ክፍል ሁለት ማጠቃለያ፤ ዓይነ ጠባብነት!

ወጣቶች እንደ 66ቱ ዘመን ዓይነ ጠባቦች መሆን አይገባቸውም።
ክፍል ሁለት ማጠቃለያ።



ከሥርጉተ ሥላሴ 29.06.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
 „የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፤ ብርቱ መጠጥም 
ጠበኛ ያደርጋል፤ በዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም“ 
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፩)
  • ·      እፍታ


ዛሬ ነው ከብራና ሳተናው የገባሁት። ትናንትና በተከታታይ የጻፍኳቸው የሰቆቃው አማራ ጉዳይ እና የእውነት ጠበቃ ማጣት በሚመለከት ስጽፍ ስለዋልኩኝ ጊዜ አልነበረኝም።
  • ·      መነሻዬ።

አሁን ዛሬ ሳተናው ብራና ላይ የኢሳቱ ጋዜጣኛ አቶ መሳይ መኮነን የመደመር ፖለቲካ አስፈርቶታል።ከዚህ አንዳንዶች ባይደመሩስ?“ (መሳይ መኮነን)
„አንዳንዶችስ ባይደመሩ ይለናል?“  ትንታጉ ጋዜጠኛ። ጽዋው የማንፌሰቶ ማህበርተኝነት ነው። ሌላ ቁምነገር የለውም። መልካም ነገር ግን ብሄርም፤ ፖለቲካም፤ ማንፌስቶም የለውም። የሆነ ሆኖ የኔዎቹ ማጠቃለያው እንሆ። የይቅርታ ልብ ሳይኖረን ለውጥ ያማል። ንጹህ ልብ ሳይኖረን ኢትዮጵያዊነት ይጎመዝዛል። ኢትዮጵያ ሰፊ አገር ናት ሁሉንም እንደ አመሉ የመቻል አቅም ችሎታ ክህሎት አላት።

ሰዎች በደከሙበት የመደመር ዕልፍኝም ቤተኛ እና ተርተኛ ይለይ ይከብዳል። ሁልጊዜ በ አጥር ተከልሎ ሁልጊዜ ቂምን ተጠልሎ ሁልጊዜ ቋስን እርሾ አድርጎ ተውልድን መገንባት ጋዳ ነው። የሚያውል የሚያሰድር የ አምክንዮ አቅም ጠፋ፤ አጅንዳ የለም መሼ ነጋ መብተክተክ …
  • ·       ገመና።

ይሄ ሁሉ ጓዝ ተይዞ ማህበረ ደራጎንን ማሸነፍ አይቻልም። ስንት ገመና ነው ያለው። አንድ ጊዜ የተዋናይት እና ደራሲ ቅድሳን ቃለ ምልልስ ላይ ድራግ መውሰድ የሚጀምሩት 6ኛ ክፍል ላይ ጀምሮ እንደሆን ስትገልጽ ሰውነቴ ነው የተንቀጠቀጠብኝ። በቃ ትውልዱ እኮ እዬጠፋ ነው። አፋር ላይ ዛሬ ሳዳምጥ  በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ የተቀበረው ፈንጅ በአግባቡ ሙያዊ ተግባር ስላልተፈጸመበት፤ በምን ግድዬለሽነት ባሊህ ባይ በማጣቱ ህዝባችን እያለቀ ነው።
በሌላ በኩል በታቀደ ሁኔታ በዬቀኑ ቤቶች አይደሉም ኑሮ በእሳት እዬነደደ ነው፤ በተሰላ ሁኔታ መብራት አገልግሎት እዬተቋረጠ ነው፤ በታቀደ ሁኔታ እነኛ ህጻናት ከኑራቸው ከተፈናቀሉ ወላጆቻው ጋር ሜዳ ላይ ፈሰዋል። 

አራሱ አኗር መስጊድ አጠገብ የነደዱትን ቤቶች ቁመና እስኪ አስተውላችሁ እዩት። አሁን ይህን የመሰለ ህዝብ እና ኑሮ ይዘን አሁንን ሎ፤ አሁንም ገበርዲን አሁንም ኬክ አሁን ሃኒ ሙን ያስፈልገናል። እንኳንስ ተቀንሰን ተደምርንም አይሆንም።

ክፉዎችን ልባቸውን ወደ መልካምነት መለወጥ የሚቻለው አንተ ክፉነትን ስተተው፤ የይቅርታ ሰው ስትሆን ነው። ይነገር - ይዘርዘር ቢባል ስንት መከራ ነው እኛ ተሸክመን የኖርነው በግንቦት 7 ካድሬዎች። እንዴ! በነፃነት አገር በግዞት እኮ ነው የምኖረው። ይሄ ቂም የሚያስቋጥር፤ ይሄ እርግማን የሚያመጣ ይሄ አልይህ አትዬኝ የሚያስብል ከሆነ የኢትዮጵያ እናቶ የ43 ዕንባ ቀጣይነት ናፋቂዎች ነን፤ የአዲስ አባባ የቦንብ ጥቃት አደጋም ፌሳታችን ነው ማለት ነው። 

በነገራችን ላይ ገና ሲጀመርም ተናግሬያለሁኝ የሴራ ፖለቲካ መንፈስን፤ ሥነ ልቦንን፤ ተስፋን ማውደም ተግባሩ ነው። ዋናው አብይ ጥያቄ ለዚህ እንተባባራለን ነው ወይንስ ከዚህ መሰሉ መሰሪ ተባበር አትደምረኝ እንላለን ነው መሰረታዊ ጉዳይ …

