ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የህዝባቸው ክብር የደም ሥራቸው ነው።

እንኳን ደህና መጣችሁልኝ
ምርመራ፤
ክፍል ስድስት
ማጠቃለያ።
„እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“
መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮

ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ
የህዝባቸው ክብር የደም
             ሥራቸው ነው።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
05.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


 ውዶቼ እንዴት ናችሁ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ባለፈው ክፍል አምስትን በዚህ ነበር የከወንኩት …  

ይልቅ ሃዘን እጠብቃለሁኝ የአማራ አክቲቢስቶች፤ የአማራ ጦማርያን፤ የአማራ የሚዲያ ሰዎች፤ የአማራ ጋዜጠኞች አዲስ አባባ ላይ ምን እና ምን ይሆኑ ይሆን እንዲህ በቀል በሳንጃ አንቱ ሲሆን እላለሁኝ። እፈራለሁኝ። ማህዲሱ አይማረኛ ላልምርህ ከቤተ መንግሥት መንፈሴ የወጣ ዕለት ስላለ … ስጋቴ ከባድ ነው።

ጠረኑን እያፈነፈነ አደነው ነው። አብዝቶ ማድመጥ፤ አላምጦ መዋጥ ለዚህ ዳጥ እና ምጥ ዘመን ማስተዋል ቢሰጠን እላለሁኝ። ዛሬ አይታዬነም ምን አልባት መኖሩ ከተገኜ የዛሬ 10 /15 ዓመት ነው ይህ ውጥን በቅሎ፤ ነፍስ ዘርቶ ነባሩን ሁሉ ደርምሶ ወይኔን የሚያስተቃቅፈው።
  
ቅንነት ጸጋ ነው። ግን ቅንነት ፈተና ሲገጥመው አደብ ገዝቶ መመርምር ይጋባል እንደ እኔ ሰለ ኦህዴድ ስለ ፕ/ ለማ መገረሳ፤ ለመሆኑ ስለ ዶር አብይ አህመድ የሞገት ነበርን? ወደ 300 የሚሆን ጹሑፍ እኮ ነው የጻፍኩት።

ይህ ብሎግ በ2014 ነው ዝም ብዬ ሥሙን ሰጥቼ ያሰቀመጥኩት ነበር፤ ሥራውን የጀመርኩት ለአብይ አክቲቢዝም ነበር። ግን ገንግኖ ብዕሬንም ብራናዬንም ሞገተው፤ ህሊናዬ ድጋሚ ተፈተነ ይህ ድጋሚ ፈተና ለግንቦት 7 እስጠው ከነበረው የተስፋ ክብር ጋር ይተካከላል … መንፈሴን ነፍሴን የሸልምኩት ለዚህ ጥገናዊ ለውጥ ሰዋዊ እና ተፈጥሮዊ አቅሙ ከቀደመው የዶር አብይ ስብዕና ጋር አዋድጄ ተስፋ በመጣሌ ነበር። ባይጸጽተኝም ምስክርነቴን ግን አብልዞታል።

በግል ተስፋዬ ሲታመም ዝም ብዬ ለማዬት ግን ፈጽሞ አልፈቅደም። ቀጣይ መንገዶችን በተደሞ መከታተል ይገባል። እንሱም ሁልጊዜ ደጅ ጥኑ፤ ስገዱልን፤ አደግድጉልን ባይሉ መልካም ነው … ደግሞ አሉላቸው እነ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ … ታጥቀው ተነስተዋል … የደም ነገር ሆኖ እውነት ጋር ግብግብ እዬተገጠመ ነው … ያዝልቅ¡

ሌላው ብሮድ ካስት እንዳሻቸው እያሾሩት ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ሚዲያ ጎረቤታሞች ሳይሆኑ ልብ እና የደም ቧንቧ ናቸው። እሳቸው ለተነሱበት ጥልቅ ኦሮማማ ሲተጉ እኛ ደግሞ ለቀደመው ኢትዮጵያዊ ትውፊት መትጋት መብት ነው። ይሄን ማስፈራራቱን ግን ቢተውት መልካም ነው። እዮር ስላላ ከደጃቸው ፍርዱን ይሰጣልና … ዝቅታው እንጂ ከፈታውን እዮር አይወደውም፤ ይጸዬፋዋልና።  

