ልደቱ እና ህማማቱ።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።

 

ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል

እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።

(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)

·       ማዕዶተ ሰባዕዊነት ለዛውም በሰንበት።

እንዴት ናችሁ ቅኖቹ? ደህና ናችሁ ወይ?





·       የሰውነት ህማማት።

ርህራሄ በተሰደደበት፤

ሰውነት በክፋት በሚጨፈጨፍበት፤

መኖር በበቀል በሚከተከትበት፤

ቂም የመንግሥት መርህ በሆነበት፤

በቀል የምንግሥት „ፍኖተ ብልጽግና“ በሆነበት፤

አገር ላይ ሰባዕዊነት ይመጣል ብሎ ማሰብ ከጅልነትም ከፍ ያለ ነው።

 

በተደራጀ፤ በተቀነባበረ፤ በሥር ዓት በሚመራ የበቀል ኦፕሬሽን ላይ

ስለ ትውልድ፤ ስለ አደራ፤ ስለ አገር፤ ስለመኖር ማሰብ መርግ ነው።

ኢትዮጵያን ቁጭ አድርጌ፤ በ አቶ ልደቱ አያሌው የመሠራውን ግፍ ፊት ለፊት አስቀምጬ አሟግታቸዋለሁኝ። ከዛ የትውልዱን ተስፋ ሳስብ መቃብር ይወርድብኛል።

ይህ የኦሮሙማ ሥርዓት ሊወገድ ይገባል። ርህርሄ ለ እኛ ከሌለው ለ እንጨቱ፤ ለወንዙ፤ ለሳር ቅጠሉ ለማን ሊሆን ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰው ይህን አመክንዮ ፊት ለፊት አቅርቦ ሊያወያዬው ይገባል።

ሰው መሆናችን ካልካድነው፤ ተፈጥሮን ካልቀበርነው በስተቀር አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይህን ያህል በደል ሲፈጸምበት ይህ የ ኦነግ አመራር በቃህ ሊባል ይገባዋል። በውነቱ ትዕግስትን የሚፈትን መከራ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው። ይህን ነውር ዓለም በትክክል ቢነገረው፤ ቢሰማ ምን ሊለው እንደሚችል አላውቅም።

አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የመሠረተው ፓርቲ ተዘርፎ በበቀለኞች ካሳም፤ ይቅርታም ሳይጠዬቅ፤ እራሱን አጠናክሮ መነሳት ሲጀምር በግፍ ተሰርዞ፤ ከሌሎች ጋር እሰራለሁ ሲልም ተሰባባሮ፤ ሃሳቡን አፍላቂ ከኮረና ጋር በሃሰት ክስ አስሮ፤ አንገላቶ፤ ሁለት ጊዜ ሙሉ ከ አውሮፕላን እንዲመለስ አስደርጎ፤ በልብ ህመም እዬተሰቃዬ እንዲሞት ሲፈረድብት ኢትዮጵያ አለች፤ መንግሥትም አላት ለማለት እኔ አልችልም።

ቀደም ሲል አልፎ አልፎ ያለው አስተዳደር ነው እል ነበር። አዎን የ ኦዳ ሥርዕወ መንግሥት የመሆን አቅም የለውም። የሠፈር አስተዳደር ነው ያለው። ይህን ዕውነት እያዳመጡ ከሰባዕዊነት ጎን አለመቆም በውነቱ ለሁላችንም ፍተሻ ያስፈልጋል። ዕውነት ነው እዬተራደ ያለው በጠራራ ጸሐይ። ልቅና ነው በቦንብ እዬተደበደበ ያለው። ሰውነት ነው በመትረዬስ እዬተቀጠቀጠ ያለው።

አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጂነር ይልቃል ጌትንት የተናገሩት እኮ የ ዓለም አቀፍ የሰብዕዊ ድርጅቶች አስገድደው በሩን አስከፍተውታል። እነኝህ ብርቅዬ አርቆ አሳቢ ቢደመጡ ከዚህ መሰል ረግረግ ባልተገኜን ነበር። የፖለቲካ ተሳትፎ ተሰርዞ፤ ያ የፋፋ አቅም ኳራንቲም ገብቶ በቀለኞች አልረኩም። አፈርን ይጠብቃሉ።

እስከዚህች ደቂቃ ድረስ በብርቱ ሁኔታ ተስፋ የማደርጋቸው ዶር ዳንኤል በቀለ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጡትን ውሳኔ ብቻ ሳይሆን ገቢራዊ ምላሽ እኔም እንደ አቶ ልደቱ አያሌው እጠብቃለሁኝ። ያሉን ተስፋ እሳቸው ብቻ ናቸውና። እርግጥ ነው ለእኔ ዶር ሊያ ታደሰንም የሚያሰራ ሥርዓት ቢያገኙ አንቱ እንደሆኑ አስባለሁኝ።  ተስፋ የሚሆን ጭምት አቅም እንዳለቸው ተመልክቻለሁኝ። አንድ ሰው አይፈርድ አንድ እንጨት አይነድ ሆኖ እንጂ አቅሙ አላቸው።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27.03.2021

ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።