ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን "በብልጽግና" መንደር የሆነ ነገር #ቢፈጠር ማን ይተካቸዋል? ለሚለው #ጠቅላዩ መልስ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁኝ።

 

ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን "በብልጽግና" መንደር የሆነ ነገር #ቢፈጠር ማን ይተካቸዋል? ለሚለው #ጠቅላዩ መልስ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁኝ።
 

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
የህወሃት ህገ - መንግሥት ተጥሶ ከምል #ተጠቅጥቆ፦ የፓርላማው ጉባኤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት #ጭብጥብጥ ተደርጎ በራሳቸው ፈቃድ በአናርኪዝም መርኽ ሚኒስተሮቹን ሿሿሙ ---:ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ። 
 
ለሚያረገርገው ካቤኒያቸው በዬጊዜው ሲያነሱ፤ ሚኒስተሮቻቸውን ሲያሽቀነጥሩ፤ በዲሞሽን ሲያንበሸብሹ ባሊህ ባይ የላትም ኢትዮጵያ። #ሃግ የሚልም የለም። በስንት ሽልንግ #ጦቢያን ዶር አብይ አህመድ አሊ እንደ ሸመቷት አይታወቅም። እንዲያ ወፍ የቀናው ዕለት በሥርዓተ አልበኝነት ህግ ጥሰው የሹመት ዓዋጁን ያስነኩታል። በሳቸው #የተጨባበጠው ፓርላማም ባሰኛቸው ቀን #ይሁንታ ይሰጥላቸዋል። መታደል ይባል መገደል አላውቅም።
 
 ኢንጂነር አንሻን የመከላከያ ሚር አደረጓቸው። ወዲያው በዲሞሽን ከሆነ ቦታ ወስደው ሸጎጧቸው። በዛ ሰሞን ደግሞ ቀኑ ላልታወቀ ጊዜ ተልዕኮው ለምን እንደሆን ባናውቅም ዶር አብርኃም በላይ ተነስተው ኢንጂነር አንሻ የመከላከያ ሚር ሆነው ተሹመው አይተናል። የሚባንን ጉድ።
 
ወደ ቀደመው ጉዳዬ ስመለስ በዚህኛው የሹመት ሂደት እንዲያው በመፈንቅል ይሁን፦ በተፈጥሮ ሁኔታ አንድ ነገር ቢፈጠር ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ማን በብልጽግና ሠፈር ይተካል ለሚለው የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ስጋት፦ እራሳቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መልስ ሰጥተዋል። ቀዳማዊ እመቤትነቱም በፍትህ ሚኒስተርነት ቀድመው ቁብ አድርገዋል። የህግ ባለሙያው ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ ከዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ጋር ይተዋወቁ ዘንድ ሁለተኛ ዕድል ሰጥተዋቸዋል።
 
የመጀመሪያው በደቡብ አፍሪካ በህወሃት እና በመንግሥታቸው በነበረው ድርድር ተወካይ ነበሩ። በዛ አህጉራዊም፦ ዓለም ዓቀፋዊም የዕውቅና ገበር ተሰጥቷቸዋል። አሁን ጠቅልለው የሳቸውን ቀጣይ የኃላፊነት ቦታ ሰጥተዋቸዋል። ትልቁ የኢትዮጵያ የሥልጣን እርከንም ነው ውጪ ጉዳይ ሚር። በዚህ መድረክ እቴጌ ዓለማችን ዶር ገዲወን ጢሞቲወስን #አሳምራ ትተዋወቃለች፦ ታጠናማለች ማለት ነው። 
 
ወጣት እና የህግ ሊቅ። ሰብዕናቸውን በይበልጥ ጥሩ አድርጎ ቦታው ይገነባላቸዋል። ከብዙ ዕውቅ ተጽዕኖ ፈጣሪወች ጋር በሚገባ ይተዋወቁበታል። አንድ ጊዜ ሰብዕናው የተገናባን ሰው መነቅነቅ ደግሞ እጅግ ይከብዳል። 
 
ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ የፍትህ ሚር በነበሩበት ወቅት ላም ጣም ያለው፤ አንጀት የሚያርስ ተግባር ተጠብቆ ባክኖ ቀርቷል። ፍትህ ላይ በነበሩ ጊዜ የአማራ ህዝብን #በገፍ እስር እና ወከባ፤ ግድያ እና አፈና ከሚታወቀው መንግሥታቸው ጋር #ሰምና #ወርቅ ሆነው የቆዩ፤ ብዙ ተጠብቆ ተስፋው ሁሉ #እብቅ የቃመበት አጋጣሚ ነበር ያስተዋልኩት እኔ በግሌ። በውነቱ የባከነ ጊዜ ነበር ማለት እችላለሁኝ። 
 
አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚር ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ የአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ይነሳ ይቀጥል ይህን እንኳን ከመርህ አንፃር ሊሞግቱ ያልቻሉ ሰው መሆናቸውን ነው እኔ ያስተዋልኩት። ስለ አማራ #እናት የወል ስቃይ፤ የጋራ ደም ዕንባ እና የውስጥ መሪር ሃዘን የማይሰቀጥጣቸው መሆናቸውን ነው የታዘብኩት።
 
