ይድረስ ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን። ኢትዮጵያ - አዲስ አበባ።

 

ይድረስ ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን።
ኢትዮጵያ - አዲስ አበባ።
"እግዚአብሄር በአንድም
በሌላም ይናገራል
ሰው ግን አያስተውለውም"
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማን እና ስለማን ይሆን የተቋቋመው???#ስለአለቅትነት ይሆን??? አነሳችሁብኝ። እንደምን ሙሁራን ለሚያቀርቡትገንቢዕይታ ዕውቅና መስጠት ተሳናችሁ???? #ቁስለት!
የተከበሩ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ከአደባባይ ሚዲያ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በጥሞና ለአራት ጊዜ ያህል አዳመጥኩት። አምስተኛውም ለአዲሱ ዓመት ተቀጥሯል። አይጠገብም። ተቋም ነው። የአወያዩ የአቶ አቤል ጋሹ የአጠያዬቅ ዘዬም ለፕሮፌሰር ሚንጋ ሜጋ አቅም ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ አግኝቼዋለሁኝ። በዚህ ዓመት በመቆጠብካዳመጥኳቸው ቃለ ምልልሶች ቀንዲሉ ሆኖልኛል ለእኔ። የኢትዮጵያን ክብረት እና አዱኛም ፏ ብሎ ያዬሁበት አጋጣሚ ነበር ማለት እችላለሁኝ። መስጦኛል። ተደምሜበታለሁኝ። ውስጤንም አግኝቸበታለሁኝ። ፕሮፖጋንዲስት ለማያስፈልገን ኢትዮጵያዊ ዜጎች ልካችን አግኝተናል ብዬ አስባለሁኝ። ለዚህም ነው እኔ ኢትዮጵያን በተፈጥሯዋ ልክ ያነበቡ፤ የተረጎሙ እና ያመሳጠሩ ከሳይለንት ማጆሪቲ ውስጥ ያሉ በቲም ፈላስፊቷን አገሬን ይመሩ ዘንድ ዕድሉን እንዲያገኙ እምመኜውም።
ፌስ ቡኬ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ሼር የማደርገው። ባሉኝ ሁሉ ሚዲያወቼም ብሎጌን ጨምሮ ሼር አድርጌዋለሁኝ። ከማህበራዊ ሚዲያ ርቀው ለሚኖሩ ወገኖቼም ሼር አድርጌዋለሁኝ። የጠራ አቅጣጫ ያለው ብቻ ሳይሆን አብዝቶ ቅንነትን ማዕረጉ ያደረገ መሰጠትን ስለአገኜሁበት። የጨመተ እና የሰከነ፤ እላፊ ያልሄደ ጠፈፍ ያለ የእኛነት የኔታነትን አይቸበታለሁኝ። መስታውትም ራዲዮሎጂም ማለት እችላለሁኝ። በፍፁም ሁኔታ የገረመኝ ደግሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህይወቴ ከልጅነት እስከ ዕውቀት አንድም ዕጣ ነፍስ ብሄራዊ ፀጋ እና መክሊትን ሊሂቅነትን አክብሮ ዕውቅና ሲሰጥ ሰምቼ አላውቅም። የተከበሩ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ግን የውድቀታችን መንስኤ ከላይ የተቀቡ ዲግሪም፤ ዲፕሎምምየሌላቸው ባለ እዮር መክሊተኛን አከበሩ።ዕውቅናም ሰጡ።
ብዙ የፖለቲካድርጅቶች ተጽዕኖ ፈጣሪን ይለቅማሉ። ግን አካዳሚያዊ ማስረጃ ካለው ብቻ። ሚዲያወችም ፈለጋቸው ይህው ነው። ብዙ በጣምብዙ ተዝቆየማያልቅ ሁለገብ ፀጋ እናክብረት ተዳፍኖ፤ ተዘሎበስውር እገዳ እና ጫናየእኛነት ማህደር ተቀብሮ ኑሯል። ያልቀናነም ለዚህም ነው። እኤአ በ2008 ይህችን ቀን ኮፐን ሃገንዴንማርክ ነበርን። የአባይ ሚዲያ መሥራችም ነበር። የሲዊዲን ራዲዮም ነበር። እኔም የፀጋዬ ራዲዮን እና ድህረ ገጽን ወክዬ ነበርኩኝ።
ስለ ነፃነት ስለ ፍትህ ርትህ፤ ስለ ዴሞክራሲ መሻትድምጽ ልናሰማ ከመላ አውሮፓ ተጠራርተን። ያን ጊዜ እነ ነብዬ ብጄ አሳምነው ጽጌ፤ ወት ብርቱካን ሜዲቃስም እስር ላይ ነበሩ። በበለፀጉ አገሮች ጉባኤ አፍሪካን ወክለው አቶ መለስም ተገኝተው ነበር። ዛሬም ሰልፋ አላቆመም። እረፍት የሚሰጠን ጠፍቶ እንባትላለን።
