ቧልተኛው አቶ በረከት ስምዖን ...
የአቶ በረከት ስምዖን ቧልት።
„አኔ በስውር በተሰራሁ ጊዜ፤ አካሌም በምድር ታች
በተሠራ ጊዜ፤ አጥንቶቼም ከአንተ አልተሰወሩም።“
ከሥርጉተ©ሥላሴ
28.08.2018
ከኮሽ አይሏ ሲዊዝ።
የአማራ ልጅ የተስፋ ትምህርት ቤት።
ይሄ ነው ድል የሚባለው የእነ ሳጅን በረከት የሰሞናቱ ምሾ።
ይገርም ነው ነገሩ። አሁን ኢትዮጵያ ነበረች እያሉ ነውን እነ ሳጅን በረከት የሚፎካክሩት? እሚገርም ታሪክ እኮ ነው እዬተጠመደ ያለው። አሁን ያለው የብአዴን አመራር ለኢትዮጵያ ህልውና ያሰጋልም ነው የሚሉት አቶ በረከት ስምዖን?እኛ የመራንበት ዘመን ንጥር ነው እያሉን ነው? ይገርም እስከ ወዲያኛው። ይህን መሰል ቧልት ከቻሉስ ስለምን አቶ በረከት ስምዖን የኮሜዲ ማሰልጠኛ አይከፍቱም? የውነት ይሻላቸው ነበር።
እንግዲህ ምርኩዞቹን ሁሉ እንደማይቀጥሉ አልሻም ማለቱን ሰሞኑን ብአዴን ልብ ሰጥቶት ውሳኔ አሳልፏል። እርግጥ ነው ብአዴን ፌድራል ላይ ውክል አድርጎ የሚልካቸው አካሎቹ ያው ተዘው ቤተ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ነው፤ ከአንድ ምንጭ፤ ትግራይም ተውክላለች የራሷን ልጆች፤ ድምጽም አላት እኩል 9ኙም 45ም፤ ብአዴን ደግሞ ተጋሩን ባህርዳርም በዳብል ያስኬድለታል።
የባህርዳሩ ቢሮው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ለተጋሩ ሽፋን በመስጠት፤ አማራ በማህሉ አፈር ላይ እንደ ተረገጠ የእንብርክክ ይሄዳል። ነፍስ ያለው ሰው ስለዚህ የግፍ ዘመን እና የሚስጢር ቅብረት የ እኔ አለማለት መቼም በድንነት ነው።
የሆነ ሆኖ ብአዴን ለኢትዮጵያ ተስፋም ቀጣይነትም አስጊ ነው ማለታቸው ብአዴን አማራነትን አጥብቋል ከሆነ መቼም ተመሰገን ነው። ይሄ በፆም በጸሎትም የማይገኝ እዮራዊ አዲስ መባቻ ነው።
ለነገሩ ዛሬ ከአቶ አቻምየለህ ታምሩ ያገኘሁት ጹሁፍ እንደሚናገረው ደግሞ ያው ብአዴን የወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ የቅኝ ተገዢነቱን ባርኔጣ እንዳላወቀ ይናገራል መረጃው።
ሕውሓት በአማራ ላይ የሾማቸው ሁለቱ ቅኝ ገዢዎች እያሴሩ ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)
„ከታች የምትመለከቱት [ወጣቱ] አሚር አማን ሐጎስ ይባላል። እናቱም አባቱም የሕወሓት ሰዎች ናቸው። እናቱ የቴዎድሮስ አድሐኖም እህት ናት። አሚር አማን የብአዴን ስራ አስፈጻሚና የአማራን ድርሻ ወስዶ የጤና ጥበቃ ሚንስትር ሆኖ እየሰራ ይገኛል።“ እንደ ብአዴን እኮ መሳቂያ ድርጅት አልተፈጠረም ኖሮም አያውቅም። ወኪል አምጡ፤ ሪኮመንድ አድርጉ ሲባል የአማራ ብቁ ሰው ጠፍቶ ያው ከጌቶቹ ሥር ይነጣፋል አቤቶ ብአዴን። መሳቂያ!