አሁን እንኳን ብንርፍ ምን አለበት? አሁን እንኳን ምን አለበት አደብ ቢኖረን። አዲስ አባባ የተረፈቸው እኮ በፈጣሪ ቸርነት እንጂ በሰውም ብልሃት ትበብብ አይደልም … መዳን ከራስ ይጀመር አሁን አተላ ሃሳቦችን እያመረትን አገር ምድሩንጥርጣሬ እና በቀል አናምርትበት።

ተግባር ነው ሰውን አንጥሮ የሚአወጣው እንጂ ቲፎዞ አይደለም። በጭብጨባ ቢሆንማ አውሮፓን ህብረት ልብ ውስጥ መቀመጥም ተችሏል። ዋሽንግተን ፖስትም ሜጄር ጄኒራል አድርጎ ሹሟል። BBC ደግሞ ፋክት ላይ ቁሙ ብሎ አፋጧል እና ወዲህ እና ወዲያ ሳይሆን ወይ መደምር ወይ መቀነስ ነው። የ እንተ ነገር ግን አንዲት ጠንቋይ ...

ይቅርታ አለማድረግ መብት ነው ይቅርታ የሚአደርጉትን ነፍሶች መኮነን ግን ወንጀል ነው። አሁን ኢሳት ሞጥሮ የለማን ያብይን መንግድ ሞጥሮ ከወያኔ በበለጠ በመንፈስ ልዕናና ጎርዶ ለመታል ታግሏል።

ዛሬ ደግሞ ካድሬዎቻቸውሁ ቀዳሚዊ የሚዲያ ባላቦቶች ሁነዋል ነገም አራጊ ፈጣሪ ትሆናላችሁ ድልዳል ስላል። ምን አልባትም ሪኮማንዴሽን ሰጪዎችም። ይህ ለ እኛ ጉዳያችን አይደለም እንኳን ለዚህ አበቃችሁ ነው። እኛ ጉዳያችን የሚሆነው ይህን የይቅርታ መንገድ እንደለመዳባችሁ ክትር ወሰን ደንበር እያሰራችሁ እናምሳለን ካላችሁ ግን አንላቀቀም ነው። ይህ ደግሞ አይቀሬ ነው።
አቅም ያለውን ሁሉ ከትክታችሁ ከትክታችሁ ብቄተ ቢስ አልባ አድርጋችሁ ጎልታችሁ መውጣታችሁ እናንትም ታውቁታላችሁ ሥራዬ ብሎ ከቅንጅት ጀምሮ ያሉትን ሳንኮች ለሚመረምር የሰከነ ፖለቲከኛም ይረዳዋል።

ጀማሪ ፖለቲካኛም አይደለንም። ሲዲ ቤት የከረምን ተንታኞችም አይደለንም። ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአጀንዳ የትግራይ ህዝብ ይወያይባቸዋል መልሰው ያመጧቸዋል ሲባል፤ መንገዱ ሥርአተ አልበኝነትን ነው አስቸኳይ ጉባኤ ማድረግ እስካልቻሉ ድረስ አይቻልም በመርህ ደረጃ ሁሉ ብያችሁ ነበር። ቅንጣት በቅንጣት የተሞገታችሁበት አመክንዮ ሁሉ አሸናፊ ነው የሆነው፤ እናንተ ደግሞ መውደቅን ስትደማምሩት ባጃችሁ።

አሁን ደንበር ሰርተን ተዚህ እና ተዚያ እናተራመሳለን ብትሉ እስቲባቃችሁ ይነገራችሁዋል፤፡ ውድድርም ስትጀመሩት። ተዘጋጁ እኛም ተዘጋጅተን እንጠብቃለን። ንጹህ ልብ ከሴራ የጸዳ ብቻ ነው ትወልድን ሊያስቀጥል፡ በዬተሄደበት በማፈረስ ፖለቲካ የትውልድ ብክነት መደምደሚያ ዘመኑ መሆን አለበት። ስለዚህ በህይወት ከኖርን ሙግቱ ስለሚቀጥል ተሰናዱ …  ከእናንተ ጋር መደመሩ በኢትዮጵያዊነት ፍልስፍ እና እንጂ በክት እና በዘወትር የዜጋ ካርድ እድለውማ ተኑሮበታል … እኛ እኮ በ እናንተ ውስጥ አልነበረም ወደፊትም አንኖርም። ይህን ለቀባሪው አረዱት አይሆነም የነረበት ሁሉ አደላድሎ ይመሰክረዋል።
  • ·       ክወና።  

በመሆን ውስጥ የሌለ ፖለቲካ ከመፈጠሩ በፊት ቃሬዛ ላይ የዋለ ነው። የሞተ ሃሳብ መሸከምም የሃሳብ ሬሳ ታቅፎ መተኛት ነው። አሳዛኙ ነገር የ የኢትዮጵያ እናቶች ግብር አቅራቢ ለሞተ አምክንዮና ሬሳ ለሆነ ሃሳብ አዲስ የሰው ቀረምት አቅራቢ መሆናቸው ብቻ ነው። ዛሬም ይህ እንዲቀጥል ነው እንድርቺ እንድርቺው። ግን ፈጣሪ አለ። ቅብዕ የፈጣሪ ነው። እሱ ይጠብቀዋል። ወገኖቼ ግርር ያለ የፖለቲካ አያያዝ ጥሩ አይደለም። የፖለቲካ አስተሳብ ዘንጣፋ፤ ለስላሳ -ዓይነ ሰፊ ሆደ ሰፊ - ህሊና ሰፊ - ቻይ - ታጋሽ መሆን አለበት። 
   
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

ቅኑን አሜኑን ሙሱያችነን ድንግልዬ ትጠብቅልን! „አሜን!“

ቅኖቹ የመልካምነት ባለሟሎች ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ!




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።