ድንግል ሆይ! ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ጠብቂልን! አደራ!


እንኳን ደህና መጡልኝ
ድንግል ሆይ!
ጋዜጠኛ አበበ ገላውን
 ጠብቂልን! አደራ!
„ኃጢያትን ተዋት እደ ልቦናህ አቅና፤
ልቦናህንም ከኃጢያት ሁሉ አንፃ“
ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፭
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26.03.2019
ከእመ ዝምታ።

ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? የማይሰማ ነገር የለም። ሌላ ሰው ቢናገረው ምንም አይደንቀኝም። 

አቶ ኤርምያስ ለገሰ በጸሐፊነትም፤ በም/ሚር ማዕረግም፤ በድርጅት አባልነትም የበቃ ተመክሮ ያለው ሰው ነው። መምህርም ነው። መምህር ሰብዕናው ለሁሉም አባትነት ይመስለኛል። አቨይ አባቴ እንደዛ ነበር።

ነገር ግን ይህ ነገር ያዳመጥኩት አመክንዮ እሱን የሚገልጥ አልመስል አለኝ። ጋዜጠኛ አበበ ገላውን አሳልፎ የሚያሰጥ መረጃ ሜዳ ላይ ዘክዝኮታል። ዘርግፎታል። ሞትም ፈርዶበታል ያ ጥቃት ያወጣ ጋዜጠና። እጅግ ያስደነግጣል። 

እንዴት ጓዱን አሳልፎ ይስጣል። ለዛውም በዚህ ቋያ ጊዜ። የኃይል አሰላለፉ ባልጠራበት ወቅት። ጓድን፤ ክፉ ደጉን አብሮ አሳልፎ፤ ጥቃትን ላወጣ ወንድም እንዴት በአደባባይ ሞት እንዲፈረድበት ይደረጋል። እያንዳንዱ ሰው እኮ ለራሱ ሰብዕና ጠንቃቃ ነው። ለዛውም ጠ/ሚር አብይ አህመድ አሁን እደማያቸው ከሆነ አይደለም ሰብዕናቸውን የሚንድ ትችትን እንኳን ለማስተናገድ የሚፈቅዱ አልሆነም። ጫን ያለ መከራ ከፊታችን ተደቅኗል። እንኳንስ ይህ በጠቅላላ በሥልጣናቸው የመጣ ጉዳይ ... 

ESAT Eletawi Part Two Mon 25 Mar 2019 1

ለመሆኑ ትውልድ የማይተካው ያ ትንታግ የጀግኖች ቁንጮ አንበሳ፤ የወንዶች ቀንዲል አሁን ጋዜጠኛ አበበ ገላው የት ይሆን ያለው?ጭንቅ ብሎኛል። ውጭ አገር አሜሪካ ከኖረ ምንም አይደለም የመረጃው ፍንጭ ቢወጣ።

ይህም ቢሆን ከዛ ላለው አገር ውስጥ ለሚገኘው የግንቦት 7 ሚዲያ ኢሳት እና ከፍተኛ አመራር አካሉ እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው። ሚዲያዎች ደግሞ እያረገቡት ነው። የ ጠ/ሚሩ ገበና ተዘረገፈ እዬተባል።፡በቀጣይ ቀናት ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም። ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው እንዲህ አይነት መዝረክረክ? ለመበቀል ይሆን?

Ethiopia: ጋዜጠኛ አበበ ገላው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮችን አጋለጠ | Abebe Gellaw on Arbegnoch Ginbot 7 Leaders

Published on Mar 19, 2019

ከቶ ኢሳት ሚዲያው አዲስ አበባ ላይ ቢዘጋ ምን ትጠቃማለችሁ? አቤስ አንድ ነፍስ ነው ያለው። ያን ጀግንነት ሲፈጽሞ ቆርጦ ወስኖ ነው በህይወቱ። እኔ ሳዬው ስለ ህይወቱ ጭንቅ ስለሌለው እዬሄደ ነው እንደ እኔ የሚቀረቀረው። የግንባር ስጋ ነው።

የሆነ ሆኖ  ዛሬ እምናቆለብሰው የለውጥ ሃይል፤ ቄሮ፤ የአማራ ታገድሎ እንኳን ውሹን ያወሳ ውግዝ ከአርዮስ ተብሏል ተሸፍኖ ነው ያለው። ብቻ የሁሉም መሠረት ነው ያ  የቀደምቶቹ ልጅ የጀግና አበበ ገላው ጀግነንት ነው የሁሉንም ልብ ያበረታው።

