ሰባዕዊነት ለአጤ ዝናቡ ለዶር አብይ አህመድ አልተፈጠረም። ጸጋቸውም አይደለም።

 

 

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።

 

ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል

እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።

(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)

 

·      







ባዕዊነት ለአጤ ዝናቡ ለዶር አብይ አህመድ አልተፈጠረም። ጸጋቸውም አይደለም።

·       ማዕዶተ ሰባዕዊነት ለዛውም በሰንበት።

በኦሮሙማ ጭካኔ ውስጥ ርህርህና ጠብ ይላል ብሎ ማሰብ ከጅልነት በላይ ነው። የተፈጠረው ለጭካኔ ነው። ደም አፍሶ ለመርካት፤ አፍርሶ ለመርካት። አውድሞ ለመርካት። ገድሎ ለመርካት። አስሮ አሰቃይቶ ቤተሰብ በትኖ ለመርካት። ይህ ሁሉ ምድር የማትችለው የሰባዕዊ መብት ረገጣን ኦፕሬሽን በበላይነት የሚመሩት አጤ ዝናቡ ዶር አብይ አህመድ አንዲት ጠጠር የጠፋባቸው አይመስሉም።

ጌታዋን የገደለች በቅሎ መስለው ማይካቸውን ቴራፒ እያደረጉ ሰለ ሰው ልጅ እኩልነት፤ ስለዜግነት፤ ስለሰፈርትኝነት ጠያፍነት ይሰብካሉ፤ ይናገራሉ ይደሰኩራሉ። ምን አበቀላቸው? ስለምንስ ተፈጠሩ? ፈታሪ ምን አስከፍተነው ይሆን እንደዚህ ያለ አሳቻ ሰብዕና ይፍጃችሁ ብሎ የፈጠረብን። በእውነት ተረግመናል። እንጹም፤ እንጸልይ፤ እንስገድ፤ እንውደቅ። ፈጣሪያችን ይቅርታ እንጠይቅ።

ሰባዕዊኒት እንዲህ በሚነድባት አገር መኖርን ማሰብ እንደምን ይቻል? እነኝህም የ እኛ ናቸው። ልንጮህላቸው ይገባል። ጩኽታችን ለላይኛው ጌታ ለአምላካችን ለፈጣሪ ለአላህ ነው።  አቤቱታችን ለ አንድዬ ነው። ይሰማናል። አቤት ይለናል። አይዟችሁን ይልክልናል።

ክፉ ሆኖ ተፈጥሮ፤ ክፉ ሆኖ አድጎ፤ ክፉ ሆኖ ኑሮ፤ ክፉ ሆኖ መሞትን የመሰለ እርግማን የትውልድ መርገምትነትም የለም። ፈጣሪ አምላክ ክፉነት እንዳይጠጋ ንጹህ ልቦናችን ይጠበቅ። አሜን።  

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27.03.2021

ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።