብዕዊ መብት መከበር ደግሞ ፒላር ናቸው። እንዲያውም
ለእኔ የሰባዕዊ መብት ተሟገችም አክቲቢስትም ናቸው። መሪነታቸው ከእናታዊ ሩህሩህ አንጀት ጋር ነው። አድማጭነታቸው ደግሞ እዮራዊ ነው። ብዙ ሸክምን ነው የሚያቃልሉት። ስለሆነም ለእኔ ዕንቁዬ ናቸው። አይቼም አልጠግባቸውም። እሳሳላቸውምአለሁኝ።
እጬጌዊቷ ጠ/ ሚር ሜርክል ለድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ
እናቶች ዕንባ ዕጅግ ቅርብ የሆኑ ህሊናችን ናቸው። እውነት ብናገር
በቴቪዥን መስኮት ሳያቸው ካለ እኔ ፈቃድ ነው ዕንባዬ የሚወርደው። ውሳጣችን ናቸው። ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባነሩ ላይ አንድ
ነገር አነበብኩኝ እና ደስ አለኝ።
ክብርት ጠ/ ሚር ሜርክል ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ
ስልክ እንደ ደወሉ እና አንዳነጋገሯቸው አነበብኩኝ። በውነት ከደስታም በላይ ሐሴት አደረኩኝ። ውይይቱ አዎንታዊ እንደሚሆን እና
ደስ ብሏቸው እንደ ደወሉ አስባለሁኝ።
በኢትዮጵያ ሴቶች የነፃነት እጦት፤ በሴቶች በፖለቲካ ህይወት
ባይታዋርነት፤ እና የመገለል ጭቆና እንዲሁም ባለቤት አልባነት ውስጣቸው እብዝቶ ያዘነ ነበር። አብሶ ዴሞክራሲ ፈልሶ እንደዛ በድቅድቅ ጨላማ ውስጥ
አላዛሯ ኢትዮጵያ ፍዳዋን መክፈሏም አጀንዳቸው ነበር።
አሁን ግን ጅምሩ፤ ውጥኑ አበረታች ስለመሆኑ ተስፋ
እንዲሰንቁ ያድርጋቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። እርግጥ ነው ከ2 ሚሊዮን በላይ በታቀደ ሁኔታ የደረሰው የወገን መፈናቀል ዕንባም ይጎረብጣቸዋል
ብዬ አስባለሁኝ።
በሌላ በኩል ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ያለው የተስፋ ጅምሮም፤ እንዲሁ ተስፋ ሰጪ መሆኑ ያስደስታቸዋል ብዬም አስባለሁኝ። በነፃነት አርበኞች ከካከቴና መላቀቅም ከሁሉም በላይ ለሳቸው የቀረበ
የደስታ የምስራች እንደሚሆን አልጠራጠረም። ኢትዮጵያ ጉዳያቸው ናትና።
እርግጥ ነው በጀርመን መንግሥት ዝምታ ማብዛት ብዙም
ባልረበሽም፤ ነገር ግን እስካሁን ድርስ ምንም ምልክት አለመኖሩ ይገርመኝ ነበር። አሁን ግን መሬት ላይ ያለውን ዕውነት በውክል
አካሉ ማረጋገጥ ይገባ ስለነበር ይመስለኛል ዳታው። ረግቶ፤ ሰክኖ መመልከቱም መልካም ነው። „የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል“ እንዲሉ።
ከሰሞናቱ ወደ ኢትዮጵያም ወደ ኤርትራም ልዑክ ከጀርመን
መንግሥት መላኩ ይታዋሳል። የዛ መረጃ አዎንታዊነት መሰለኝ ባለርግጥ ሆነው ስልክ ለዶር አብይ አህመድ ለመደወል ያስቻላቸው ክብርት ጠ/ ሚር አንጌላ
ሜርክልን።
ኢትዮጵያዊው የነፃነት ፈላጊው ብዙም ግልጽ ላይሆንለት
ይችል ይሆናል። ግን የጀርመን መንግሥት ለመላ ኢትዮጵውያን ነፃነት የነበረውን ቀናዒነትን ያህል የከወነ የለም ብዬ አስባለሁኝ።
ተናጠላዊ የሆኑ ከአንድ የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት
