የወሎ ማህበር ምሥረታ የሴራው ሹርባ።


እንኳን ደህና መጡልኝ
የወሎ ማህበር ምሥረታ
የሴራው ሹርባ።
„ጥበብስ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።“
 መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26.03.2019
ከእመ ዝምታ።


·         መግቢያ

ትናንት አንድ ጹሑፍ ጽፌ ነበር። የግንቦት 7 ስብሰባ በባህርዳር መስተጓጎል ሆን ተብሎ ታቅዶ እንደተከወነ ። የወሎ ማህበርም በተመሳሳይ ሁኔታ የተከወነ ነው። ታቅዶ ታልሞ። በአዲሱ የብአዴን አመራር ጫና ለመፍጠር። ከኦነጋውያን የሜጫ ሱናሜ ጋር እኩል እንዲታይ ለማድረግ። የዚህ ቅንብር ባላንባራስ ደግሞ ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው የሳቸው ኔት ነው ይህን ተግባር የሚየስከውነው። ክልሉን ማወክ ያስፈልጋል። የሜጫ ፖለቲካ በሁለት እግሩ ይቆም ዘንድ … የሳቸውም የቃልኪዳን ሰነድ ይዘልቅ ዘንድ።

·         ጉዳይ።

የተከባራችሁ የጹሑፌ ታዳሚዎች ... በኢትዮጵያ የነበሩ 14 ክ/ አገሮች ነበሩ። እነዚህ 14 ክፍለ አገሮች በጣሊያን ትልም እሰፈፃሚ በኦነግ እና በህወሃት የወል ኮሶ ህገ መንግሥት ክልል በሚል ስያሜ በዛ ሥር ወድቀው ፍዳ እያስከፈሉ ነው። ዛሬ ጉዳዬ ይህ አይደለም።

አማራ የሚባል ማህበረሰብ ከዬለም ጀምሮ ሰፊ የምንጠራ እርብርብ 50 ዓመት ሙሉ ተካሄዶበታል። ይህ ሥልጡን እና አስተዋይ ህዝብ ትቢያ ለብሶ ከመቃብር በታች መኖሩን የሚያልሙ እልፎች ናቸው። ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ መንፈስ ሁሉ የዚህ ደቦ አባልተኛ ነው። እከሌ ተከሌ የለበትም።

ስለሆነም አማራን ወጥ መንፈሱን ለመጻረር የማይደረግ ነገር የለም። ያው ዘር አልባ እንዲሆን ከጸደቀው ህገ መንግሥት ጀምሮ በፖሊሲ ደረጃ 27 ዓመት ተግባሩ በትጋት ቀጥሏል።

እንሆ ዕድሜ ለጀግናው ኮነሬል ደመቀ ዘውዱ ያን ቋያ ሞገዳማ አብዮት አስነስቶ የአማራን መንፈስ ዳግም ልደቱ በመታወጁ ያገረሸባቸው መንፈሶች በግልጽ እና በስውር ደባ የተፈጠሩበትን እዬተገበሩት ይገኛሉ። እበሶ የ አብን ልቆ እና በቅቶ መውጣት እንሆ እያደናበራቸው ይገኛል።

የሆነ ሆኖ አማራን ለማዳከም አማራን  በመናጆትን የሚያሰልፉት ብልጦች በዬዘመኑ የሚሰሩት ሴራ ዋንኛው አማራን በክ/ አገር ማደራጀት ነው። ክ/ አገር የሚባለው የሚዲመጠው አማራ መሬት ላይ ብቻ ነው። አስቡት ወገኖቼ ኢትዮጵያ በቋንቋ ፌድራዚም በክልል እያለች ነው ይህ ፈሊጥ አማራ ላይ ብቻ የተጫነው። የወለጋ፤ የኢሊባቡር፤ የጋምጎፋ፤ የሲዳማ፤ የጅማ፤ የሀረርጌ፤ የባሌ፤ የአርሲ ማህበር የለም፤ ያለው የሽዋ፤ የጎንደር፤ የጎጃም ነው። አሁን ደግሞ የወሎ።

ይህ ለምን ስለምን ሆነ ብሎ አንድም ሰው ደፍሮ የሚጠይቅ የለም። አማራን ከሥሩ የማፍለስ ተልዕኮ ስለመሆኑ ልብ የሚለው የለም። የአማራ አቅም ራሱን ችሎ ወጥቶ የፖለቲካ ተፎካካሪ እንዳይሆን ለማድረግ ታስቦ፤ ታቅዶ የሚከወን ከጆኖሳይድ የማይተናነስ ነገር ነው የሚፈጸመው። አሁን የ አማራ ወጣቶች አብን በግራ በቀኝ እዬተዋከበ የሚገኝበት ሚስጢርም ይኸው ነው።