 አሁንማ ጭራሽ የፍትህ ሚኒስተር ጉዳይ እማይሰማ፤ እማይታይ ገመና የለም ፍትህ በኢትዮጵያ የዶር ገዲኦን #ሌጋሲ #የሳሎን #ክፍል #ጉባኤ ሆኖ አረፈው። ኢትዮጵያን ለምታክል ታላቅ አገር እና ቻይ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን የመሰለ የሰርክ ውርዴት #ይኮመድዳል
 
ሌላው በካቢኔ ስብሰባም ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በላይ ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ #ድርብ ድምጽ ይኖራቸዋል። ባለቤታቸው ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ እና እሳቸው #ጣምራ ድምፁን ይዘው ይቀርባሉ። ይህ በራሱ የተፋለሰው ውሳኔ ተራጋጭነትን ያገናዝባል። ጠቅላይ ሚር አብይ ግን ሎጅካሊ የሚኖራቸው ድምጽ #አንድ ብቻ ይሆናል። 
 
ስለዚህ በድምጽ #ሞናፖሊም ዶር ገዲዮን > ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ህጋዊ የሆነ የብልጫ አቅም አላቸው። ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ ኢንፓዬር በኢትዮጵያ ካቢኔ የሚጠበቅ ዘባጣ ገጠመኝ ነው። ለውጭ ጉዳይ ሚር ከተማላው ህዝብ የተሻለ ተመክሮም፤ ልምድም የላቸውም። ገና ፊደል ቆጣሪ ናቸው። ሁለት የማህበረ ኦነግ ምክትሎች ግን አውታራቸውን አደላድለው ይጠብቋቸዋል። አይነኬዋ አንባሳደር ብርቱካን አሉ፤ ሌላም። ማጃጃልም አለው ዓይነት። ይህ ፈጣጣነት ግን የሥርዓተ መንግሥትን ህግጋት ጠንቅቆ ያለማወቅ ብቻ ሳይሆን ያለ #ቅብዓም ይመስላል። 
 
ይህም ብቻ አይደለም ለቀዳማዊ እመቤትነት እራሳቸውን ያጩም እንዳሉ አልፎ አልፎ አደምጣለሁኝ ፦ በሌሎች ገጠመኞች። ከቤቴ ሆኜ ውሽክ እላለሁኝ። በማህል ደግሞ ይህ የታሪክ ተፈጠረ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር + ፍትህ ሚር= የሳሎን ቤት ጉባኤ። ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ ከባለቤታቸው ጋር ካገኙት ወሳኝ ቁልፍ የኃላፊነት ቦታ ጋር ዕድሉ ከፍ ቢል በሙያ ብልጫ ያለው ይሆናል።
 
ዛሬ ዓለማችን ሁሉንም ነገር ነጣጥላ ሳይሆን አቀናጅታ ስለምታዬው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዛሬ ባለው ያልፀና መንግሥታቸው #እክሉ ጠንክሮ ቢቀጥል፤ #መፈንቅል ቢገጥመው ወይንም ተፈጥሮ #ብታኮርፍ ብሎ ለሚያስብ የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ የቤት ሥራውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቀድመው የሠሩት ይመስለኛል። ያው ኢትዮጵያ እንደ #ጥንቸል የመሞከሪያ ጣቢያ አይደለች???
 
የሆነ ሆኖ ምንም እንኳን ለውጭ ጉዳይ ሚር ሆነ ለፍትህ ተቋም ቁልፍ ቁንጮነት ዬሹመቱ አፈፃፀም #ሪህ ቢኖርበትም። ጎርበጥባጣ - ቢሆንም ለዶር ገዲወን ቤተሰብ ግን ብዙ ደልዳላ ምቹ ሁኔታ ተክፍቶለታል ብዬ አስባለሁኝ። ሌላም በወሮ ሃና አርዓያሥላሴ በኩል የወንድማቸው በሌላ #ቁልፍ የኃላፊነት ቦታ መቀመጥ ቤተ- ዘመዳዊ ጉባኤ ለቤተ- መንግሥቱ እጩነት ……… ያሰኛል።
 
ቀደም ባለው ጊዜ ዶር ወርቅነህ ገበየሁ ለዚህ መሰሉ የቀጣይ መሪነት ቦታ በመንፈስ የታጩ ነበሩ። የዛሬውን ባላውቅም በህወሃት እና በፌድራሉ ጦርነት ከታሰቡት አንዱ የነበሩ ይመስለኛል።
 
የሆነ ሆኖ የአንድ አገር ፓርላማ #ሥርዓተ አልበኝነትን እንዲህ ተቀብሎ አጨብጭቦ ሲያፀድቅ የኢትዮጵያ ትውልድ ተስፋ በሥርዓተ - መንግሥት መርኃዊ አገነባብ ላይ የህሊና ኪንታሮት ይተክላል። አናርኪዝም በምንም መስፈርት ለትውልድም ለአገርም ድዌ ነውና። ህግ ተምረህ ለመርኽ መገዛትን ካልፈቀድከው መማርህ የቋንጃ ምን ይሁን???? ሁለቱም ባለትዳሮች የህግ ሙሁር ግን በህግ ጥሰት ሹመታቸውን የተቀበሉ። ትውልድ ከዚህ ድርጁ ግድፈት ምን ሊማር ይችላል ነው ጉዳዬ። 
 
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁልኝ። ኑሩልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/10/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
#ትእግሥት #ሲያልቅ፦ #ፍቅር #ይሰደዳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።