ቅንነት ላለው ፍጡር እንዳለ መቀበል ምን ያህል እንዳስጠቀጠቀን፤ እደግመዋለሁኝ እንዳስጠቀጠቀን ተመክሮ ተደርጓል። ካለ ልጓም፤ ካለ ደንበር አቅም ማዋጣት የቀደመ የሁላችን ዘመቻ ነበር። ያ በመታመን ውስጥ ፍጹም እንኳን በተመጣጠነ ሁኔታ ተገባር ላይ መታዬት አልታዬበትም።

ኢትዮጵያዊነት ለፕ/ለማ መገርሳ መናጆ ነው … እሳቸው ነፍሳቸው እስኪጠፋ የሚተጉለት ለኦሮሞ ህዝብ ብቻ ነው። ለነገሩ መንገዱ ጠማዳ በመሆኑ እንጂ ኦሮሞዎቹ ባለ እጥፍ ድርብ ባለቤት ቢያገኙ መልካም ነገር ነው። ሁለመናችሁን ተክለ ሰውነታችሁን እንውረሰው፤ እንውረረው ነው መከራ ያመጣው …

ስለዚህ ያለፈው አልፎ መጪውን ቅንነትን ለማስቀጠል ሁሉንም ነገር መፈተሽ ያስፈልጋል። ግልጽነት በሌለው ጉዞ የድምጽ አልባዎች የኢትዮጵያ እናቶች እንባ አይደለም ማስወገድ መቀንሰ አይቻልም። እኔ አሁን ላይ ሳዬው ፍላጎታችን፤ ግባችን፤ ራዕያችን ምን እንደነበረ ሁሉ ይገርመኛል? ለኦነግ ዓላማ ነውን የታገለነው? ይህ እኮ ነው ያልገባን ሚስጢር።


 በደመሳሳው እንኳን ይህን የቀጣይ ዘመን መርዶ ቁጭ አድርገን አወያይተን አነጋግረን መፍትሄ ለመሻት እንኳን ፈቃደኞች አይደለንም። ምህንድስናው እሾኽማ ነው … አልገባንም፤ እንዲገባንም አልፈቀድነም … በምንም ሁኔታ ቀዶ ጥገና ቢደረግለት ፈቅ የሚል አዳኝ መንፈስ የለም። ቢቻልማ አልተከፈለንም ነበር እኮ ሌት እና ቀን እንዲያ ዶር አብይን ጠ/ሚር እጩ ሳይሆኑ ነበር ስተጋ … የነበረው። ከእኔ ሌላ ለኦህዴድ መልካም ዕድል የመኜ አልነበረም … በንጹህ ልቤ ነበር አቋሜን የገለጽኩት። ለካስ ኦነግ እንዲጋልብብኝ ነበር። እም!

ልብ የሚሰብሩ፤ ማህጸን የሚቀዱ፤ ኢ ሰብዕዊ የሆኑ ጭካኔዎች፤ ደንበር የሚጋፉ ንግግሮች ሲደረጉ እንኳን አይከፋቸውም። ለሰው ልጅ የሚሰጠው ክብር ለደሃውም፤ ለተገፋውም ጭነት ለበዛበትም ሊሆን ይገባ ነበር።

ኢትዮጵያዊነት የዜግንት እኩልነት እንጂ የዜግነት እንርቦና ሲሶ አይደለም። ስለሆነም ሙግቱ ይቀጥላል። ትናንትም ሥርጉተ - ሥላሴ እምሞግተው ስለ ዕውነት ነው የእናቴ ልጅ የለም፤ አንድም ቤተሰብ የእኔ ፖለቲከኛ አይደለም፤ ስለሆነም ከልጅነት እስከ እውቀት በማምንበት አቋም ላይ እቀጠልላሁኝ እንደ ኢትዮጵያ ፈርሼ ለመሰራት አልፈቅድም፤
የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ መንገድ አፍርሶ መስራት ነውና … እኔ እኔ እንጂ የትውስት ማንነት የለኝም፤ ቀይ የቤተ መንግሥት ምንጣፍ ስላማያስፈልገኝ የሚሰማኝን በድፍረት እና በሃቀኝነት እጽፋለሁኝ።

… ፍቅር መቻቻል - ምህረት - ይቅርታ - ከትናጋ አልፎ መሬት ላይ በተግባር መገኘት አለበት። ይህ ሲሆን በቀደመው የመንፈስ ቤተሰብነት መቀጠል ይቻላል … ቢያንስ ሰው ምን ይለኛል ይበሉ፤ ይሉኝታ እንኳን አልፈጠረላቸውም በአደባባይ ስለሚሰሩት የማንአለብን ተግባር፤ ማተብ ይኑራቸው ቢያንስ ፈጣሪን … ይፍሩ …