እንዲት በውጥረት አማራ ክልል እንደሚታምስ ስትመለከቱት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የፌድራሉን ማናቸውም ገመና የተሸከመው ሌላ ክልል አይደለም አማራ ብቻ ነው። በሥም የሚሰበከው ኢትዮጵያዊነት ሌላ ቦታ እንዲሰበክ አይፈለግም። ኢትዮጵያዊነት ግማዱን ለዘማናት ተሽኮ ለኖረው ማህበረሰብ ምጥ ለእናቷ አሰተማረች ሆኖ እዛ ላይ ነው መከራ ሲታይ የባጀው።

ለዴሞክራሲ ለውጥ እያደረግን ነው የሚለው የአብይ ካቢኔ በራሱ በሚመራው ድርጅት እንኳን አንዲት ራፊ መሬት ለህብረ ብሄር ነኝ ለሚል ድርጅት ቦታ የለውም። አማራ መሬት ግን ጫን ተደል መከራውን ቆልሎበታል። ይህም ብቻ አይደለም አክቲቢስት የሚባለው ሁሉ ተቀባይ እና ሸኝ ይኸው ክልል ነው።

ይህም ብቻ አይደለም የጎንደር፤ የጎጃም፤ የሽዋ፤ የወሎ ህብረትን ተሸካሚም ይኸው ክልል ነው። ስለምን ሁሉም የሚሠሩት ለአንድ ዓላማ ነው። አማራ የሚባል ማህበረሰብ አንገቱን አቀርቅሮ በባይታወርነት እንዲኖር ማድረግ እና ማስደረግ።

ይህን ለውጥ በጠንካራ ዝግጅት ያዋለደው አማራ ሆኖ ሳለ ሽልማቱን ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሰጡት ለግንቦት 7 ነበር። ብአዴንም ያን ሁሉ የተጋበትን ገድሉን አሳልፎ ሸልሟል። እያሸበሸበ። ዛሬ ይልቅ እስኪበቃው የግንቦት 7 ካድሬዎችን እና ሚዲያው እያስታጠቁት ነው ብአዴንን። ለምኖ እንዳይበላ አድርገው አራግፈውታል። የሚገርመው አማራ ለግንቦት 7 ቅኝ ተገዢነት የተሰጠ እስኪመስል ደረስ ... ግርም ይላል ቁጣው፤ ትእዛዙ ፍጥጫው ... ቆርሶ የሚያበላ፤ ቀዶ የሚያለብሰው ለ አማራ ህዝብ ግንቦት 7 እስኮመስል ድረስ... የሆነ ሆኖ ...  

ESAT Eletawi Part One Mon 25 Mar 2019

Published on Mar 25, 2019
ኢሣትም እንደሕወሓት ያደርገው ጀመርሳ! – አሊጋዝ ይመር (ከላኮሜልዛ)
March 26, 2019

የአማራ የህልውና የማንነትተጋድሎ የሚለውን ቃል የትኛውም ሚዲያ አያነሳትም። የትኛውም የፖለቲካ ሊሂቅ አይደፍራትም። ለምን ድሉ ታሪኩ አቅሙ ተፈሪ ስለሆነ ተቀብሮ እንዲቀር ይፈላገል። ለነገሩ አባቶቹ ባበጇት አገር ባይተዋር እኮ ነው … የለም የሚባል ማህበረሰብ።

ሰሞኑን እንኳን ብታዩት የኢሳት ጋዜጠኞች እዛ ነበሩ፤ ግንቦት 7 ማርቆስ ነበር፤ እንደ ገና ግንቦት 7 ባህርዳር ነበር። ባህርዳር ከተማ ላይ የሰላማዊ ነዋሪዎች ማፈናቀልም ነበር። በተጨማሪም ወሎ ላይ ደግሞ የወሎ ማህበር ምስረታ ነበር … በሌላ በኩል ጠ/ሚር አብይ አህመድ የብአዴንን አመራር አካላት በጫና ትግራይ ድረስ ሄደው ይቅርታ እንዲጠይቁ ወከባ እያደረጉባቸው ነው፤ በዛ ላይ ትግራይ እጬጌ የጦርነት ጉሰማ እያደረገ ነው፤ በሽዋ በኩልም ሌላ  የአማራ መፈናቀል ደርሶ ወደ መተሃራ ተፈናቃዮች እያመሩ ነው …

በሌላ በኩል 90 ሺህ ወገነን ተፈናቅሎ ጎንደር ላይ ሜዳ ላይ ነው፤ 44 ሺህ ልጆች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል በዚህ ላይ በ30 ሚሊዮን ዎቹ የሚገምት እርዳታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሌሎች ክልሎች ሲያደርግ ለአማራ ክልል 4 ሚሊዮን ብቻ ሰጠሁ ብሏል … እዬት ተመልከቱት … ግፉን
‹‹ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠውን ድጋፍ አልቀበልም፡፡›› የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው
March 24, 2019

