ለምን ሥማችሁን #አብይ አትሉትም? ጓዘ ቀላል ጥያቄ ለፋና፤ ለዋልታ፤ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ፤ #ለኦሚኮ።

 

ለምን ሥማችሁን #አብይ አትሉትም? ጓዘ ቀላል ጥያቄ ለፋና፤ ለዋልታ፤ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ፤ #ለኦሚኮ
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ።
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"
 May be an image of text that says 'ebs ੴ ዋልታ RC'May be an image of 1 person and textMay be an image of 1 person and text
 
እንዴት ናችሁ ማህበረሚዲያወች። የማንእንበላችሁ? የማንስ ትሰኛላችሁ? መቼ ይሆን ለገባችሁት ሙያዊ ቃል ሟች ሆናችሁ የምትገኙት? ዘወትር አንጋችነት አይሰለቻችሁም?
ግን ስለምንሥማችሁን አብይ አትሉትም።መሃያ ቆርጠው የሚያስተዳድሧችሁ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ናቸውን? በቃ የሳቸው ውሎ አዳር ዘጋቢ ብቻ ሁናችሁ ቀራችሁ እኮ?
ግን የቀራችሁንስ መቼ ታስደምጡን ይሆን? የሌሊቱን አዳርንም፤ የጠሎት ሥርዓቱን ሁለመናውን ልጠቅሰው የማልሻውን ሁሉ? እሳቸውም እኮ እንደ እናንተ ኢትዮጵያ ቀጥራ የምታስተዳድራቸው አገልጋይ እንጂ አሰሪያችሁ አይደሉም። ይህንያክልግልምት ብሎን እስኪያቅለሸልሸንድረስ ዝክረ እሳቸው ብቻ? ሥራጠፋን?
የሚገርመኝስለ ራሺያ እና ዩክሬን፤ ስለ ፍልስጤም እና እስራኤልሐተታ አላችሁ። አንዳንድጊዜ ፋና፤ ዋልታ፤ ኢቲቢ፤ ጁቢተር ላይ ያላችሁ ይመስለኛል። በቃ የመጠቃችሁ። የደም አላባ፤ የዕንባ ጎርፍ፤ የድሮንሥልጣኔ በህዝብ፤ በቅርስ፤ በውርስ፤ በሃይማኖት፤ በትውልድ ላይቀንከሌት በጭካኔ እዬዘነበእናንተ የጠቅላይ ሚር አብይአህመድን ፋንታዚስታቆላምጡ፤ ስታሽሞነሙ ግንመሬት ላይ ስለመኖራችሁ ይረዳኛል።
ለእኔ በኢትዮጵያ መከራ ላይ እያላገጠ፤ እዬተጫወተ ያለው እናአረመኔነት እንዲንሰራፋ፤ ትውልድ በባዕቱ፤ ትውልድ በሁለመናው ይነቀል ዘንድ እዬሠራችሁ ያላችሁ ሚሳኤሎች እናንተው ናችሁ። የጥፋት መልዕክተኝነትን ስለምን እንደምንትከባከቡ ይጨንቃል። ይጠባል።
የኢትዮጵያ አምላክም ሩቅ ይመስላችኋል። የኢትዮጵያአምላክም የማይፈርድይመስላችቿል። ግንዕንባም፤ መከፋትም፤ ማዘንም፤ መገለልም፤ መጨቆንም፤ መረሸንም፤ መፈናቀልም፤ መደፈርም ሁሉ የመከራ ዓይነት አምላክ አለው።ይፈርዳል። ይዳኛልም።
በርዥኑን ቀይሩት። ጭካኔን በአካል ተአምሳል 365×5= ?! እዩልን እያላችሁ እምታስገድዱትን ቢያንስ ቀንሱት። ፀያፋን ንግግርስ አላዳመጣችሁምን? "ሸለፈታምን" እንደ አንድኩሩ ኢትዮጵያዊ በፋና፤ በዋልታ፤ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ራዲዮ እና ቴሌቪዥን የምትመሩ፤ የምትሠሩ ምን ይሰማችኋል? ክብር፤ ኩራት???? ወይንስ ውርዴት????