እነሱ ለክብሩ የሚጠነቀቁለት ህዝብ እንዳላቸው ሁሉ እኛ ደግሞ ባለቤት ለሌላቸው ህዝቦች የግድ ነው እንተጋለን ቢያንስ ይህን ቋያ፤ ይህን ቁር፤ ይህን መታበይ ፈጣሪ ያስታግሰው ዘንድ እንጸልያለን … የኢትዮጵያውያን ቀን እንዲያመጣ

የሚገረመው ነገር ዛሬ በመደዳ ለውጥ አደናቃፊ እዬተባለ ያለው ዘመቻዋጋ ያስከፍላል። ዛሬ ያልታያቸው ነፍሶች ነገ ጸጸትን ይሸከሟታል። ውዳሴ ከንቱ ለባለ ጊዜ ማሸከም ለምልዕት ዕንባን ፍትህ አይሰጥም።

ለዛውም የውጭ ግንኙነቱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ የሚታወቅ ነገር የለም። የተጀመሩ ነገሮች ብዙ ናቸው ውጤታቸው እና ስኬታቸው ወይንም ሊያመጡ የሚችሉት ጫናዎች ክፍት ናቸው በር አልባ …

በላዩም በታቹም ክፍት የሆነ አዲስ የካኪ ከረጢት እሰቡት ወገኖቼ … ተጨረሰ፤ ተጠናቀቀ፤ አለቀ የሚባል አንዳችም ነገር የለም … መጀመር ነው፤ መወጠን ነው ልክ እንደ አራስ ድመት … በዬቦታው መምድምድ። አሁን አንድ ዓመቱ ነው ጥገናዊ ለውጡ ማንቆለባባሱን ትቶ እውነት እና እውነት ምን እና ምን እዬሆኑ እንደሆን በማስተዋል መመርመር ያስፈልጋል …  

ለመሆኑ ጥገናዊ ለውጡ የረጅም ጊዜ፤ የአጭር ጊዜ፤ ሁለቱን የሚያገናኝ ኦፊሻል የሆነ ግንባራቸው የተስማማበት የፖሊሲ የጊዜ እቅድ አለውን? ፖሊሲ አለው ወይ ጥገናዊ ለውጡ? ወይንስ ፖሊሲው የተገመሰ ነው? ወይንስ ባለታሬና ቁንጮ ነውን?

ምክንያቱም የእትዬ ትግራይ ነገር እኮ አለ … እውነት ወደ ሆነው ነገር ቢያንስ መጣጋት የሚያስፍልግ ይመስለኛል … ወጥ ፓርቲ ስለሚባለውም በዬትኛው የመንፈስ የበላይነት? ሊሻሻሉ የተጀማማሩ ህግጋት ማነው ሰብሳቢያቸው? በምንኛው ይሆን እዬተቃኙ፤ እዬተጠኑ፤ ያሉት በኦሮማማ? አገር የፈረስ ግልቢያ ሜዳ አይደለም …

·       የዕለቱ ጭብጤ እና ዕድምታው። ማጠቃለያ ነው ስለ ጠ/ሚር ለማ መገርሳ።

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | -ሐበሻ

ይህችን ነገር ፈተሽ ትደረግ። መቼም ሞቶ ማውጣት አይቸግራቸውም … „በአዲስ ወግ“ ጠ/ሚር አብይም ጦርነቱን ያወጁት በዚህ ከላይ በለጠፍኩት ሊንክም  ውስጥም የመንፈስ ስምምነት ውርርስ መመልከት ይቻላል በፕሬዚዳንት ለማ መገርሳም። ምርጫ ዴሞክራሲ ገለመሌ የለም አይኖርምም … ብየ ነው እኔ እማስበው። ቢኖርም ኦሮማማን አውራ አድርጎ በማውጣት ነው የሚሆነው …

ጠርዝ ለጠርዝ ሳንጓዝ ማህል ላይ ተገናኝቶ እውነቱን መድፈር ያስፈልጋል። ወቀሳው የኖርንበት ነው፤ ፍረጃውም ህይወታችንም ነው፤ መገለሉም ደማችን ሆኗል። ስለዚህ ለኦነግ የልማታዊ ካድሬነት አለማጎብደድ መብታችን ነው። ቀይ ምንጣፍ ስለማንፈልግ … እነ እንደልቡ ሞገደኞቹ የሚሰማነን እንናገረዋለን …