 ይህን መረጃ እንዲህ እንደ ቄጠሜ በእልህ እና በቁጣ ሲዘረዘር በአደባባይ ገድላችሁ አሳዩን ነውን? … ስለምን ትጨካከናለችሁ? ሙያ እኮ ታላቅ ቃልኪዳን ነው። ጓዳችሁ እኮ ነው ጋዜጠኛ አበበ ገላው።

አሁን እኔ እሞግታቸሁአለሁኝ። ስለነፍሳችሁ ግን ይጨንቀኛል - በጣም። ለዚህ ነው ከቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት በኋዋላ ግንቦት 7ም ኢሳትም አገር ባትገቡ ይሻላል ያልኩት …

መረጃ እንዲህ ሜዳ ላይ አይዘከዘክም። ይህ እኮ ከባድ አገረዊ ብሄራዊ ጉዳይ ነው። ሆድ እኮ ብዙ  ይችላል። ያለቦታው ያለግዜው። ለነገሩ አቶ አሰፋ ጫቦ እኮ ካለወቅቱ መረጃ አወጣለሁ ብለው ነበር ሞት የተፈረደባቸው። የጋዜጠኛ ሙሉጌታ ህልፈትም በዚህው ማዕቀፍ ውስጥ የሚታይ ነው።

እናንተ ያላችሁ ዲስ ላይ ነው። ሌሎች ጓዶቻችሁ ደግሞ ኢትዮጵያ ላይ ናቸው። ቀድሞ ነገር የደህንነት ሰራተኛ ሲኮን መደበኛ ሥራ ነው። ሙያ ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ ተፈልጎ አይደለም ዩንቨርስቲ የሚመደበው። ዕድል ጉዳይ ነው ሙያ የሚጠናው።

የግንቦት 7 እና የሚዲያው የልብ ምት መሰረት የኤርትራ መንግሥት ነው። የኤርትራ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ሙያቸው ይኸው ነው። ኢትዮጵያን ባለ በሌለ ኃይላቸው ሲሰልሏት ነው የኖሩት። ሙያቸው ነዋ!

ከኤርትራ ጋር የሠራ ድርጅት እና ሚዲያ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለመንግሥታቸው እና ለድርጅታቸው ታማኝ መሆን የሚደንቅ አይሆንም። እንጀራቸው ነው። ሙያቸው ነው። ድርጅታቸው ኢህዴግ መንግሥታቸውም ሲኖር ነው ነውና ህይወታቸው የሚኖረው። በዬዘመኑ ባለው ሥርዓት መሥራት ደግሞ ግድ ነው።


80ሺህ ህዝብ ልሰደድ ቢል እንዴት ይችላል? ጫካ ልግባስ ቢል ይቻለዋልን? ስለዚህ ኑሮውን ለማሸነፍ የግድ ነው በሥርዓቱ ውስጥ ዕድል በሰጠው ቦታ መስራት። ሁላችሁም ነበራችሁበት። ያ ደግሞ ወንጀል አይደለም።

በሌላ በኩል አሜሪካን አገር ኢሳትም ሆነ ጋዜጠኛ አቶ ኤርምያስን ጨምሮ ነፍሳቸው ተረጋግቶ፤ የመኖር ዋስትናቸው ተጥብቆ የሚኖረው ይኸው ሙያ በሚሰራው ጥብቅ ተግባር ነው። ዓለም ራሷ ሚዛኗን ጠብቃ ያለችው በዚኸው በዬአገሩ ባሉ መሰል የደህንነት ተቋማት ነው። በሲአይኤ፤ በሞሳድ፤ በኬጂቢ … ወዘተ …

ስሊዚህ የህውሃት ሥርዕዎ መንግሥት እስትንፋስ የነበረው ኢንሳ ጠላቴ ባላቸው ድርጅቶች፤ ሚዲያዎች፤ ግለሰቦች የቻለውን ያህል መታገሉ ሌላውም ዕድሉን ቢያገኝ የሚያደርገው ነው።

ሥርጉተ ምን ኑሯት ነው ከብዕር በስተቀር ድርጅታችሁ ግንቦት 7 ሲያሳድደኝ የኖረው። ቅብር ብን ብዬ እንደጠፋ በትጋት ሲሳራበት የነበረው ስለምን ነው? ተቸችን አይደለም ወይ? ስንቱ ሊሂቅ ነበር በጎሪጥ የሚታዬው ሰብዕናው ታፍልሶ ማህበራዊ ህይወቱ ታውኩ በዘመቻ ሲገለል የነበረው። ሁሉም ደርሶታል። አሁንም እዬደረሰው ነው።