ሠራተኛው እንጀራው ጉሮሮው ነው። የመወሰን አቅም የለውም። አስተዳደሩ ይህን የመከራ ዘመን የሚመጥን አመራርን መፍቀድ እንደምን ተሳነው? "#ሸለፈታም!" ይህን ጠያፍ ቃል ሚዲያችሁ ሲመራው፤ ሲያጥጥመው፤ ጌጤ ብሎ ማዕረግ ሲሰጠው ኢትዮጵያ በዚህ ውስጥ መቀበሯን ላረዳችሁም እሻለሁኝ።
የሚሻለው ሚዲያችሁን "አብይ አህመድ አሊ" ብሎ መሰዬም ነው። እኛም እንደ ዜጋ በእናንተ ዝልግልግ አመራር እና በሥማችሁ አንገት ከምንደፋ። ዕብደት አይሉት ዕብደት፤ ይህን መሰል እጅግ ጠያፍ ቃል በኢትዮጵያ በጀት በሚተዳደር ሚዲያ???
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የቱሪዝም ሚር ወይንም የአሽዋ ሚር ወይንም የብሎኬት ማምረቻ ድርጅት ማናጀር፤ ወይንም የኮንስትራክሽን ኮሚሽነር አይደሉም። ወይንም የሪዞልት ኢንቤስትር። የአገር መሪ ናቸው። ለዛውም የአፍሪካ አንከርን ኢትዮጵያን የሚመሩ። ይህም ብቻ አይደለም የዓለም የሰላም ሎሬት ተሸላሚ የሰላም አባት። ግን ሁሉምፊክሽን ሆኖ የቀረ።
የእናንተ መደበኛ ተግባር የፋንታዚ ልዑልን የትወና ተግባር ሞድ መቀመር ብቻ ሆነ። ሞርዳችሁ፤ ጠርባችሁ ለአንዲት ሰዓት ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው የማድመጥን ሀሁ እንዲቆጥሩ ማድረግ ነበር። ያ የተከበረ ቢሮ የሸሪሪት ድር ቅልቅሉንከሚያስነካበት። ሮላችሁ ጠፍቶባችኋል። እኛ የሞድ ሾው አልናፈቀነም። እንዴት እንደሚገለማ ብነግራችሁ። የእኛ የሲዊዝ መሪወች መልካቸውን እምናዬው ለአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫ ሲሰጡ ብቻ ነው።
ሲዊዝ ሰባት መሪ ነው ያላት አንዱ ብቻ ይታያል። የትም ቦታ፤ የትም አገር በቀይ ምንጣፍ የሚንጎባለል የሲዊዝ መሪ አቀባበል ታይቶ አይታወቅም። ቢሄዱም ሻንጣቸውን እዬጎተቱ እንደ አንድ ግሎባል ዜጋ ብቻ ዬሄዱበትን ካለ ግርግር ከውነው ይመለሳሉ። በዚህ ቅኝት ውስጥ ላለን ኢትዮጵያዊ የእናንተ የዕዬለት የጠቅላይ ሚር ዲኮሬሽን ቋቅ ሊለን ግድ ይላል። ለዛውም በሚሊዮን ደም የጨቀዬ አመራርን ስትኮፍሱ።
እርግጥ ነው በኢንሳ እንደምትመሩ ይረዳኛል። ሚዲያወች የሰላዮች አስተዳደር መዋኛ ሆኗል። መኖርን ለማኖር መታገስ ሊኖር ይችላል። ግን የላይኛውም ማዬቱን መመዘኑን መዳኜቱንም መዘናጋት አይገባም።ከሁሉ ዓይናችንምጆሮችንም ዝሏል። ዓመት ይዞ እስከ አመት የፋንታዚ ዳንቴል???? ያቅለሸልሻል።
ሳይከፈለው የደገፈ፤ ያበረታታ የወደደ እና ያከበረ ህዝብ በባዕቱ የጲላጦስ አምሳያ አሳቻ መሪ እንደ ጣለበት እያንገሸገሸው ተገንዝቧል። ፕሮፖጋንዳችሁን ቀንሱ። ፕሮፖጋንዳ ጭራሽ የማያስፈልገን ኢትዮጵያዊ ዜጎች እንዳለንም ተገንዘቡ። ለዛውም በሞታችን ላይ የሚከፈት የፕሮፖጋንዳ ገብያ???
