#ጉግት ለጦርነት ጠቃሚ አይደለም። ሞት #ጎትትም ነው። ቂምና #በቀል የሚያዘምርም ነው።

 

#ጉግት ለጦርነት ጠቃሚ አይደለም። ሞት #ጎትትም ነው። ቂምና #በቀል የሚያዘምርም ነው። 
 
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ጤናይስጥልኝ አዱኛወቼ የብዕሬ እና የንጹህ መንፈሴ ፈቃደኛ አድማጮቼ እንዴት አላችሁልኝ?
 
ጦርነት #ብራቮ ጎሽ የምትሉት ሰው ሰራሽ አውዳሚ ክስተት ሊሆን የሚችል አይደለም። ጦርነት ተገደውም ይሁን ፈቅደው ይጀምሩት ለድል የሚያበቃ፤ ለትውልድ #ቅርስ ውርስ የሚሆን ጉዳይ አይደለም። የአለማችን ፖለቲከኞች ጦርነትን #በሁለት ይከፍሉታል። #ህጋዊ (አመክኖያዊ ወይንም ምክንያታዊ) እና #ህገወጥ (አልቦሽ ምክንያታዊነት) ብለው። ህጋዊም ይሁን ህገወጥ ማገዶው የሰው ልጅ ነው። እንጨት እንጂ የሰው ልጅ የተፈጠረው ለማገዶ አይደለም።
 
ፈጣሪ የረዳው #እንጨት ለታቦትም ይሆንና አክብሮተ ነገሩ ሰማያዊ ይሆናል። የሆነ ሆን ጦርነት እቅዱ ምንድን ነው ከተባለ #የእናቶችን #መሃጸን #ለቄራነት ማሰናዳት ነው። በዚህ በያዝነው ወር የዘለንስኪዝም ዕቅድ በወር 50ሺህ የራሺያ እናቶችን ማህጸን ወደ "#ሊኳንዳ" ቤት መውሰድ ነው። ለቃሉ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ። 
 
ይህን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዓለማችን አላሰናዳችም። እጅግ ያሳዝናል። ጦርነቱ እንደተጀመረ ዘለንስኪዝም እስከ 10 ዓመታት የመዋጋት አቅም አለን ብለው ነበር። ይህም የዩክሬንን እናቶች ማህጸን በታቀደ #ቄራነት ያሰላ ነበር። ይህን ጨካኝ እይታ ዓለማችን ከማውገዝ ተቆጥባ #እንክህ እንክህ ስትል ስመለከት ማህጸኔ እንደ ዱባ ይቀረደዳል።
 
የእስከዛሬው አልበቃ ብሎ የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ መንግሥት በባህር በር የይገባኛል ምክንያት ጉጉሡ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ተካሯልም። #አይጠቅምም። በፍጹም አይጠቅምም። ሁለቱም ሉዓላዊ መንግሥታት #ሊጠሞኑ ይገባል። #ጥሞና ይውሰዱ ትእዛዝ አይደለም ትህትናዊ ማሳሰቢያ እንጂ። ሁለቱም #ያከሰሩትን ዘመን አንድ ሁለት ብለው ሊቆጥሩት ይገባል። 
 
ትውልድን በጦርነት #መሰቀዝ ሰማያዊ እርግማን ነው። ለየትኛው ጊዜ። ያ - አልፏል። ይህም - ያልፋል። የሚመጣውም ማለፋን ጠንቅቆ አውቆ ነው የሚመጣው። ከሁሉ የሚያሳዝነው የዕቅዱ መተርጎሜያ አንከራዊ ጉዳይ #የማገዶው ጉዳይ ነው። ማገዶው የእናቶች ማህጸን #ቄራነት ወይንም "#ሊኳንዳቤትነት" ነው። ይሰቀጥጣል። ይቆጠቁጣል። ያሳፍራል። ያንቀጠቅጣል። የህሊና እድገትን ደረጃንም ያሳያል። እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን አሰባስባችሁ ስታዩት የፖለቲካ #ኢንፍሌንሽን ወይንም ግሽፈት መሆኑን ትረዳላችሁ።
 
ይህን ሃሳብ ይዛችሁ ስትመረምሩት ደግሞ ጭካኔ፤ ቂም፤ በቀል፤ ጥላቻን ለማምረት መጣደፍን ያመላክታል። ሰውን ማክበር፤ ሰውን ከማዳን አለመነሳቱን፤ ተፈጥሮን ለማዳን ከተፈጥሯዊነት መራቆትን ያመለክታል። ይህ ለሰው ልጅነት ደረጃ የማይመጥን ክስተት ነው።
ሰው ለሰው ክብሩ፤ ኩራቱ፤ #አጽናኙ እና #አይዞህ ባዩ ይሆን ዘንድ መፈጠሩን የሳተ መንገድ ነው ጦርነት። የትኛውም ምድራዊ ገዢ ውቅያኖስን፤ ወንዝ ተራሮችን፤ የወርቅ እና የዓልማዝ የማዕድናትን መገኛ ይዞ አልተቀበረም። ቢባዛ ሳጥኑ በወርቅ ሊለበጥ ይችላል። ከዛ በተረፈ የሰው ልጅ ባዶ እጁን እንደመጣ #ባዶ እጁን ይመለሳል። ይህ አልገባንም። ይህ ሊገባን ይገባል።
 
ትውልድ በሰብዓዊነት፤ በተፈጥሯዊነት በመከባበር እና በመረዳዳት ይቀጥል ዘንድ መትጋት ብቻ #መሰልጠንን ያመለካትል። ከዚህ ባነሰ መራመድ ግን ከሰውነት እና ከተፈጥሯዊነት ውጪ ያደርጋል። 
 
ስለሆነም የኤርትራም መንግሥት ይሁን የኢትዮጵ መንግሥት ትርፍ መነጋገሩን፤ መናናቁን፤ መዘላለፋን አቁመው በስክነት ወደ ተፈጠሩበት የሰዋዊነት እና የተፈጥሯዊነት #መሃባቸው ይመለሱ ዘንድ ይህ ሁለተኛ ጸሁፌ ነው። ባለ ቅኔወቹ ጎንደሮች "ልብ ያለው ሸብ" ይሉታል።
ከሁሉ በላይ #ውህድ ማንነት ላላቸው ልጆቻቸው ሁለቱም ማንግሥታት ተስፋ ሊያስቡበት ይገባል። ግዴታቸው ነውና።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
• «ኤርትራ ሠራዊቷን በአስቸኳይ ከግዛቷ እንድታስወጣ እና ለድርድር ዝግጁ እንድትሆን ኢትዮጵያ ጠየቀች»
• «ኤርትራ "ትርጉም የለሽ ውዝግብ ውስጥ ለመግባት ፍላጎት የለኝም" ስትል የኢትዮጵያን ክስ አጣጣለች»
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/02/2026
 
በቃ! ጦርነት።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።