የሆኖ ሆኖ አቶ መለስ ሞተውም መንፈሳቸው ሰጥለጥ አድርጎ እዬመራ ነው። ዛሬም የኢትዮጵያ ልብ ያላቸው ብልህ ሊቀ - ሊቃውንት ይጮኃሉ አድማጭ ግን አላገኙም። እርግጥ ነው ጠሚር አብይ አህመድን በጥዋቱ ቢሞግቱ ይህን ያህል ገንግነው በተራ ዘለፋ የኢትዮጵያን ህዝብ ባላሳፈሩት ነበር። ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ እኔ ከዛ ፍፁም ጠያፍ ንግግራቸው በኋላጠቅላይ ሚር አብይ ይደበቃሉ ብዬ ነበር። እራሳቸው ቴሌቪዥን አይደሉ አላፈሩም።
#ወደ ቀደመው ……
ፕሮፌሰር ሚንጋን በቪዥን ኢትዮጵያ በግንቦት ሰባት ዘመነ አጤነት ቃለ ምልልስ ይደረግላቸው ስለነበረ አዳምጣቸውም ነበር ያን ጊዜም። በቅርቡም እንዲሁ አንድ ቃለ ምልልሳቸውን አዳምጫለሁኝ። ሚዲያውን የሚስከብር ሰብዕናቸው ትውልድን የመቅረጽ አቅሙ ልዩ ነው። ከሁሉ በፊት ለፊት፤ በስተ ኋላ፤ በግራ እና በቀኝም የወከሉት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን ብቻ መሆኑ ይህን የዝንቅንቅ አረማዊ ዘመንን የመግራት አቅሙ አንቱ ነው ብዬ አስባለሁኝ።
እኒህ የአገር ቀንዲልን ጨምሮ ሌሎችም ብርቱ ትጉኃን ለአቀረቡት የውስጥነት የዕውቀት መላ እና የመሐንዲስነት ሃሳብ ግን የኢትዮጵያን ችግር አመክንዮዊ በሆነ ኩነት አብራርቶ ለፍትህ ያበቃል የተባለው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኢሜል እንኳን መልስ ለመስጠት አልደፈረም። ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ተስፋው ቁሞቀር መሆኑን ገልጠዋል። እኔም የጨነገፈ ስል ከሞገትኩት ጋር ተዋህዶልኛል።
እንዴት በኢሜል እንኳን መልስ መስጠት አቃተው አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ? እራሱን መናድ መወጠኑን ያሳያል። የተከበረው የተከበረውን የራሱን አምሳያ ማክበር፤ ዕውቅና መስጠት ከተሳነው ለዛ በባዶ እግሩ ለሚሄድ፤ እራፊ ከአንገቱ አድርጎ ያልፋልን ሲጠብቅ ለኖረ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ተስፈኛማ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከቁብ እንደማይቆጥራቸው ልብ ልክ ነው።
እኔ በግሌ ከማህበረ ኦነግ የምጠብቀው የመፍትሄ፤ የተስፋ፤ የምህረት፤ የፍትህ፤ የይቅርታ ትፍስህት የለኝም። ምክንያቴ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵዊነትን አብዝቶ ከሚጠዬፍ፤ ከሚበቀል፤ በበታችነትስሜት ከሚሰቃይ፤ በኢትዮጵያ ቀደምትነት፤ ፍልስፍና፤ ረቂቅነት በቅናት ከሚደብን ድርጅት ስለማይጠበቅ። ኢትዮጵያ እንድትከስል የወሰነው በወል ዕብደታችን "በኢትዮጵያ ሱሴ" ግርፍ ቅላፄ ነበር።
እኔየሽግግር ፍትህ፤ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፤ ሥም አያጡም ሌላም ይፈጥራሉ ጠሚ አብይ አህመድ አሊ። ሁሉም የጉሮ አጥንት ነው። አለቅትም።
ቢያንስ እነኝህ የተከበሩ የኢትዮጵያ መንፈሶች ለሚያቀርቡት ዕይታ ስለምን ዕውቅናስ? ትኩረትስ? አክብሮትስ ሊነፈግ ቻለ???
ውዶቼ ዛሬ እንዴት አደራችሁ ሳልል ቸከቸኩት አይደል። እንዴት ናችሁ። ብታደምጡት ትፈወሳላችሁ። ማስተዋልን ይሸልማችኋል። ሚዛናዊነትን ያበረክትላችኋል።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ኑሩልኝ።
ሥርጉተሥላሴ
SerguteSelassie
25/12/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ጊዜ ቅኔ ነው።
ዕውነት ወጌሻ አያሻውም።
 
 
ተጠያቂነት የሌለበት መንግሥት እና ሀገራዊ የፋይናንስ ቀውስ || ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ይናገራሉ #Ethiopia

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።