ውል የፈፀማችሁ የጠቅላይ ሚር አብይ ጋር ነው የሆነው። ረድነትም አለው ዓይነት? አንጋችነትምአለው መልክ? ደጋፊነትምአለው ገጽ፦ እንደምን ለዛፌ ጥላየሰው ሞት ደጀኔ ነው ያለን ቤርሙዳ መንፈስቤቢ ሲተር እንዲህ ይኮናል። በሌላ ዘርፍጥረት እያደረግን ነው ልትሉ ትችሉ ይሆናል። የአሳግማቱ ከጭንቅላቱ ሆነ እና ሁለመናው አሳንጋላኮሶ ሆነ። እኔ ስቅለት ላይእንዳላችሁ ይሰማኛል።
የገረመኝ ያን ፀያፍ ቃል "ሸለፈታም" ብለው የኢትዮጵያን ሚዲያ፤ የኢትዮጵያንፓርላማ፤ የኢትዮጵያን የመሪነት ቅብዓ፤ የኢትዮጵያንካቢኔ፤ የኢትዮጵያን ተቋማት ካራከሱ በኋላደግመው ደግሞ ሚዲያ ላይ ሞሽራችሁ ቅበላ ላይ አዋላችኋቸው። #ኧረ #ተያይዛችሁ #ተደበቁ። አንድ ቤተሰቡን አጥቶ መንገድ ላይ ያደገ ጎረምሳ የማይደፍረውን ጠያፍ ቃል አንድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚር የዛሬን አያድርገው እና በጥንት በጥዋቱ በከበረው ቀደምት ዕንቁ የአዬር ኃይል የምስረታ በዓል አከባበር ላይ? ከዚህ ቀደምም፤ ወደፊትም ለሚፈጠረው የሠራዊቱ አመራር፤ ቤተሰብ፤ ተከታይ ሁሉ ቅስም ሰባሪ ውርዴ ገጠመኝ። የዚህ ቤተኛ በመሆናችሁ አቤቱ ፋና፤ ዋልታ፤ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና የሞጋሳተጠማቂው #ኦሜኮ እንኳን ደሥ አላችሁ¡¿¿¿¡¡¡¡ ይህ ዝልኝ ቃል እንኳንስ በመሪ፤ እንኳንስ በብሄራዊ ሚዲያ በዜግነቱግርማሞገሱን ባላሸለተ ባተሌም አይገለጽም። "#ሸለፈታም። ጠቅላይ ሚርአብይ አህመድ እና ሚዛናቸው"
 
 
#እስቲ ኢትዮጵያን ጠይቋት ምንሽን ነው ያመመሽ ብላችሁ???
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ፈቅጄ ከማደምጣቸው ሙሁራን ወገኖቼ አሉ፤ የሉምም። የዚህን አሳቻ መሪ እና ዘመን ጠንቅቀው የሚከታተሉ ስለአሉም ስለለሙ ፈቃዴ በዛ ይወሰናል። ደግፎም ሞጋች፤ ተቃውሞም ሞጋች ይሁን እኔን የሚገዛኝ ትንታኔው እንጥፍጣፊ ፕሮፖጋንዳ የሌለው ከሆነ ብቻ አዳምጠዋለሁኝ።
ፕሮፖጋንዲስት ስለማያስፈልገኝ በውስጤ ጉዳይ። የሆነ ሆኖ ከአሚኮ ወዶ እና ፈቅዶ ወደ ኦሚኮ የተቀዬረው ኦሜኮ እና ፋና፤ ዋልታ፤ ኢቲቪ ይህን ብታዳምጡት ስንት ውድ የአዬር ላይ ጊዜ እንዳባከናችሁ ቁጠባ ያስተምራችኋል። ኡራኖስ ላይ ይሁን ጁቪተር ላይ አድራሻችሁ አሳቻ ስለሆነ። ለነገሩ የኢንሳ ተለዋጭ ቢሮ ተደርጋችሁ የለንም። ኢትዮጵያ በሽታው ባልታወቀ ህመም ስለመሰቃዬቷ ይህ ጭምት፤ ጨዋ፤ ስኩን ሚዛናዊ ዕይታ አቅጣጫ ያመለክታል። ለእኔ ሞዴል ነው።
"ተጠያቂነት የሌለበት መንግሥት እና ሀገራዊ የፋይናንስ ቀውስ || ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ይናገራሉ #Ethiopia"
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24/12/2023
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።