ሌላው ልብ ያልተገጠመለት ልባም ማሰብ የሚገባው … አሰባሳቢው ሞቶ አሁን ላይ  ስሜነኛ ፖለቲካን በሰልት ማግለልና ማደከም ነው የተያዘው። ይህ ፍሬ ነገሩ ነው። ሰሞኑን የባህርዳሩ ጉባኤም ይኸው ነው ዕድምታው።

ይህ እንግዲህ „ከኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፤ ስንኖር ኢትዮጵያ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን፤ እኔም አንተም አንቺም ኢትዮጵያዊ ነሽ“ የባጀው የ4ኪሎ ስብከት ስክነቱ ሙቀቱ የሚለከባት እግረሙቅ ነው።

ግርባው ብአዴንም ለመናጆ ስለመፈለጉ ልብ ቢኖረው በምልሰት ኪሳራውን አስቦ ቀጣዩን ቢያንስ ከሥር ለመከተል ልብ ይሰጠው ነበር። ለነገሩ የፌድራሉን ጫና ተጭኖት እንደጎበጠም ከሆነ ምርኩዝ ቢጤ ቢያፈላልግ መልካም ይሆናል። ክትክታ ፍለጋ ቢሞክረው …  ለነገሩ ከቁጥርም የሚያስገባው የለም። በቃ እንደ ዘንቢል የተገዛውን ዕቃ ለመሸከም … ለመጫን የፈቀደ ነፍስ ሲጥ እስኪል ድረስ አሳምረው ይጩኑታል … ለማ የዋዛ … ምድር እንደሳቸው ዓይነት አልፈጠረችም - ለዘመናችን። ቀዳዳው እዬበዛ አስቸገራው እንጂ …

ቀድሞ እኔን እዬደገፋኳቸውም እነሱን አታውቋቸውም እል ሁሉ ነበር … ግን በ በ አውንታዊ አቅማቸውን ነበር። ወደፊትም ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳን የሚያውቅ ነፍስ አይኖርም …

ሲያሰኛቸው ለሽ ሲያስደርጉ፤ ሲያሰኛቸው ዱብ ዱብ ሲያስደርጉ፤ ሲያሰኛቸው ማራቶኑን ሲከነዱ … ሁሉም በዓይነት ቡፌው ተዘርግቷል … አንድ ጋዜጠኛ „ዴሚግራፊ“ ስለሚለው ጽንሰ ሃሳብ እንኳን አጀንዳው ሊሆን አለመፍቀድ ምን ዓይነት ፍላጎት? ምን ዓይነት ግብ?

 እና ተግባር ያለው ስለመሆኑ የዴሞግራፊ ፋሽስታዊ ራሲስት ስሪት ባለዬሁህም ባልሰማሁህም መሸብለል በአንድ ጋዜጠኛ ሰብዕና ውስጥ አንከረባብሰው ምን ያህል በልብ እንደተነጠፉ የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳን የተደማጭነት ልክ ያሳያል። ስንት የቀውስ ዓይነት ነው ያለው … እንዴትስ ይቃናል እንዲህ እዬተሸሞነሞነ ….
  
በዬዘመኑ … ለእውነት ግርዶሽ እና ክትር ሲፈጠር አልተሰራለትም። እውነት እውነት ነው። የኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ሙያ ከእውነት ጋር በዬዘመኑ እዬተፋጠጠ የግንባር ስጋዎችን ሰማዕትነት ተደራቢ ሆኖ ዋጋ ያስከፍላል … ሁሉም ሰው ዕውነት ቢኖረውም ሰው ይህን ያህል ፍዳ አይከፍልም ነበር።

የሆነ ሆኖ ቤተ-  መንግሥት እና መንፈሳቸው እንዲህ ይለናል … በዚህ አገላለጽ ሌላው ከራሳቸው ግንባርም አቅም ያለው ሰው ሊያስተናግዱ እንደማይፈቅዱ ነው የሚነግሩን፤ ይህን ፕሬዚዳንት ለማ ነው የሚሉት … 

„ኦሮሞ ማወቅ ያለበት፣ እዚህ በተመንግስት ውስጥ እናንተንም ጨምሮ አንድ ላይ ነው የገባንበት ዛሬ፡፡ የኦሮሞ ቤተመንግስት ልናደርገው አይደለም፤ የሀቅ ቤተመንግስት፣ የእውነት ቤተመንግስት ሊያደርገው ነው ኦሮሞ የገባበት እንጂ፣ ኦሮሞ ብቻ የሚዘፍንበት ቤተመንግስት ለማድረግ ከሆነ እኛም የትናንትናዎቹን ነው የምንሆነው፡፡ 