ጋር የሚያግዙ ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል፤ ወይንም ድርጅቶች፤ ወይንም ግለሰቦች ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል፤ በመንግሥት ደረጃ፤ በመሪ
ደረጃ ግን የጀርመን ግን ሁሉንም አካታች የሆነ በተለይም በኢትዮጵያ እናቶች ተኮር፤ በነፃነት ታጋይ እስርኞቻችን ላይ፤ በተፎካካሪ
ፓርቲዎች ተገላይነት ላይ እጅግ የእኔ ያለው አጅንዳው ነበር ለጀርመን መንግሥት።
ውሳኔምውም፤ አቋሙም ግልጽ ነበር። ምንአልባት ዕድል
አግኝተው ኢትዮጵያ ቢሄዱ በጣም እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው እንዳለፈው ጊዜ ከኢህዴግ የሚቀርባላቸውን ጥያቄ አሻም የሚሉ ላይሆን ይቻላል።
አሁን ጠረኑ ሰውኛ መሆኑ፤ አሳታፊ ለመሆን መፍቀዱ፤ አቃፊ ለመሆን ያለው መሰናዶ፤ አብሶ በሴቶች በኩል ያለው የፖለቲካ ተሳትፎም
እና ተነሳሽነትም ውጥኑ የሚበረታታ ስለሆነ አዎንታዊ ምልከታው ሚዛን ይደፋል ብዬ አስባለሁኝ።
ሲጠቃለል ሁኔታውን አብዝቼ የመከታተለው መደበኛ ሥራዬ
ስለሆነ ዛሬ ዜናውን ሳይ ደስ ብሎኛል። የሁለቱ አገሮች ጠ/ ሚሮች በስልክ መገናኘት ምን አልባትም እንደ ፈረንሳይ ግብዥም በቀጣይ
ሊኖር ይችላል ብዬ አስባለሁኝ። ይህ ቢሆን አጅግ የበለጠ ደስ ይለኛል። ምክንያቱም የታማኝነት ህልውና ያስጠብቃል ብዬ ስለማስብ። ፊት ለፊት፤ ገጥ ለገጥ መገናኘት ደግሞ ትርፋማነቱ ዲካ የለሽ ነውና።
ሳጠቃልለው ይህ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ እና ለለውጡ ሐዋርያት ልዩ የአቅም
መቅኖ ነው። ክብርት ጠ/ ሚር ሜርክል የጀርመን መሪ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን መንፈሳቸው የተለዬ ነው። ነፍሳቸው ሰውኛ እና ተፈጠሮኛ
ነው። ጠረናቸው እናታዊ ነው።
ክብርት ጠ/ ሚር ሜርክል የምዕቱ የፍቅራዊነት መሪ ናቸው- ለእኔ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ክብርት ጠ/ ሚር አንጌላ ሜርክል የመከባባርም መሆን ናቸው። የቸርነት ቅኔም- ጥበብም ናቸው። የመሪነት ሎሬትም ናቸው። የብቃት ቃናም ናቸው። የመቻቻል አዝመራም ናቸው። የማድመጥ ተቋም ናቸው።
እውነታኛዋ እናታዊዋ ርህርህናዊ መራሂነታቸው፤ ስለስብ ትጋታቸው እና ሉላዊነታቸው የልብ አድርስ የአንጀትም አርስም ነው። በተገኙበት አለምአቀፍ ይሁን አህጉር አቀፍ ጉባኤ ላይ ሁሉ አግላይነትን እና ጨቋኝነት የሚጠዬፉ የሚታገሉም ብርቱ ሴት ናቸው!ማእካለቸው ሰውነት እና ተፈጥሯዊነት ብቻ ነው። ልዑል እግዚአብሄር ይጠብቅልን። አሜን!
- · ምርኩዝ።
ውዶቼ በዚህ ዜና ውስጥ ባንሩ ላይ ነው ማንበብ የምትችሉት።
„Ethiopia: በብላክ ማርኬት ዶላር በህገወጥ ሲሸጡ የቆዩ ሱቆች ታሸጉ!!
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ
ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ምሽት።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