#የጠይም #ዕንቁ የእልልታ ዜና። "ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት በተመድ መንበር ላይ ተሰይሟል"
"አድርገህልኛል እና አመሰግንሃለሁኝ።" አንድ ቀን፣ አወን አንድ ቀን ኢትዮጵያ #ተመድን የመምራት ዕድል ይኖራታል።
ከጥቁር አልማዝ ይልቅ ጠይም ዕንቁ ቢባሉ።
ከአቶ Trotsky Wendesse የተገኜ የምስራች ነው። አድካሚ ቀን ነበረኝ ዛሬ ግን ይህን መሰል ዜና ብርታትን ይቸራል።
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"
መልካም የሥኬት የምርምር ዘመን ይሆንላቸው ዘንድ እመኛለሁኝ። ኢትዮጵያም እንኳን ደስ አላት።
==========
"ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት በተመድ መንበር ላይ ተሰይሟል
ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ በላይ ዓለምን እያስፈራት ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ጉዳይ፣ ዛሬ በአንድ ስመ-ጥር ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት እጅ ላይ ወድቋል። ይህ ወጣት አዕምሮ፣ ከሀርቫርድ እስከ ኦክስፎርድ፣ ከማይክሮሶፍት እስከ IBM የጥበብ ማማዎች ላይ ተራምዶ፣ ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) መንበር ላይ ተሰይሟል!
የሳይንሱ ኮከብ ጉዞ
• የማይክሮሶፍት ኩራት፦ በ "AI for Good" ላቦራቶሪ ውስጥ ዓለምን የሚለውጡ ምርምሮችን ሲመራ ቆይቷል።
• የኦክስፎርድና ሀርቫርድ አሻራ፦ ማሽኖች ለሰው ልጅ ጤና እንዴት እንደሚሠሩ በሚያስደምም ጥልቀት የመረመረ ባለሙያ።
• የዕውቀት ጎተራ፦ ከ27 በላይ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ምርምሮችን ለዓለም ያበረከተ የዘመኑ ጥቁር አልማዝ።
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአውሮፓውያኑ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተላለፉት ታሪካዊ ውሳኔ፣ ዶ/ር ግርማው ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 40 ታዋቂ ምሁራንን እንዲመራና እንዲያስተባብር በይፋ ሾመውታል።
"ኢትዮጵያ በዲጂታል 2030 ጉዞዋ ላይ ሳለች፣ እንዲህ ያለውን 'ባለምጡቅ አዕምሮ' ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ መላኳ ለሀገር ትልቅ ኩራትና ለቀጣዩ ትውልድ ደግሞ ተስፋ ነው!"
ግርማው አበበ (ዶ/ር) በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት፣ ይህን አስፈሪ የተባለለትን ቴክኖሎጂ ለሰው ልጅ ሰላምና እድገት እንዲውል በማድረግ ረገድ የዓለምን መሪ ሚና ይጫወታል።"

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