መከረኛው አቶ እስክንድር ነጋ እና ቲሙ ... በአሳቻው ጠቅላዩ ...
እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።
ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።
(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)
ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት።
·
ኢትዮጵያን ከፈጠራት ፈጣሪ ጋር ግብግብ የገጠሙት አጤ ዝናቡ እና ሰባዕዊነት።
ውዶቼ ሰሞኑን በገጠመኝ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የልብ የሚያደርስ ተግባር ላልከውን እችላለሁኝ።
የሆነ ሆኖ በጥቂቱም ቢሆን ባለችው ትንሽዬ ቀዳዳ እዬሞካከርኩኝ ነው።
· ሰው መሆን ባልተቻለበት አስተዳደር ሰውነትን
ውለድ ለማለት ይከብዳል።
መዋዕለ ዕድሜውን፤ መዋዕለ መንፈሱን፤ መዋዕለ ተፈጥሮውን ለእናት አገሩ የሰዋው የአቶ እስክንድር
ነጋ ሰብዕና እንዲህ በጭካኔ ሲቀጠቀጥ ይህ ትውልድ ተስፋው በምን ያህል መከራ ውስጥ እንደ ተዘፈቀ ማዬት ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስተር
አብይ አህመድ ስንት ዓይነት ሰው እንደሆኑ እያዬሁኝ ነው። ዕዳ ከሜዳ አሰኝቶን ብዙ በጣም ብዙ ስለ እሳቸው ደከምን በተለይ እኔ።
ስለሳቸው ፍዳ ታዬ። ስለሳቸው ወገኖቻችን አስከፋን።
ይሆኑ መስሎን። ተፈጥራዊነት፤ ሰዋዊነት አብዝቶ ይናገሩት የነበረው ግርዶሽ አታለለን። ዓለማችን
የባህሪ መነጠር አልፈለሰመችም እና። እንሆ እሳቸው ታምነው መከራን ጠንስሰን፤ መከራን አዋለድን። አዝናለሁኝ። በጣም። እጅግ በጣም።
ሳጃም፤ ቦንቡን፤ መድፉን፤ ስላቁን፤ መሰቃውን ቻልን። መቻል ግድ ነውና። የተረገመው መጋቢት 18/2010 ጉልት ብለን ያደርንበት
ማዕልተ መርዶ ተመልሶ ባይመጣ ምርጫዬ ነው። ግን ተፈጥሮ ያደርገዋል።
· ቅነንት ብቅደመ ሁኔታ ሊታሰር አይገባም።
የሰው ልጅ ቅን መሆን አለበት። ወገኑን ሲቀብል ልክ እንደ ህጻን ልጅ ሲፈጠር እንደሚቀበለው
ዓይነት በጸዳ ድንግልና መቀበል ይኖርበታል። ንጹህ ልብ የህሊና ዕዳ የለበትም። ተጎዱ ግን ብንጹህ ልብ የሰውን ልጅ አስተናግዱ።
እንዲህ ሊሆን እንዲያ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ተጠራጥራችሁ አትጀምሩት። ፈታሪ የተጠረገ ልቦና ነው እና የፈጠረልን። ቤተ መቅደሱ
ነን እኮ።
ሰው ሰውነቱ የሰብዕናው ንጽህና ድንግልናው ነው። ሰው ሰውነቱ ንጽህናው እና ድንግልናው ከሆነ
ለዬትኛውም ሰብዕዊ ፍጡር በንጽህናው ልክ እንኳን ደህና መጣህ ሊለው ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። ማመን ብቻ ሳይሆን እኔ የሆንኩትን
ነው እምጽፈው። ሰው እራሱን ነው የሚጽፈውና። ቅንነት የመሰለ አልሚ ምግብ፤ ንጥረ ነገር የለም። የውስጥ ንጽህናን ያጸድቃል። ያሰብላል።
· አሳቻ ስብዕና።
የ አጤ ዝናቡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሰብዕና አሳቻ ነው። ለዚህ ነው አገራችን ኢትዮጵያም
አሳቻ መንገድ ላይ የምትገኜው። እንዲህ ዲያቢሎሳዊ ሰብዕና አጤ ዝናቡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ይኖራቸዋል ብዬ በፍጹም አላምንም
ነበር። በፍጹም። እኔ የተሳሳትኩ ስለሚመስለኝ ነው ይህን የምለው። ነገር ግን አልተሳሳትኩም ከ2016 ጀምሮ እሳቸውን በሚመለከት
የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ዳግሜ አዳምጣለሁኝ ዛሬም ከራሴ ጋር ሙግት ስላለብኝ። የኢትዮጵያ ህዝብም እኔም አልተሳሰትነም። የተሳሳተው
የሳቸው ተፈጥሮ ነው። ፍጥረተ ነገራቸው አሳቻ ነውና።
በተሳሳታቸው ተፈጥሯቸው ላይ ምንም ማለት አልሻም። ለጊዜው። ራሱን ያቻለ ፍልስፍና ነው። ዘለግ
አድርጌ በማዕዶተ ተናኜ አቀርበዋለሁኝ።
ዛሬ ልል እምችለው የሚያሰቃዩትን ቤተስብ ሁሉ ከእስር ይለቁ ዘንድ ግን አሁንም በትህትና አሳስባቸዋለሁኝ።
አቶ እስክንድር ነጋ፤ አቶ ስንታዬሁ ቸኮል፤ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም፤ ወ/ት አስካለ ደምሌን ከእስር ይልቀቁ። የማናውቃቸውን በሥምም
እንዲሁ ይፍቱ።
አይበቃም በቀሉ?
አይበቃም ጥላቻው?
