ዛሬ ችሎት ከቀረቡት ተከሳሾች መካከል ሰባቱ በነጻ እንዲሠናበቱ ችሎቱ መወሰኑን

 

በእነ ጋዜጠኛ መስከረም አበራ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 16 ተከሳሾች ክሳቸውን እንዲከላከሉ ብይን ተሠጠ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ጸረ-ሽብር ወንጀል ችሎት፣ በጋዜጠኛ መስከረም አበራ፣ ገነት እስማማው፣ ጎበዜ ሲሳይ እና ዳዊት በጋሻው የክስ መዝገብ በቀረበው የአስተያየት ሰነድ ላይ "ክሱን ይከላከሉ ወይም አይከላከሉ" በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ጥር 28 ቀጠሮ ሠጥቶ እንደነበር ይታወሳል። 
 
ችሎቱ፣ በእነ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው መዝገብ ሥር የተካተቱ ተከሳሾች የዋስትና ክርክር እንዲያደርጉ ብይን በመስጠት ለሚያዚያ 23 2018 ዓ፣ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጥቷል። 
 
ዛሬ ችሎት ከቀረቡት ተከሳሾች መካከል ሰባቱ በነጻ እንዲሠናበቱ ችሎቱ መወሰኑን ዋዜማ ከተከሳሾቹ ጠበቆች ሠምታለች። በዛሬው ችሎት በጠቅላላው በክስ መዝገቡ ከተካተቱት 51 ተከሳሾች መካከል ችሎት የቀረቡት 23ቱ ናቸው።
 
ዋዜማ ራዲዮ
February 5, 2026
ፎቶው የቆየ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።