#ቅኔው ጎጃም ላይ ያዬሁትም ዕውነት ከሆነ እጅግ አሳዝኖኛል።

 #ቅኔው ጎጃም ላይ ያዬሁትም ዕውነት ከሆነ እጅግ አሳዝኖኛል። ቢያንስ ለአማራ እናት #ዕንባ መቆም እንዴት ይሳናል? ባልተለመደ ሁኔታ #በእናቶች ላይ የሚፈፀመው፤ በግራጫማ ፀጉር ባበቀሉ ወገኖች ላይ ያዬሁት የእንብርክክ ስቃይ፤ የከፋም እርምጃም ሰማሁ ለዚህ ነው ሙሉ ቅኔው ጎጃም ከሐምሌ 5 ጀምሮ መኖሩን የሰጠው? ለዚህ ነው? ለጭካኔ? ከጨካኝ ተሽሎ መገኜት እንዴት አይቻልም? ሙሉ የጦርነቱ አቅም የፈሰሰው እኮ ቅኔው ጎጃም ላይ ነው።

 የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አገዛዝ የውጭ አገር ቅኝ ገዢ እስኪመስለኝ ድረስ #በእልህ ማቱን ያፈሰሰው በዚህ ጨዋ ህዝብ ላይ ነው። ከመጀመሪያዋ ከሐምሌ 5ቱ የተጋድሎ ንቅናቄ ጀምሮ #በጠና አቅም እና #አቋም ሳይሽረከረክ፦ ለመደለያ ሳያድር የትግሉን መንፈስ ያስቀጠለ ጀግና ህዝብ እንዴት በተስፋወቹ ይቀጣ? ግፍ አይሆንም? አልቅሻለሁ። የት ይሂድ ይህ ህዝብ? ምርጫ አለውን? ማስተማር መንገር ማሳመን እያለ እንደዛ? ነገስ???

ሥርጉ2024/07/24

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።