ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።

 

ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል

እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።

(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)

ማዕዶተ ርትህ ሰባዓዊነት።





ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ

የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር

አዲስ አበባ።

የማክበረዎት ዶር ዳንኤል ሆይ!

አንድ ጊዜም ይህን ጉዳይ አጽህኖት ሰጥቼ አንስቼ ነበር። አዲስ አበቤ ሰብዕዊ መብቱ ሲረገጥ ባለቤት የለውም። ምንም የመኖር ዋስትና የለውም። ልጆቹ በዬዘመኑ በ አደባባይ ይረሻናሉ፤ ካሳ ተከፍሎት እንኳን አያውቅም። ልጆቹ በሰማዕትነት ተዘክረው አያውቁም።

እኔ ይህ ለምን ሆነ ብዬ ሳስበው፤ ሳወጣ ሳወርደው አዲስ አበባ ላይ ራሱን የቻለ አንድ የሰብዕዊ መብት ኮሚሽን ግብረ ኃይል እንደሚያስፈልግ ይሰማኛል። በሚመጣው ምርጫም ብዙ ቀውስ ሊከሰት ይችላል። ከ አሁኑ ችግሩን ኮሚሽነዎት ተረድቶ ከማንም ከምንም ከዬትኛውም ክልል ያልተዳበለ የ አዲስ አበቤ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይከፍቱ ዘንድ በታላቅ ትህትና አክብሮት እጠይቃለሁኝ።

አስፈሪ ደማና፤ አስፈሪ ድባባ ነው ያለው። ከምርጫ ጋር ተያይዞ በጣም እጅግ በጣም ተጎጂ የሚሆነው አዲስ አበቤ ነው። የሚያሳዝነው ጉዳቱ እንኳን በ አግባቡ አይዘገብም። የተጎጂ ቤተሰቦች ሥማቸውን እንኳን አናውቅም። ከሰኔ 16/2010 ጀምሮ እስከ ሸኜነው ሳምንት ድረስ አዲስ አበባም የደም ከተማ ሆና ነው የባጀችው። ሟቾቹ ደመ ከልብ ናቸው።

ሰፊ የቃጠሎ፤ የዝርፊያም መከራ ሊኖር ይችላል። የትንንቅ ጊዜ ነውና። እባክዎት አቤቱታዬን ከጉዳይ ጥፈው አንድ መላ ይሠሩለት። እርግጥ ነው የቀውሱ ብዛት፤ የመከራው ዓይነት ልክ የለውም። ግን ዋቢ አላገኜም። ይህን ባለፈው ጊዜም አመልክቻለሁኝ። ዛሬም መድገም ግዴታዬ ነው።

አዲስ አበቤ ሁልጊዜም ማገዶ፤ ሁልጊዜም መከራ ተቀባይ፤ ሁልጊዜም ፍዳውን የሚይ ቅን ህዝብ፤ ደግ ህዝብ፤ ቻይ ህዝብ ነው። እንደተረገጠ የሚኖር ህዝብ። አቶ እስክንድር ነጋ ሁነኛው ህሊናው ነበር እስከ ቲሙ እስር ቤት ነው። በመስከረም 5/2011 ኦነግ ሲገባ የተረሸኑ 5 አዲስ አባቤ ደመ ከልብ ሆነው ቀርተዋል። ከታሠሩት 1300 አዲስ አበቤ እነኝህ አልተፈቱም እስካሁን። ከ አርቲስት ሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞም የየኔታዋ ልጆች እንዲሁ እስረኛ ናቸው።

በቀጣዩ ምርጫ ምርጫ ከኖረም ምን ሊፈጠር እንደሚችል ከባጀብን መከራ ተነስተን መገመት ይቻላል። ስለዚህ እባከዎትን የተሟላ መሳነዶ አዲስ አበቤ ላይ እንዲኖር ያደርጉ። እባከዎትን?

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27.03.2021

ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።