በሌላ በኩል የህወሃትም ካድሬዎቹ ሰላሜን ሲያውኩት የኖሩት ምን ጠበንጃ፤ መድፍ፤ መትረዬስ ኑሮኝ ነውን? ኮንፒተሬ ሁሉ ሃክ ተደርጎ ነበር።

አሁን ደፍሬ ሰውም አምኜ ከሰው ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ማድረግ አልችልም። ግን ይህን ስላደረገ የህወሃት ሥርዕወ መንግሥት አማራጭ በጠፋበት ጊዜ አንድ የተስፋ አማራጭ ሲፈጠር ያን ደግፌ ወጥቻለሁኝ። እስር ቤትን ነበርኩኝ - እኔ። አውቀዋለሁኝ መከራውንም የስለላ ድርጅታቸው የሚሰራውን።

ነገር ግን የተሻለ ነገር ሲመጣ ደግሞ አማራጩን እንጠቀምበት ዘንድ ተግቻለሁኝ። በርካታ መልካም ነገሮችም ተገኝቶበታል በዛ ለውጥ። አሁን ያለው ትርምስ የራሱ የሆኑ ፖለቲካዊ ዕድምታዎች አሉበት። ሁሉም አላረፈለተም። ቀዳዳ ሲገኝም ያው ማነኮር ነው እንኳንስ እንዲህ ያፈጠጠ ነገር መጥቶ ... 

እኔ አቋሜ የነበረው ሥር ነቀል ለውጥ ነበር። በጣም ጠንካራ አቋም ነው የነበረኝ። ግን በእጅ ያለው ነገር መርምሬ ከደረስኩበት በኋዋላ በዕድሉ መጠቀም የተገባ ስለሆነ ስላመንኩበት ሞግቻለሁኝ። ጥገናዊ ለውጡ ከሆነበት ዕለት ጀምሮ ግን ድክመት ያልኩትን የስታመምኩበት፤ ያለፈኩት የለም በእያንዳንዱ ጉዳይ የሰላ ወቃሰዬን በጥዋቱ ነው የጀመርኩት።

ግንቦት 7 ቀንቶት አገር ቢገዛ ያው መሰሉን ይፈጽማል ደህንነት አልባ መንግሥትነትን አይረከብም እና። ውጭ አገርም አብሶ ለንደን ላይ እርሾ ሳይኖረውም አይቀርም። መንግሥት እሆናለሁ ምኞታም ስለነበር።

ግንቦት 7 እራሱ እኔን ሲያሳድድ ብዕሬን ሲያሳፍን አይደለም ወይ የኖረው? ሊሂቃን ሲያስገልል ማህበራዊ መሰረታቸው ሲያነኩት አይደለም ወይ የኖረውን? አሁንስ አብን በሚመለከት ምን እያደረገ ነው? ሌላውን ተከድኖ … ሁሉም ለራሱ ኢጎ ነው የሚሠራው። ለህዝብ እማ ታዬ እኮ …

ግንቦት 7 ገዢ ቢሆን ደግሞ የዘመዶቼን ዕጣ ፈንታ አገኛት ነበር። እስኪ ይንገሩን እነሱ ተፎካካሪ ሃሳብ አስተናግደው ከነበረ? አንድም ቀን ስለ ግንቦት 7 የወቀሰ ነገር አቅርበው ያውቃሉን? ጽፈው ያውቃሉን? አንድ ጊዜ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ደፍሮ ወጥቶ ነበር በወልድያ ጉዳይ። ከዚህ በስተቀር መላዕክታኑን መንካት ያው እንጦርጦስ የሚያስበይን መከራ ነው።  ኤርትራ ላይ የነበረውን ደግሞ በጥሞና ተከታትለነዋል። ከሥር ለጥፌዋለሁኝ። 

እስኪ ስለ ሰብዕዊ መብት ያውም ስለ ጓዶቻቸው ይጨንቃቸው ከሆነ ኢሳቶች ይህን ይመርምሩት። የሰው የክት እና የዘወትር የለውም። ዛሬም ባህርዳር ላይ ድርጅታቸውን የሞገቱት እነዚኸው አርበኞች ናቸው። ከዚህ እንደተለመደው መከራቸውን እንዳይናገሩ ስለታፈኑ … ለሰው ልጅ ይጨንቃቸው ሌላው ስለጎዳው አንደሚታገሉት።

