ከፈጣሪ አምላክ ጋር #እርቀ #ሰላም ማውረድ ለሁሉም ይበጃል። #ለፋኖይዝምም ሆነ #ለአብይዝምም።

 

ከፈጣሪ አምላክ ጋር #እርቀ #ሰላም ማውረድ ለሁሉም ይበጃል። #ለፋኖይዝምም ሆነ #ለአብይዝምም
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

 
እንዴት ሰነበታችሁልኝ ማህበረ ክብር። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።
ዘመነ ብርሃነ ልደት፤ ዘመነ አስተርዬ በአማራ ክልል በትላልቅ ከተሞች
በሰላም መጠናቀቁን ሰማሁኝ። የአፍሪካ፤ የአለም፤ የኢትዮጵያም ርዕሰ መዲና በሆነችውበአዲስዬሜ እንዲሁ። በውነቱ ደስም ብሎኛል። 
 
በኦሮምያ ክልል ክልትምትም የሚለው የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት
ዓውደ ዓመታት አሁን ከሆነ በአማራ ክልልም መፈጠሩ፦ #መስተጓጎሉ በብዙ አዝንበት የነበረ በኽረ ጉዳይ ነበር። ሰሞናቱ ተመስገን ነው።
 
እርግጥ ነው በፈታ ደይሊ ዜና እንዳዳመጥኩት አልፎ አልፎ #ጠሽ #ጧ እንደነበር አዳምጫለሁኝ። የሆነ ሆኖ ግን በመላ የአማራ ክልል እና በሌሎችም ክልሎች እግዚአብሄርን ያስከፋ መስተጓጎል ባለመድረሱ ተመስገን ነው።
 
ጎንደር #የሎዛ #ማርያም ቀጣይ ክብረ በዓል በ21 አለና ከበዓለ እመቤታችን በዓላት ጋርም ግብ ግብ እንዳይኖር፦ በአጽህኖት ለሚመለከታቸው #ለፋኖይዝም አለቆች እና #ለአብይዝም የመንግሥት ሠራዊት አባላት አሳስባለሁኝ። 
 
ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር ግብግብ ትርፋ መትነን ነው። ለማንም አይጠቅም።
በውነቱ #መባረክን#መቀደስን#መመረቅን መፃረር የጤና አይመስለኝም። የሆነ ሆኖ ዕዓላቱ በአንፃራዊ ሰላም መጠናቀቃቸው፤ መልካም ነገር ነው። ደንግጬ ነበር በጦር ድሮን #ጥበቃ ይደረጋል፤ #እርምጃም ይወሰዳል ሲባል። ሦስቱም አካላት #ፋኖይዝም#አብይዝም#ሽመልዚም ትእግስቱን ሰጥቷቸው በዕላቱ ካለ ህውከት መጠናቀቃቸው
መልካም ነው። የፈጣሪ አምላክ ዓውደ ምህረትን ማወክ #ቅጣቱ የሚቻል አይደልም
 
በመጨረሻ ለሰማዕታት ቤተሰቦች ሁሉ #መጽናናትን እመኛለሁኝ። የተከፈለው መስዋዕትነት፤ የተዘጋው በር፤ የታቀበው መኖር፤ የተስተጓጎለው ደህንነት ዋጋውን መተመን አይቻልም። የእኔ በዚህ ዘርፍ ዝምታዬም አመክንዮዊነበር። ሃሳቤ ተጨማሪ #አቀጣጣይ ወይ #አድካሚ እንዳይሆን በማስላት በጥሞና ግራ ቀኙን ስከታተል ነበር የባጀሁት። 
 
ማስተዋል። ስክነት። ሁለገብ ጥንቃቄ። አድማጭነት። አቅምን መተመን፦ እግዚአብሄርን አላህን ማስቀደም እራስን ለማረም መድፈር፤ የተደጋጋሚ ግድፈት ባለሟል ላለመሆን መጠንቀቅ፤ ከሁሉ በላይ አንድ እስክርቢቶ ገዝቶ ያላሳደጉትን አቅም የአያያዝ ጥንቅቄ ማድረግ አትራፊ ጎዳና ይመስለኛል። ላም እረኛ ምን አለ ከተደመጠ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/01/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።