"ሁለተኛው ሰውዬ «የአማራ ክልል» የሚባለው ምክር ቤት ሕግ ተርጓሚ ፣ አማራን ወክሎ የፌዴሬሽን ም/ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ክፍል ሰብሳቢ ነው። " ስሙ መኮነን ወልደ ገብርዔል ይባላል። የሕወሓት ታጋይ ነው።“ የፌድራሉ አፈ ጉባኤ ደግሞ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። ዳብል ድምጽ አላቸው ማለት ነው። ከብአዴንም እነ ታጋሩ።
በስንቱ ይሳቅ? ይግርም እሰከ ወዲኛው ነው። እኔ እኮ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስለምን አይለውም ነበር ብአዴን ከሚባል። ለነገሩ አሁን አርማዬንም ሥያሜዬንም እቀይራሉኝ እያለ ነው። አማራን ማስወከል ነው ቁም ነገሩ። አማራን ማብቃት ነው ቁምነገሩ። ዕድሉን እያሰላፈ እዬሰጠ ምኑን ነው ሥልጣን ውክልና የሚለው ይሆን ብአዴን? አቶ አለምነህ መኮነን አክሎ ተሸክሞ እሽሩር እያለ የአማራ ድርጅት ነኝ ማለት እራሱ ያሳፍራል። ወንዱ ኦህዴድማ ጥርት ባለው መንገድ እራሱን አስወክሎ ዘመኗን ያጣጥማል በጥምር ድል።
የአማራ ብሄር ድርጅትነት ቧልት እና ቀልዱ ይሄው ነው። ድርጅቱ የአማራ ይባላል ተግባሩ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይን የኮታ፤ የውክልና ውርስ ማሳካት ነው። ለዚህ ነው አማራ ሊሂቅ በቅብረት 27 ዓመት የተኖረው። ዛሬም ይህ ትወና መኖሩ ይገርም ነው። እሰከ መቼ ለሚለውም ገደብየለሽ ነው። በዚህ ርዕዮት ሁሉም ሊሂቃን ይሰማሙበታል። አማራ የሚፈለገው በቃ ለጠበንጃ ያዥነት፤ ለእግረኝነት፤ ለዘበኝነት ብቻ ነው የሚፈለገው፤ መናጆነት …
አሁን ከሊቅ እከከ ደቂቅ መታመሱም ከዚህ የታመሰ መንፈስ የሚቀዳ ነው። አማራ አሁንም አቅም ያለው ይመራው እንጂ ከዚህ መጣ አትበሉ አይባልም፤ ስለምን ይህን ሌላው ክልል አይባልም? ስለምን ይሄ ሌላው ክልል ላይ አይደፈረም?
የሆነ ሆኖ ሳጅን በረከት ስምዖን ላፈረሷት ኢትዮጵያ ሳይቆጩ ገና ልትፈርስ ነው ብለው ሰግተዋል። መጀመሪያ አገር መኖሯ ይረጋገጥ። አብዮታዊ ዴሚክራሲ የአፍሪካ ነብርነት እከኩ እኮ ታዬ በአደባባይ። ለዚህም እኮ ነው አሁን ወደ አፈረስነው ኢትዮጵያዊነት እንመለስ የሚባለው። አማራ ኢትዮጵያ አልክ ተብሎ 27 ዓመት ሙሉ ፍዳው በላ፤ አሁን ደግሞ እሱ አማራ ነኝ ሲል ደግሞ ተፈራ እና ወንጀል ነው ተባለ አማራዊ ዞገኝነት።
ሁለም አማራ ላይ ሲደርስ ነው ወንጀል የሚሆነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲል እስር፤ ግድያ፤ ስደት፤ አፈና ገጠመው፤ እሺ ይሁንላችሁ ብሎ አማራ ነኝ ሲል ደግሞ ደረጃው ወረደ፤ ለአማራ በዞግ መደራጀት አያምርበትም፤ ለኢትዮጵያ አስጊ ነው፤ አማራ የአባቶቹን ሌጋሲ ያስቀጥል ወዘተ ይባላል፤ ከዛም አልፎ ተርፎ የአማራ ሥነ - ልቦናዊ አቅሙ የእሱ አይደለም ተውሶ ነውም አለበት። አማራ ሥነ -ልቦናው በቅብረት እንዲኖር ያልፈረደበት ዜጋ ለማግኘት ይቸግራል። ሃጢያተኞች!
