ከአሜሪካ #ፈርስት በሚደንቅ ሁኔታ እግዚአብሄር #ይቅደም!
"#አሜሪካን ዳግም #ታላቅ ለማድረግ፦ በአሜሪካ #ህይወት ውስጥ፦ መልሰን የምናስገባው #ታላቁ ነገር፤ #እግዚአብሄር ነው።" (አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶናል ትራንፕ።)
ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ። ይህ #የምዕት መሪ ቃል ፍፁም ቅዱስ፤ #የፀደቀም ቃለ ህይወት ነው - ለእኔ። የተባረከ የመሪነት መርህም፤ ቀናም ጎዳና ነው። ቃሉ ኪዳኑ ከፈጣሪ ጋር ነውና አቅሙን የአለም ንጉሥ ክርስቶስ ይስጥ። አሜን።
ለክቡርነታቸው ይህን ዕውን የሚያደርጉበት የህይወት ዘመን ይስጣቸው። አሜን። ይህ መሪ ቃል ከሞት በተደጋጋሚ ያተረፈ፤ ፈቅዶ እና ወዶ ለመረጠ ለቀባ ተደጋጋሚ የዕድል በር ለሰጠ አምላክ የቀረበ #የምስጋና #ስጦታ ነው። የመፈፀም አቅሙን፦ ክህሎቱን መዳህኒዓለም ይሰጥወት ዘንድ እንደ አንድ የግሎባሉ #ባተሌ ዜጋ በፍፁም ልቤ እመኛለሁ። ከቂም፤ ከበቀል የፀዳ መንፈሰ ደርጅቶ፦ መስመሩን አጥርቶ ፈጣሪ ይመራወትም ዘንድ እመኛለሁኝ።
ለእኔ እንደ ቃለ ምህዳን ነው ያዬሁት። ፍፃሜውን ያሳምረው ፈጣሪ። አሜን። በአንድም በሌላ የአለም አገሮች ሆኑ ዜጎች ከአሜሪካ ጋር ትስስር አላቸው እና። ስጋት፤ ጭንቀት፤ ፍርሃት የሰውን ልጅ በቁሙ ይፈትነዋል። በዚህ የአመራር ሽግግር ደስ ያላቸው እንደአሉ ሁሉ የፈሩም፦ የሰጉም ዜጎችም አገሮችም ይኖራሉና።
መሪነት #አጽናኝነት እንዲሆን ፈጣሪ ይርዳ። መሪነት #አረጋጊነት ይሆን ዘንድም አማኑኤል ይርዳ። አሜን። መሪነት ሰባዕዊነት እና ተፈጥሯዊነቴ ይሆን ዘንድ ከሞት ያተረፈ አምላክ ይርዳ። አሜን። ለዘመነ ክቡር ፕሬዚዳንትዶናል ትራንፕ እና ለአዲሱ ቲማቸው መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆን እመኛለሁኝ። ለአለማችንም #ሰላም ምግቧም፦ #ህይወቷም እንዲሆን እመኛለሁኝ። ትውልድ ጦርነት ሳይሆን #ሰላምን ብቻ ይወርስ ዘንድም ፈጣሪ ይርዳን። አሜን።
«የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን መንገዱን ያዘጋጃል።»
( ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
«ትራምፕ በመጀመሪያ የሥልጣን ቀናቸው በርካታ ትዕዛዞችን ለማስተላለፍ ቃል ገቡ»
«ለቁልፍ ኃላፊነቶች በትራምፕ እምነት የተጣለባቸው አስሩ ባለሥልጣናት እነማን ናቸው?»
Sergute©Selassie
20.01.2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