እሱን አንፈልግም እኛ፡፡ እሱን አይደለም የምንፈልገው፡፡ በህግ ከሆነ፣ በምርጫ ከሆነ፣ በስርዓት፣ በህግ ከሆነ ዶክተር ዐቢይ ከዚህ ቤት ውስጥ መውጣት በሚያስፈልገው ጊዜ መውጣት አለበት፡፡ 

በጉልበት ሊቀመጥ አለበት ብለን አናምንም፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ [ዐቢይ] እዚህ የገባበት፣ ማንም ሰው መጥቶ በጉልበት፣ እሳት አንድጄበት ነው የማስወጣው ቢል፣ እንሞታታለን እንጂ አንለቅም፤ እንሞታታለን እንጂ፡፡ ይሄ የስልጣን ጉዳይ አይደለም፤ ይሄ ለስልጣን ስለ መስከርም አይደለም፤ ዲጊኒቲ፣ የኦሮሞ ክብር ጉዳይ ነው፤ የኦሮሞ ልጆች ክብር ጉዳይ ነው፡፡“



ለዚህ ክብር እኛ መከራችን ስንበላ፤ ስንሞግት ባጅተናል አቤቶ ብአዴን መላ ሁኔታውን አስርክቧል፤ ታሪኩንም ጭምር አሳልፎ ሰጥቷል። ዛሬ ሥልጣኑ ተጥቅልሎ በእጅ ሳላለ ያሻቸውነው የማድረግ ሙሉ መብት ተስጥቷቸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ነው አይሉም ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ „የኦሮሞ ክብር ጉዳይ ነው፤ የኦሮሞ ልጆች ክብር ጉዳይ ነው፡፡“

ሰለዚህ ለዚህ አብሮ መሰለፍ አቅም ማዋጣት ይገባልን? አደብ ገዝታችሁ መርምሩት። ዛሬ የተሰለፉት አበረው የተደመሩት የፖለቲካ ሊሂቃን ሆኑ ጋዜጠኞችም የመሠረቱት ለኦሮሞ ክብር፤ ለኦሮሞ ልጆች ክብር ነው። በቃ።

ብአዴን እነሱ ለኦሮሞ ክብር ይህን ያህል ጉልበታም አቋም ሲኖራቸው፤ ይህን ያህል ሌት ተቀን ለኦሮሞ ልጆች ልዕልና ሲታጉ እሱ የት ነው ያለው? ጁቢተር ላይ ሜርኩሪ ላይ ወይንስ ኡራኖስ ላይ? ምንድን ነው እየሠራ ያለው? ያ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ከሱማሌ ክልል የተፈናቀለው ወገን በአዲስ አባባ እና በዙሪያው ሌሎቹ 6 ሺህ  አዲስ አበባ ከተማ እንዲሠፍሩ የተደረገው ለኦሮሞ ክብር፤ ለ ኦሮሞ ልጆች ክብር ሲባል ነው የመነገረን። ሰንፎ ላለመታዬት፤ በሁሉም መስክ ክብርን ስለማስከበር? ምን አለ በዚህ ውስጥ ምንዱባዎችን ቢያስቡ?

ካቢኔው ሌት ተቀን የሚታገው፤ መከላከያው አገሩ የሚጠብቀው፤ ደህንነቱ አገሩን የሚጠብቀው፤ እያንዳንዱ ዜጋ በሙያው ሌት እና ቀን የሚንደፋደፈው  ለኦሮሞ ህዝብ ክብር እና ለኦሮሞ ልጆች ክብር ነው። ይህ ነው አትናገሩት፤ አትውቀሱት፤ አትተቹት እዬተባለ ዲስኩር የሚነገረው።

በዛ በቤተመንግሥት ዙሪያ ጥበቃ የሚያደርገው ሁሉ ለኢትዮጵያ መሪ ሳይሆን  ለኦሮሞ ክብር እና ለኦሮሞ ልጆች ክብር ነው።  


 „የሚሰራው ነገር እርባና የሌለው፣ ጥፋትና ስህተት ከሆነ የራሱ ስህተት ብቻ አይደለም፣ ወደ ኦሮሞ ነው የሚመጣው፡፡ እሱ እዚህ ፍርሃት ካሳየ፣ ፍርሃቱ የሱ ብቻ አይደለም፤ ኦሮሞን ፈሪ፣ ውዳቂ ያደርገዋል፡፡ 