የሆነ ሆኖ ብአዴን ሌላም ማስጠንቀቄያ ተስጥቶላት። ሳጅን በረከት የሚመሩት የሴራ መረብ አፋር ላይ ደግሞ ግጭት እንዳሰናዳለት ልብ ሊለው ይገባል። አፋርም ቢሆን ግጭቱን ላለማድርግ ልብ ሊገዛ ይገባል። የኢትዮጵያ የመካላከያ ሠራዊትም በዚህ ባገኘው መረጃ መሰረትነት ጥንቃቄ እና ልዩ መሰናዶ ማድረግ ይገባዋል። ሳጅን በረከት ስምዖን ዝም ብለው ዘው አያደርጉም መረጃ። የቀረው የቀውስ ቀጣና አፋር ብቻ ነው። አፍር እና አማራን ቀውስ ውስጥ ለመጣል አዲስ ጥንስስ እንዳለ ተደምጧል። ፌዳራል መንግሥትም ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል። ሰው ከተፈናቀለ እና ጥፋት ከተፈጸመ በሆዋላ ከመረባበረብ ከጥፋት በፊት ብርቱ ጥንቃቄ ለግራ ቀኙ ይጠቅማል።
ሌላው ሳጅን በረከት ስምዖን እኔን ከሥልጣኔ ያሰወገዱኝ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው ባይ ናቸው። መቼም ይህን እውነት ፈጽመዎት ከሆነ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ታላቅ ባለውለታ ናቸው። የውነት ከልቤ ላመሰግናቸው እሻለሁኝ። ዛሬ በዬቦታው በዬሁኔታው ስሞታቸውን እያሰሙ ነው አቶ በረከት ስምዖን። እንደ ሽብርም አድርጓቸዋል። መቅኗቸው ፍስስ ያለ ይመስላል ... ግን ለሴራ መቼውንም ቢሆን አይዝሉም።
ደግሞ ገራሚው ነገር እርጅናዬን ጎንደር ወይ ባህርዳር አሳልፋለሁ ብዬ ነበር ነው የሚሉት። በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ ነው። ማህከነ! ተሳህለነ! ማረን! ይቅር በለን ያሰኛልም።
ይህንማ እማ አያድርገውም ልዑል እግዚአብሄር። ደግሞ መረብ ሰርተው ብቅ የሚሉትን የአማራ ልጆች ብበክለት ለመለቀም ነው ይህ እሳቤቸው። መቼም ቀና ለማሰብ አያታሰቡም እና። የጃርት መንፈስ ነው ያለባቸው ሰውዬው … ወይንም እፉኝት እዬገደሉ መወለድ …
ብቻ ብቻ የሳጅን በረከት መንፈስ መጠለያ ስለጣም ይመስላል እኔ አማራ ነኝ ከማለት የማንነት ቀወስ ወጥቶ ዛሬ ጎንደር ተውልጄ ያድኩኝ ኤርትራዊ ነኝ የሚሉት። እኛም ያልነው እኮ ይህንኑ ነበር። ሊሸከሙት ባልቻሉት ቀወስ ውስጥ መኖራቸው እኮ ነው አቴንሽን ሲከር ያደረጋቸው ... ሁልጊዜም አትርሱኝን ደጅ ሲጠኑ የሚገኙት በዚኸው ነው።
አቶ በረከት ስምዖን ሆነ ካቢናቸው ሲቀልድ ባጀ፤ አማራ ሳይሆኑ አማራ ነኝ ብሎ 27 አመት በሙሉ የሞት ተዝካርም፤ የመኖር ተዝካርም፤ የተስፋ ተዝካርም ባጀበት - አማራ። በጸረ አማራ ቡድን ታረደ፤ ተፈናቀለ፤ መሞከሪያ ሆነ፤ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር ተገደደ፤ ተገለለ፤ ቅስሙ ተሰበረ፤ መከነ ተወረረ ተዘረፈ ምን ያልሆነው ነገር አለና … አማራ።
አሁን ሁሉም የልቡን ሠርቶ ደግሞ እንደገና አማራ ስለ ራሴ በትውስት ሳይሆን በመንፈሴ ውስጥ ሁኜ ለህለውናዬ እታገላለሁ ሲል ሌላ ጨዋታ መጣ፤ ከራሱ ከሊሂቃኑ ሳይቀር፤ ድሮም የቀበሩት እነሱው ናቸው፤ ዛሬም ተቀብሮ እንዲቀር እዬዶለቱ ያሉት እነሱው ናቸው።
የሆነ ሆኖ የመጨረሻ ቀኑ ከሆነ የሳጅን በረከት ስምዖን ኑዛዜ አውን ከሆነ፤ መቼም አማራ የዘንድሮውን መስከረም ቅዱስ ዮሖንስን የሳጅን በረከት ስምዖን የህልፈት ዘመን ብሎ ዲል አድርጎ ደግሶ ማከብር አለበት የውነት።
ጥላውንም፤ ሻማውንም ማስገባት ያስፈልጋል ለዬታቦቱ። ለግሼን ብዬ ነበር ሥልጣን ለቀቅኩኝ ባለሉበት ጊዜ አውነት ከሆነ በማለት፤ አዎን ለታቦታት ሁሉንም ነገር ማድረግ ይገባል። ስለታችን እዬሰመረልን ነው።
አማራ በጉድጓድ ውስጥ እንዲኖር ያደረጉት አቶ በረከት ስምዖን ናቸው። በቃህ ከተባለ አማራ እሳቸውን ለመጨረሻ ጊዜ ያለቀው ልዑል እግዚአብሄር …. ስለ ነገረ እትዮጵያ አሁን ሙሴ አላት ጭንቅ የለም፤ አጋፋሪም አያስፈልግም …
ብአዴን ነፍሱ ካለችም ይህን የተዛበ የፌድራል ውክልና ጉዳይ በአስቸኳይ መስመር ያስይዘው፤ ይህም ለራሱ ቢል ነው። ይሄ አጉል እውደድ ባይነት እና ከንቱ ውዳሴ የትም አያደርሰውም ብአዴን። ሁሉ የተወከለበትን አጀንዳ ነው እዬሠራበት ያለው … ሥራውን ይሥራ ብአዴን የተወከለበትን ተፈጠርኩ ለ አማራ ካለ ... አለዛ ያው ነው ... መፍረስ ...
„አማራነት ይከበር!“
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