የጉልበት ገለባ።
እንኳን ደህና መጡልኝ
„መሐላውን ቢያፈርሱ፤ ከሃጢያት ሥራ ወገንም ሁሉ ቢሠሩ ግን ጠላቶች ሆነው፤
በሰማይ ጽላት ይጽፋሉ፤ የሚጠፉ ሰዎች በሚጽፉበትም መጸሐፍ ይጻፋሉ፤
ከምድር ላይ ከሚጠፉ ሰዎችም ይቆጠራሉ።“ መጽሐፈ ኩፋሌ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26.03.2019
ከእመ ዝምታ።
የጉልበት ገለባ።
የጉልበት ገለባ
የዋልካ ዘለባ
የስጋት ዘንባባ
የሜንጫ ወለባ
ልዑሉ አለሜ ከዬትስ ተነስቶ ከማንስ ተገባ?
ጮማ ጮማ ወሬን ስለሰው ከርሜ
በሐሴትም ስከር ስዘምን ከርሜ …
መታረም ታወጀ ከዘመን ዘማሜ።
የወንዶቹ ቁንጮ ንዋይ ከግርማሜ
ጥራኝ በመንፈስህ የቁርጥ ቀን ደሜ!
እንዲህ ወደ ጦቢያ ዓለም ተጨነቀ
እንዲህ ወደ ዕንባዬ ጉንጬ ተደነቀ
ተስፋ በሞት አፋፍ እዬተቀደደ።
በነዶበነዶበነዶበነዶበነዶበነዶበነዶ በነዶበነዶ ….
በሜትርም ሳይሆን በዝልቅ ተበይዶ
ወይ ነዶ ወይ ነዶ!
ተስፋ ሆይ! በቦንዳበቦንዳበቦንዳበቦንዳበቦንዳበቦንዳ
ንዳድ ተነዳ ንዴትም ተንዳ…
ጣራተንገዳግዶ ጅብገደል በዘንዶ
በተርታ በተርታ በሲቃ ተነዳ
ነፍስ ተቀርድዳ
መንፈስ ተወርድዳ
የስሜት ስቅነት ታርሶ በዘንጋዳ
የተስፋ ቁሪንጣ እንዲህ በከርዳዳ …
ሱቅ ከፍቶ ሲያደባ፤ ሲያማትር ሲያደባሲያደባሲያደባ
ኬኛኬኛ ብለን ሆድም እንዳይባባ ….
አባባ አባባ የአባት ሆድ በዳባ
ቤተኛ ርስተኛ የውስጥ ቁርሾእርሾ እንዲህ በገደማ።
ገዳሜገዳሜገዳሜገዳሜገዳሜገዳሜ ገዳሜገዳሜ
ዳገት ገደምዳሜ …
… የታሬ የቁንጮ የወይራ ጎልማሜ
ዝልቦዬን ታቅፌ ሆኛለሁ ገርዳሜ።
ቅንነት ተምንስ ተማንስ ተጋብቶ?
ታማኝነት ቢሆን በስስ በወረራ ደርቆ
ሂድልኝ ጠበቀ ቃልም ተፈቅፍቆ።
ክህደት ድንኳን ሰርቶ ቤቱን አሳምሮ
መጪታ ግሪደር ከአራስ ቤቱን ሰርቶ
ታረሰች አገሬ ሽብሩ ጎምርቶ።
ስጋት ቤት ሰራብኝ እንደ ትናንትናው
ማለፊያ የሌለው ጠፍቶበት ሁነኛው።
ብጠራው ብጣራው አጥሪና አጣሪ አቤት ባዩ አቶ
እባባማ ዞማው በሠርገኛው አምሮ
ሰልፉን አሳምሮ በመቶበመቶበመቶበመቶበመቶ
አገር ገዛ አሉ የበሰጨኝ ሽቶ።
ኦዴፓዎች አዴፓዎችን ማሰር ጀምረዋል – ሰለሞን ቦጋለ
March 26, 2019
ውጡልንና ዛቻ በአሰላ ከተማ እየተሰማ እንደሆነ ተዘገበ
March 26, 2019
· ሥጦታ ለግራሞት። 26.03.2019 ሲዊዝሻ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