ይሄ ብቻ ነው እንጂ የተለየ ኪኒን ተሰጥቶት አይደለም ለሁሉም፡፡ አሁንም እዚህ ወንበር ላይ ሁለት ወይም ሶስት  ዓመት መቀመጥ ሳይሆን፣ ስርዓቱ መለወጥ አለበት፤ መለወጥ መቻል አለበት፡፡ ይህም ከፍተኛ ድጋፍ ይፈልጋል፡፡ የምሁራኖቻችንን ድጋፍ ይፈልጋል፤ የህዝባችንን ድጋፍ ይፈልጋል፡“ ይሄ የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ንግግር ነው።

ድጋፍ የሚፈልጉት ይህን ሥልጣን ለማስቀጠል ከ ኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ከ ኦሮሞ ህዝብ እና ከ ኦሮሞ ሊሂቃን ብቻ ነው? እና ታዲያ ምን ባዮች ነን?፡አለቅላቂ? አንጠፊ? ደጅ ጠኝ? ምን እኮ ምን? እኛን እኮ አይፈልጉንም - ፍሞ!

„ስርዓቱ መለወጥ“ የሚሉት? ከኦሮሞ ህዝብ እና ከኦሮሞ ሊሂቃን ከሆነ ለዚህ ማህበረሰብ ብቻ የሚሆን ምቹ ሁኔታን መፈጠር ነው እኔ የሚረዳኝ። አሁን ይሄ ንግግር አብሮነትን ኢትዮጵያዊነት መንፈሱ ብናኝ ነገር ይጋብዛልን?   

ሥልጣኑ የተፈለገበት ምክንያት የቡራዩ ጭፍጨፋ፤ የጌዲኦ ቀራንዮ፤ የለገጣፎ ለገዳዲ ጎለጎታ፤ የሻሸመኔው ፈርኦናዊነት እንዲዳፈን የሚፈለግበት መሰረታዊ ምክንያት ለኦሮሞ ክብር፤ ለኦሮሞ ልጆች ክብር ሲባል ነው። መከራው ገፍቶ እነሱ ከቤተ መንግሥት እንዳያስወጣ። ያ ከመጣ „እንሟሟታለን“ ነው የሚሉት።

የተደፋ ቢዳፈ፤ የተጎዳ ቢጎዳ፤ ያለቀስ ቢያለቅሰ፤ የተበደለ ቢበደል ለኦሮሞ ክብር፤  ለኦሮሞ ልጆት ልዕልና የማድረግ ብቃት እና ክህሎት ሲባል መዳፈን አለበት። ለዚህ ነው የሻሸሜነው ወገን ተገድሎ ተዘቅዝቆ ሲሰቅሉት የመንግሥት ሚዲያን OMN ጨምሮ ውሾን ያነሳ ውሾ የሆነው …  

ለዚህም ነው ቡራዩ ላይ ያሁሉ ሰቆቃ እንደዛ ሆኖ የውሽማ ሞት ሆኖ የቀረው። ሄደውም አላዩትም ቀድሞ ነገር። ሌላው ለተጎጂዎች መርዳት እንኳን አይፈቀደም። እኔ ይህን ሳስብ ህሊና የት ሄደ እላለሁኝ።

አሁን እነ አለዝዜ ተሰልፈው ወዳሴውን ሲደረድሩ … አትንኳቸው ሲሉ … መከራውን ቢጨምረው እንጂ አይቀንሰውም … ነገ ከማይወጣበት መከራ ይደረሳል። የሚራራ ነገር የላቸውም። ርህርህና እኮ አክብሮት ለሰጠህ ቢያንስ መኖር ነበረበት …

ለዚህም ነው የቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው አሟሟት ደመ ከልብ ሆኖ የቀረው፤ ለዚህም ነው የጌዴኦ ሰቆቃ በዛ መልክ በማጎሪያ ካንፕ ድራማው የተከወነው፤ ለዚህም ነው የሰበታ፤ የለገዳዲ ለገጣፎ ጉዳይ የሚዲያ ጫጫታ የተባለው …

ለዚህም ነው አዲስ አባባ ላይ 5 ንጹሃን ሰማዕታት ጉዳይ መንግሥት አገር ላይ እንደሌለ ሁሉ ደም ከልብ ሆኖ የቀረው ለማን ሲባል ለኦሮሞ ክብር እና ለኦሮሞ ልጆች ክብር ሲባል … ጉዳዩ በ አጀንዳ መወያዬት አይፈቀደም? ደግሞ ተገድሎ ተገኜ የሚባለው ማን ይሆን ተረኛው? ወዮልሽ አገሬ ነው!

