ይድረስ ለሹክሹታ አዘጋጅ ለትጉሁ ለጋዜጠኛ አቶ ሄኖክ አለማዬሁ ..

እንኳን ደህና መጡልኝ

ይድረስ ለሹክሹታ አዘጋጅ
ለትጉሁ ጋዜጠኛ 
ለአቶ ሄኖክ አለማዬሁ ..

„መሐላውን ቢያፈርሱ፤ ከሃጢያት ሥራ ወገንም ሁሉ ቢሠሩ ግን ጠላቶች ሆነው፤
በሰማይ ጽላት ይጽፋሉ፤ የሚጠፉ ሰዎች በሚጽፉበትም መጸሐፍ ይጻፋሉ፤
ከምድር ላይ ከሚጠፉ ሰዎችም ይቆጠራሉ።“
መጽሐፈ ኩፋሌ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፪

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26.03.2019
ከእመ ዝምታ።

ይድረስ ለሹክሹታ አዘጋጅ ለጋዜጠኛ አቶ ሄኖክ አለማዬሁ ...

Shukshukta (ሹክሹክታ) - የቤተመንግስቱ ምስጢራዊ ጉባዔ | TPLF | Dr Abiy Ahmed | ADP





እንዴት ነህ እናትዬ? ደህና ነህ ወይ? ትናንት ነው ይህችን ፍሬ ነገር ከልቤ ያዳመጥኩት። እናልህ እንዲያው ለአቤቶ ብአዴን ትጠይቅልኝ ዘንድ ይህችን ኮለምኩልህ። ሥራ እንደሚበዛብህ ግን አውቃለሁኝ። እና ትንሽ ላስቸግርህ አሰብኩኝ … ዛሬ ቪንቲ ፏ ብላለች… እቴጌ መነን ከች ገና በማለዳው>>

·       ወደ ጉዳያችን …

ሹክሹክታ ቅንብሩ ተፍሬ ነገሩ ልብን ይገዛል። እስቲ ጠይቅልኝ የእኔ እናት ዶር አንባቸው መኮነን እንዴት ነው የዘር ማፍረያቸው የተነቀለውን ምንዱባን ከልዑኩ ቡድን ጋር አብረው ተዝርዝሩ አስገበተው ከሆነ ጠይቅልኝ?

 ከዛ በግፍ ከነነደው የቅዳሜ ገበያ ብትን አፈርም ለ አቤቱታ … ለተማለዱን …  ከተነቀለው ጥፍርስ ከቶ ቤተኛ ይሆን ለምህረት ልመናው?

44ሺህ ልጆች ከትምህርት ገባታቸው እንደተፈናቀሉ ሰምተናል የእነሱስ ውክል አካል ይኖር ይሆን? "መብቴን እጠይቃለሁ ግዴታዬን እወጣለሁ ላይ" ልጆች እንደተወከሉት ማለት ነው፤ ሌላም አለኝ 90ሺህ ተፈናቃዮችስ ውክል አካል አብሮ ይሄድ ይሆን ያቺው እራፊውን ከአንገቱ ላይ አድርጎ?

ሌላም አለኝ የጎንደር እናቶች 44 ዓመት ዕንባስ በማንቆርቆሪያ? ወይንስ በኮዳ ወይንስ በቸረቸራ በዬትኛው ይዘው ለመሄድ እንዳሰቡ ሹክ ብትለኝ የማከብርህ? እርግጥ ነው በቸረቸራ ከሆነ ሟተት ማሰራት ሊኖርበት ነው የኦዴፓ ሥም ወራሹ ብአዴን?

ሌላም አለኝ ድንጋይ ተሸከምው ለመሄድስ የላስታ አለትን እንዲህ ከወደ ወሎ አስምጥተው ከተጓዦች ዝርዝር አስገብተውት ይሆን? እናቱ ወደ ዶር አንባቸው መኮነን ስልኳን ቃጨል አደርግና እባክህን ጠይቅልኝ?

አልጨርስኩኝም ... ሌላም ለዶር አረጋይ በርሄ የጠ/ሚሩ አማካሪ ለሆኑት አቶ ጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ያዘጋጁት መዳሊያ ካለም እሱንም እንዲህ ወደ አዲስዬ ቀጨል አድርግ እና እስኪ አንድ ለመንገድ ደግሞ በለን አባትዬ?

ለኦነግ የዲሞግራፊ ለውጥ ሲባል ጥቃትን ተንተርሶ በመተኛት ስንት ኪሎ እንቅልፍ ብአዴን ግርባውም እንዳስመዘገብም እሱንም ... ፈተሽተሽ አድርገህ የሚሉትን ሹክ በለን

… አዬ ደብርዬ ወንዱ ያስረገርገዋል ... ከፓትርያክ እስከ እጬጌ ከሊቅ እስከ ደቂቅ... የወንዶች ቁንጮ ... ራሱን አስከብሮ ያለ፤ ... ከፋም ለማም

የጋሞ የጌድኦ መከራ ያው ፍደኛው አማርኛ ተናገራችሁ ነው አይደል? የኦሾቲዝ መከራ ተሸካሚ ያደረጋቸው፤ እናማ እናማልህ እጬጌው ተፈሪው አማርኛንስ ሳጥን አሰርተውለት ይሆን እነ አቤቶ ብአዴኖች? እሱንም አደራ እንዳትረሳ... ለነገሩ አቶ ገዱ ቆመስ እንደሆኑ ሰምተነዋል …   

በተረፈ ... ኑርልኝ የእኔ ጌታ ፈጣኑ ሁለገቡ ጋዜጠኛ አቶ ሄኖክ አለማዬሁ ... እም! እኔን ይርሳኝ ተዘንግቶኝ … የተረሳ ብልህነት ደግሞ አለኝ… የዓመቱን የአዲሱን ካቢኔ ጫን ተደል ተጫኙ የግርባው ብአዴን ደንደስስ ደክሞት ከሆነ ድንገት ካቴና ለእረፍት እንደ ሃኒ ሙን ተዘጋጅቶለት ይሆን? "የጣና ኬኛ ሽልማትን" እያዳመጥን ስለሆነ … እንዳለ አመራሩ ይከዘን ከሆነ ከጃዋርውያኑ ከ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በመለስ …


ኦዴፓዎች አዴፓዎችን ማሰር ጀምረዋልሰለሞን ቦጋለ ኑርልን ለእኛም ለአላዛሯ ኢትዮጵያም ...
ውጡልንና ዛቻ  በአሰላ ከተማ እየተሰማ እንደሆነ ተዘገበ 
March 26, 2019

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሽንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
ሰላም የዘረፉትን በመመለስ ብቻ ነው የሚመጣው!
ሰላም በጫና በአድሎ አይገኝም!
የህሊና ሽፍትነትን ፕሮፓጋንዳ አይመክተውም!

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።