ይህም ሆኖ ተወቃሽ ተነቃሽ አማራ ክልል ነው። ዓመት ያልሞላው ጮርቃ ህፃን አብን ረመጥ ላይ ነው ያለው። ይህን ድርጅት ከፖለቲካ ማዕቀፍ እንዲወጣ ነው ታስቦበት ታልሞበት በሚዲያ ድጋፍ ችግር ፈጠረ እዬተባለ እዬተቦካ እዬተገጋረ የሚገኘው። የዚህ ሁሉ መሪ ጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።

የወሎውም ታቅዶ ሆን ተብሎ የተከወነ ነው። ቀውስ እዬተመረተ ያለው በደቦ ነው። አማራ እልል እልል ብሎ ለአፍታም ከተጋድሎ  መዘናጋት እንደሌለበት በአጽህኖነት ሳስስብ የኖርኩት። ሁነኛ ባለቤት የለውም አማራ። ሁነኛ ወሳኝ አካል የ እኔ የሚለው የለውም አማራ። ባጎረሰ ሲነከስ ነው የኖረው። ስለዚህ ለራሱ ራሱ ለመሆን ወደ ራሱ ተመልሶ ስክነትን መጠጣት ይኖርበታል።

የአማራ ህዝብ ብስጭትን ዋጥ አድርጎ አሁን ድርጅት ስለላው አማራ አብን እሱን መጠራቅቅ ውስጥ የማያስገባ ጠንቃቀ ተግባራትን መፈጸም ግድ ይላል። ከህግ በላይ መሆን የተገባ አይደለም። ህግን ባከበረ መልኩ ስርዓትን በተከተለ መልኩ ሙያ በልብን ተግባራዊ ማድረግ ይገባዋል።

ሁሉም ነገር የተከወነው ታቅዶ ነው። የአማራን አቅም ቅስም ለመስበር ለማንከት ለማንኮላሸት። እንደገናም አዲሱን የብአዴን አማራር ሰላምንም ለማወክ። እፉኝት የትም ነው ያለው። የቻለ አቅም ያለው መንግሥት እመራለሁ ያለ እስኪ ትግራይ ላይ ሄዶ ቢሮ ከፍቶ ህዝብ ሰብስቦ ያነጋግር። ይቻላል? 

ራሱ የፌድራሉ ጠ/ሚር የትግራይን ህዝብ ሰብስቦ ማናገር አይቻልም። እነሱ ቆፍጠን ስላሉ አስተናግደው፤ አሳትፈው፤ እርድተው ወቃሽ ነቃሽ የለባቸውም።  ብአዴን ደግሞ ግርባነቱን አሁንም ቀጥሎበታል … ለሴራው ፓለቲካ የተገባ ፖለቲካዊ ማብራሪ መስጠት ሲገባ እንደዚህ ያለ ነፍሱን የሳተ ጭብጥን ያለገናዘበ ጉዳይ ይፈተፍታል … ራሱን በራሱ ለማጥፋት የሚጥር የመካራ ሌሊት  … ነው ብአዴን። ወዳጁን ጠላቱንም ሳይለይ ያገኜ ሲረግጠው እና ሲጠቀጥቀው ውሎ የሚያድር። 

·         ክወና።

ሌላው ግን ግጭት ለማንም አይጠቅምም። ጥያቄ ያለው አካል ጥያቄውን በአግባቡ ማቅረብ ይገባዋል። ስለምን ሰው ይጎዳል። ያ የሚጎዳው አካልም እኮ ወገን ነው። የሃሳብ ልዩነቱን ሥርዓት ባለው መልክ መግለጽ ሲቻል ወደ አመጻ ወደ ጉዳት የሚወስድ ነገር መቆም አለበት።

የመንግሥት ይሁን የግል ንብረቶችን ማቃጠልም የተገባ አይደለም። ዕዳ ውስጥ ለተዘፈቀች አገር ተጨማሪ ዕዳ መፍጠር የተገባ አይደለም። ስለምን የህዝብ ሃብት እና ንብረት ይጋያል። ስለምንስ ጉዳት ይደርስበታል። ነገ እኮ ትውልዱ የሚማረው በእነዚህ ቅርስ እና ውርስ ነው።

·         ተጨማሪ ምርኩዞች።

የግንቦት 7 ችግር ወደ አዲሱ ዉህድ ፓርቲ እንዳይሄድ ሌሎች ጥንቃቄ ያድርጉአበበ በለው
/ ብርሃኑ፤ ኦዲፒ እና አዴፓ (ሚኪይ አምሃራ)
February 15, 2019
ታቅዶ ስለመከወኑ በማስተዋል ይመርምር።


የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።