አይበቃም ክፋቱ?
አይበቃም ሸሩ?
ይህን ሁሉ አሻሮ ቁርሾ ይዘው „ኢትዮጵያን እናንተ አታውቋትም እኔ ነኝ እማውቃት“ ሲሉ መሬት
ተክፍታ ብትወጣቸው ምን ሊሆኑ ይሆን? ቀብራቸው በሥርዐት መሬትስ ትቀበለው ወይንስ ቀባሪ እያደመጠ ወደ እንጦርጦስ ሲላክ ይደመጥ
ይሆን? ብዙ ጭካኔ ነው የፈጸሙት። ብታቂ ርህርና አልፈጠረላቸውም። አዝናለሁኝ።
… ያሰሩት እኮ ኢትዮጵያኒዝምን ነው። ያሰሩት ኢትዮጵያዊነትን ነው። ያሰሩት ዜግነትን ነው።
ያሰሩት መኖርን ነው። ያሰሩት ትዳርን ነው። ያሰሩት መታመንን ነው። ያሰሩት ልጆችን ነው። ያሰሩት ዕውነትን ነው። ያሰሩት መርኽን
ነው። ያሰሩት ፍቅራዊነትን ነው። ያሰሩት የረሱትን „መደመርን“ ነው። ያሰሯት ኢትዮጵያን ከነ ሙሉ ክብሯ - ማዕረጓ - ጥበቧ
- ብቃቷ ነው።
·
እኔ ልንገረዎት አጤ ዝናቡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ። ልድገመው።
ያሰሩት 100 ሚሊዮን ህዝብን ነው።
ያሰሩት ኢትዮጵያዊነትን ነው
ያሰሩት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ነው
ያሰሩት ኢትዮጵያን ከነሙሉ ክብሯ ነው።
ያሰሩት የኢትዮጵያን ማዕረግ ነው።
ያሰሩት ጋራ ሽንተረሩን ነው።
አሰሩት ቅርስ ውርስ ትውልድን ነው።
ያሰሩት ፍቅራዊነትን ነው።
የፈጁት የስሜን ፖለቲካን ነው።
ያሰሩት „የኢትዮጵያዊነትን የሚያሳሳውን ቱሪዝም ተናግሬ አልጠግበወም“ ያሉትን ተፈጥሯዋን ነው።
ያሰሩት ልዩ፤ ልዑቅ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ጥበብን ነው።
„ያሰሩት ኢትዮጰያዊውን ልቅና ነው።“
የሰሩት የሚሊዮን አንደበትን፤ የሚሊዮን ልሳን፤ የሚሊዮን የወል ድምጽ ነው።
ለአንድ እንጨት ብለው ይህን ያህል ሚሊዮን ህዝብ ማሰቃዬት አይገባም ነበር። አራት እግር ያለውን
እጨት ትተው ሄሮድስ መለስ ዜናዊ እንዳለፉ አይተውታል። ነገም ከሞት የሚቀር እንደሌለ ያውቁታል። ሁሉ ሰው ሞቶ ማዬትን አይናፍቁት።
ይህ ሳጥናኤልነት ነው። ስንቱን ገድለው ይጨርሱታል?
አሁን እኮ ዓራት ዓይናማ ባለ ድርብ አንጎል ከጭምትንት ጋርም እያዬን ነው። ኢትዮጵያዊ ልቅናን
ልዕልናን በረሸኑ ቁጥር ፈጣሪ ለተስፋችን መጠጊያ አላሳጣንም። ተስፋ ሰጪው አማላካችን አላንቀላፋም። አይምሰለዎት አለን፤ አለን
የተከደነ ሲሳይ። መርዶ እንደሆነበዎት አውቃለሁኝ።
ለዚህ ነበር ዲያቆን ዳንኤልን ተወዳዳሪ አድርገው ያወጡት፤ ሌላም አማካሪዎችትን ያወጡት፤ ስለ
እቴጌይቱ ሃውልት አዲስ ፕሮጀክት ተነደፈ የሰማነውም በዚህው አቅም ፍራቻ ነው። አትችሉትም ይህን አቅም። ኢትዮጵያን ማሸነፍ አትችሉም
ሲሉ ነበር። ይህ እርስዎንም ይመለከታል። እርሰወ ፉክክረዎት ከኢትዮጵያዊነት ጋር ነው። ውድድረዎት ከኢትዮጵያ ጥልቅ ጥበብ ጋር
ነው። ግን አይችሉትም። ኢትዮጵያም ኢትዮጵያዊነትም ያሸንፍወታል። መታበዬዎትም እስከ ግብረ ኃይለወት ጋር ፈጣሪ ልኩን ይሰጠዋል።
ይጠብቁት። ስንቱን አሳጡን? የሚታመን ተስፋ የሚደረገውን ሁሉ መነጠሩ ወይ አዝረክርከው ከስብዕና በታች ጠቀጠቁት።
ፈጣሪ ልብ ይሰጠዎት። ከፈጣሪ ጋር ውጊያ ላይ ነውት። ይህ አይበጀወትም። ቅኖችን ይፍቱ፤ ቤተሰባቸውን
አያሰቃዩ። እንቅልፍ ተኝተው ማደረዎት ይገርመኛል። አንደበተዎት አለመዘጋቱም ይገርመኛል። አንድ ቀን ልሳነዎት ቢዛጋ ምን ይሆኑ
ይሆን? ለነገሩ አሁንም በሙሉ ጤንነት ላይ ይሆናሉ ብዬ አላስብም። በዬሰከንዱ በሽታን ይሸምታሉ። ክፉ ነገር በሽታ ነው። ሸፍጥ
ደዌ ነው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
27.03.2021
ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