Ketarik Mahder - አርበኞች ግንቦት ኤርትራ ውስጥ ነው መከፋፈል የጀመረው ሲል የግንባሩ ወታደር ተናገረ።- NAHOO TV
Published on Jan 1, 2019
Ketarik Mahder - አርበኞች ግንቦት ኤርትራ ውስጥ ነው መከፋፈል የጀመረው ሲል የግንባሩ ወታደር ተናገረ።- NAHOO TV
Published on Dec 31, 2018
Ketarik Mahder -"አትዮጲያ የገቡ አትዮጲያ የገቡ የአርነኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች በድርጅታቸዉ ተማረዋል!" ክፍል 1-NAHOO TV
Published on Dec 31, 2018

Ketarik Mahder - የአርበኞች ግንቦት ሰባት የቀድሞ ወታደሮች 'የትም ተጥለናል' አሉ።- NAHOO TV

Published on Jan 1, 2019


ይኸው ይህን እስኪ ደፍረው ድርጅታቸውን ያፋጥጡት። የአቶ ነአምን ዘለቀን ከድርጅቱ መልቀቅ እንኳን በቂ ሽፍን ለመስጠት ፈቃዱ የለም። ሌላውም እንዲሁ ነው
የሆነ ሆኖ ለጋዜጠኛ አበበ ገላው ሞት ነው ድርጅቱ ኢሳት የፈረደበት። እንደ እኔ ከሰሞናቱ በጫራት ጭብጥ ይመስለኛል። እንዲህ አለመተዛዘን የተገባ አይደለም። 

የፈለገ ቢያስቀይመኝ ብከፋበትም በግንቦት 7 በድርጅቱ አመራር አካላት አንዲት ነገር እንድትደርስባቸው አልፈልግም። ስለምን? ወገኖቼ ናቸው። ስጋዎቼ ናቸው። አንድ ቀን ደግሞ ዙረን እንገናኛልን፤ ባንገናኝም ባሉበት ጤናቸውን ይስጥ መዳህኒተ - ዓለም።

ኢሳት ቢያውቀው፤ የግንቦት 7 ደጋፊ እና አድናቂ ቢረዳው ለዚህ ሁሉ ለዛሬው ቀን ያበቃው ገናና የአቤ ተጋድሎ ነው። ራሱ /ሚር አብይ አህመድን /ሚር ያስደረገ፤ ዶር ደብረ ጽዮንን እጬጌ ያደረገው ደፋሩ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ነው። አጅሬ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ቢኖሩ ይህን መሰል መቀናጣት ህልም ነበር የሚሆነው።

ዛሬ ሁሉ ተረስቶ ያን ልክ ያልተሰራለትን ጀግና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲብጠለጠል አዳምጣለሁም። መነሻን ማወቅ ያስፈልጋል። እራሱ ኢሳት ነፍስ የሰራው እኮ በእሱ ሞገዳማ ድምጽ ነበር። የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የማስደንገጥ ተግባር ሲከውን በዛች ዕለት ብቻ ስንት ሰው የኢሳት አባል እንደሆነ ጓደኞቼ ስላሉበት አውቃለሁኝ። 

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲታሰሩም ተስፋ ለሽ ብሎ ሲተኛ እኔ አለሁኝ ብሎ ጥቃት ያወጣ ጀግና ነው አቤዋ።

አሁን ደግሞ ለበላኃሰብ ተላልፎ የተሰጠ መከረኛ። እንዴት በሚስጢር የተያዘን ሉዕላዊ ጉዳይ እንዲህ ሜዳ ላይ ላይ ይዘረገፋል። አሁን /ሚር አብይን ለማጋለጥ እኮ ሌላ ነገር አስፈላጊም አይደለም። አጃቢ ነገር አያስፈልግም።

ራሳቸው በራሳቸው እዬሳሱ ስለሆነ። ራሳቸውን በራሳቸው ሰብዕናቸውን እዬሸረሸሩት ስለሆነይህ ደግሞ በድርጅታቸው በኦዴፓ ብቻ ሳይሆን ከጎናቸው እንደ ፍቅረኛ የሸጎጧቸው ባለተመክሮ የተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ ድርጅት ሊቀመናብርት ናቸው ውስጣቸውን ገዝግዘው መለመላቸውን እንዲቀር ያደረጉት። ተቡርቡረዋል። 
  
እና ሌላ ጉርጉንጉር፤ ሩቅ የሚያስኬድ ነገር የለም። ምክንያቱም ከኢትዮጵያ በላይ ማንም ምንም ስሌለ። ድሮም ሰፍ ብለን የወደድናቸው ኢትዮጵያ ስላሉ ነው። አሁን ደግሞ ስትፈርስ ዝም አንልም።

