#ኢትዮጵያ እንዲህም ናት። #መምህር ናትና።
https://www.youtube.com/watch?v=Xm14vSdXkLc&t=216s
እሙኃይ አለምነሽ እና ልጃቸው ወጣት ዕፀገነት ብርሃኔ። #ፈጣሪ በፈጠረው የእናት እና የልጅ ፍቅር፣
#ፈጣሪ በፈጠረው ፍጹም ታማኝነት ልክ።
#ፈጣሪ በፈጠረው መከራን ታግሶ የማሳለፍ ልክ።
#ፈጣሪ በፈጠረው ልክ የጊዜ ቁምነገር የተረጎመበት መክሊት።
#ፈጣሪ በፈጠረው ልክ የጋብቻን በኽረ ተፈጥሯዊ ህግ በመፈጸም ………
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ። "
ክፍል ሁለት ላይ ዕፂ ዘማሪ ለመሆን ወስናለች። በሌላ በኩል "እንኳንም ኢትዮጵያ ተወለድኩኝ። እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንኩኝ።" የሚል ኃይለ ቃል ተናግራለች።
ኢትዮጵያ እንዲህ ናት። ወንጌሉ እንደሚለው በአንድም፣ በሌላም ታስተምራለች። #ወደ 5ሺህ የሚሆን ስልክ ተደውሎላት ከኢትዮጵውያን እና ከኤርትራውያን፣ ችላ ያነሳችው #ሥማቸውንም የመዘገበችው ከ1500 በላይ ነው።
ስለወላጅ አባቷ ሥም ሆነ ክስ በብዙ አድማጭ ብትጠየቅም፣ "ቤተሰቡን አልረብሽም። እህት እና ወንድሞቼን አልረብሽም። እነሱ እንደ ሌላው ሰው ሊያደምጡት፣ አብረውን #ሊያለቅሱ ይችሉ ይሆናል። እኔም #አባቴ ሥም አልጠራም። በፍርድ ቤት አሳውቄ አስወስኛለሁኝ። በእናቴ አባት ሥም ነው የምጠራው። " በጣም የደነቀኝ የመወሰን አቅም።
"እና ሳላውቀው ይቅርታ ላደርግለት አልችልም። መጥቶ ይቅርታ ከጠየቀኝ፣ ይቅርታ አደርግለታለሁኝ። አባትነቱ ግን የለም። ልጅነቱም #የለም" ብላለች።
እነማን በብልህነት ማሰብ እንዳለባችሁ ታውቁታላችሁ። ለድንኳን ኑሮ አንድም ሲበዛ ነው፣ እንኳን የክት እና የዘወትር። ነውር ነው። ፈጣሪም ይከፋል።
ተዘርዝሮ የማያልቅ የሴት ልጅ መከራ አለ። እራስን ገዝቶ፣ ስሜትን ተቆጣጥሮ፣ በተሰጠው ልክ መኖር ምኑ ይሆን የሚያቅተው።
ሥርጉትሻ 28/05/026.
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