እንደዚህ መሰል ኢ-ሰብዕዊ ድርጊቶች መናገር፤ ማጋለጥ፤ በዛ ላይ ትንታኔ መስጠት ወንጀል ነው ያስከስሳል፤ ያስቀጣል። ስለዚህ የልብ ልብ የተሰጣቸው ደግሞ ጭካኔያዊ ተግባራቸውን ይቀጥላሉ ማለት ነው፤ ህግ እና ህጋዊነት፤ የመኖር ዋስትና እና ቀጣይ ተስፋ ከዚህ አንጻር ነው ሊታይ የሚገባው።

ማፈናቀሉም ይቀጥላል፤ ግፉም ይቀጥላል፤ እስሩም ቀጣይ ነው፤ ግድያውም ቀጣይ ነው አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ በኦሮሞ ሥም አይፈለገም እና … ይህን የሚያጋልጥ፤ ስለዚህ ጉዳይ የሚጽፍ ጋዜጠኛ እና ጸሐፊ ከአንግዲህ አንድ መስመር ብቻ ነው መከተል የሚኖርበት ማለት ነው … ዝም ማለት!

የበሩ መዘጋት ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ በጥሞና ማዬት ይገባል። አንዲት ነቁጥ  የኦሮሞን ሊሂቃንም መናገር፤ መውቀስም ወንጀል ነው። እነሱ ግን ዘፍጥረትን ኢትዮጵያ መሬት ላይ አንድደው አመድ ሲያደርጉት ነኪ የላቸውም። እንዲያውም ይህን አንዲያሰተምሩ መድረክ ተመቻቸ … ጭካኔ እዬመራህ አላዬሁም፤ አልሰማሁም ማለት የህሊና ሪህ ነው። 
  
ይህን ደግሞ የሚገፈጥ ጀግና ሲገኝ ደግሞ መከራ ነው። ብስጭቱ ይሄው ነው እንዴት እኛ እንወቀሳለን? እንዴት እኛ እንተቻለን የኦሮሞ ልጅ ሆነን? የኦሮሞ ክብር፤ የኦሮሞ ሞገስ፤ የኦሮሞ ጥንካሬ በእኛ ነው የሚለካው ነው የሚሉት ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ።

ከእነሱ በፊትም የኦሮሞ ህዝብ ነበር አሁንም አለ። አጤ ሃይለሥላሴ እኮ ኦሮሞ ናቸው፤ ኮ/ አብዲሳ አጋ፤ ሃይለማርያም ማሞ የጦሩ ገበሬ ፈረሱን እንደሰው አስታጠቀው ሱሪ ብልጅነታችን የተማርነው ነው። አይደለም ወይ? ፓን አፍሪካን የመሰረቱ፤ በተመድ ሰፊ ድርሻ የነበራቸው አጤው ነበሩ። ሌላው ሁሉ ቀርቶ ማለት ነው። የኦሮሞን የማድረግ አቅም በእነሱ ጥብቆ ብቻ ነው የሠፈሩት።  

እኔ የጢቾን /አርሲ/ ሴቶች አውቃቸዋለሁኝ፤ በ4ሳምንት የክ/ሀገሩን ኮታ ብቻ ሳይሆን ከኮታ በላይ ነበር የሠራነው። እነሱ እንደሚነግሩን አይደለም የኦሮሞ ህዝብ የኦሮሞ ህዝብ ወተት ነው። ሰው ጠል ያደረጉት እነሱው ናቸው። እነሱው ሊሂቃን ልጆቹ ናቸው የግድብ ገደል ሠርተው ፍዳውን እያስከፈሉት ያሉት። ትናንት ደም ገበረ ነገ ደግሞ በቀልን እያበቀሉለት ነው ልክ እንደ መልካም ዘር። ለወደፊቱ መከራ ነው እያጩለት ያለው …

ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ በዚህ ውስጥ እኛ ብንደክም፤ እኛ አቅም ብናጣ እንኳን ክብራችን ስለሚነካ ጸጥ ረጭ ማለት ነው ያለባችሁ እሰከነ ገማናችን አክበራችሁ አውድሳችሁ እጬጌ በሉን ነው የሚሉት። ምክንያቱም ባለፈው አንድ ዓመት መላኮች አለመሆናቸውን፤ የበታቾቻቸውንም አካላት ስላልገሩ መከራውን አይቷል ይህ ህዝብ። ከዴሞክራሲ በፊት የመኖር ዋስትና ያግኝ ህዝብ …