ሁሉም የተሞገተበት በልብ ሽፍትነት ምክንያታዊ ጉዳይ ነው። ስለ አገር ሲሶ ፍቅር ሊኖር ስለማይገባ። ኢትዮጵያን በእርቦ እና በሲሶ አፍቅሮተ ሆኖ አይሆንም። ምነው ግንቦት 7 ከኦነጋውያን ከኡጋዴ ነፃ አውጭ ድርጅት ጋር ተደራድሮ አልነበረም ወይ? ምን አዲስ ነገር አለው የአሁኑ የኦዴፓ አቋም? እስከ ዘር ቆጠራ ተሂዶ የኦሮም ደምነትም + ጉራጌነት ብራስልስ ላይ አዳምጠናል … በራስ ሲሆን አበባ በሌላ ሲሆን ጥቅርሻ አያምርም …





ሌላው የመረጃ አያያዝ እና ወቅት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የሚያስከትለውን አደጋም ማሰብ የተገባ ነው። በቀል ደግሞ ጥሩ አይደለም። ያን እኮ እንርሳው ተባብለናል። ያን ብናስታውሰውማ ቀድሞ ነገር እኮ ይህም እንዲህ ያም እንዲያ አይሆንም ነበር። ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ መንፈስ ጋር ያልተለካለከ የለም። ያም መብት ነው። ከኦነጋውያን ጋር ያልተለካለከ የለም። ያም መብት ነው።




በተጨማሪም ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ከስሜታዊነት መውጣት  በእጅጉ ያስፍልጋል።  አገር የደቦ ጨርቅ አይደለችም እና። አገር ከሃሳብ በላይ ናት። አሁን እንኳን ዘለንበት ንፈሱም፤ ቅጠሉም፤ እሳሩም ዘላይ ሆኗል። እና ተግ እንበል። የተበሳጨ አዬር ነው ያለው። በዚህ በጠ/ሚሩ አብይ አህመድ ላይ ይህ መረጃ ምን እና ምን ሊሆን እንደሚችል መዳህኒዓለም እንደ ጥበቡ ይፍታው። 

ወቃሽም ከመሆን በፊት ምን አለኝ ብሎ ማሰብ ይገባል። ምን አለኝም ብቻ አይደለም እኔስ ምን አድርጌ አውቃለሁ ማለት ይገባል። ሁሉም በዬጓዳው ለተቆለለው ኢጎ ሲከስም፤ ሲገፋ፤ ሲነቀል፤ ሲያስወግዝ ነው የኖረው፤ የትውልዱ ብክነትም ምኑ ተሰልቶ ... 

አሁን ላለው መከራስ ማን አስተዋፆ አድርጓል ብሎ በጥልቀት መመርምር ይገባል። ሩቅ ሳይኬድ ይህ ለውጥ እንዲደናቀፍ፤ ግርግር እንዲፈጠር ወዘተ …  ብዙ ነገሮች ተከውነውበታል። ቅንነት አይሸመት ነገር? የስልጣን ሱስ በሽተኛ ነው የሚያደርገው። ሥልጣነ አፍቅሮት መዳህኒትም የለውም። 

ወሳኝ በሆነው አገራዊ ጥያቄ ላይ፤ በእጅ በሌለ መንፈስ ይህን ያህል መፎግላትም የተገባ አይደለም። ያለፈረሰ የለም። ስለምን? በመኖር ውስጥ ያልነበረ ቀድሞውን የፈረሰ ነውና።
ሚዲያ ሚደያ እንጂ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም … ሚዲያ ደግሞ ማዕከሉ ሰው ነው … የነፍሱም ማስኬጃ ደግሞ ዕውነት ነው … አቅሙ ከኖረ አገር ስላለው ምስቅልቅል ይህን ከልባችሁ ሆናቸሁ መርምሩት … አቶ ሚኪ አማራም፤ ፎርቹን ጋዜጣም ዘግቦታል … ማን ከማን ጋር የኃይል አሰላለፍ እንዳለው። ነገ ደግሞ ጊዜ ደግሞ እያረገፈ ጥራት ያለውን አቅም ለገብያ ያቀርባል …

/ ብርሃኑ፤ ኦዲፒ እና አዴፓ (ሚኪይ አምሃራ)

ድንግል ሆይ አቤን ጠብቂልን!
ድንግል ሆይ ስለ አቤ ቸር ወሬ አሰሚኝ!

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሽንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።