በቃ እነሱ የፈለጉትን ያድርጉ፤ የፈለጉትን ኢ - ሰብዕዊ ሁኔታ ይፈጥሩ፤ ህግ ይተላላፉ በስንፍና በትችት እንዲቀርብባቸው አይፈልጉም። የዚህ ችግሩ እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ „ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም“ የሚለው ነገር የህሊና በሽታ ሆኖባቸዋል።
ያልሆነ አመክንዮ ነው በሥነ - ልቦናቸው ላይ ጫና የፈጠረባቸው። 

ሰው መሆናቸውን እራሱ እረስተውታል። ማስተባበያውን ሲናገሩ … እዬተበሳጩ ነው የሚናገሩት … እዬተናደዱ ነው የሚናገሩት … ንዴቱ ቁጭቱ በማን ላይ? የተሰጠን መታመን በመቅበር ወይንስ መተመንን ድርብ ሸማ በማልበስ?

ራስን መጠዬቅ ይጋባል ሌላን ከመክሰስ፤ መጸጸት፤ መቆርቆር እኮ  የአባት ነው … ይህ ሁሉ ህዝብ እዬተፈናቀለ ሜዳ ላይ ፈሶ ይህን ያህል መዘመን?ለምን ይሆን እንዲህ አድረገው የኢትዮጵያን ህዝብ እና  የኦሮሞ ህዝብን፤ ሙሁራኑን ለመነጠል ያሰቡት? ምን ሲሉ ትዝ አላቸው?  የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት በተለዬ ሁኔታ ይመለከቱታል?

 „ይሄ የስልጣን ጉዳይ አይደለም፤ ይሄ ለስልጣን ስለ መስከርም አይደለም፤ ዲጊኒቲ፣ የኦሮሞ ክብር ጉዳይ ነው፤ የኦሮሞ ልጆች ክብር ጉዳይ ነው፡፡“

እንግዲህ ድክመትን ለሚገልጽ በዚህ ውስጥ አስጊ የሚባሉት ንዑዳን በዛቻ፤ በማስፈራራት፤ በእገታ ውስጥ ይሆናሉ ማለት ነው። በዶላር እዬተከፈላቸው ደግሞ የምክር አገልግሎት የሚሰጡት የሚዘምኑ የቤተመንግሥት ጩለሌዎች ደግሞ ወደ ኦዴፓ ካድሬነት የእነሱና የቤተኞቻቸው አልበቃ ሌሎችንም ጫና ስለመፈጠራቸው ህብር ዘግቧል። ፕሮፖጋንዲስትም ሆነዋል።

ሌሎችንም እጅ በመጠምዘዝ ላይ ስለመሆናቸው አዳመጠን … እኛ የታዘብነው እንዳለ ሆኖ ማለት ነው … የሚገርመው ነገር ግን በቃ የሰው ልጅ የራሱ ህሊና እና መንፈስ እያለው የሌላውንም ካለወረስኩህ እንደ ሃብት ንብረት ማለቱ ነው ገራሚው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቂልነት … የሚገርም ነው?

Ethiopia: "/ ብርሃኑ ነጋ የእስክንድርን እጅ ለመጠምዘዝ ይሞክሩ ነበር" - ክንፉ አሰፋ

Published on Apr 4, 2019

The warning for journalists / አዲሱን መንግስት የሚፈታተኑ ጋዜጠኞች ማስጠንቀቅያ ደርሳቸው

ኢንጂነር ታከ ኡማ ምክትል ከንቲባ ካቢኒያት የኦዴፓ ድርሻ
Published on Apr 4, 2019 /ካላስገደሏቸው ዕድለኞች ናቸው/

… እነሱ ምንም አይሆኑም … እንዲያውም አቅም ፈሪው ወረርሽኙ የሁሉም ስለሆነ በቀላቸውን ቢወጣላቸው አጤው ኦዴፓ ጫን ያለ እርምጃ ቢወስድም ደስታውን አይችሉትም። ሲያስደነግጥላቸው እሰዬው ነው።

·       ቅኖች ሆይ!

አላያችሁም በሂልተን የቃልኪዳን የሰነድ ስምምነት አብን ብቻ ሳይሆን የአማራን ሰፊ ህዝብ ሲወርፉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጭብጨባው ደርቶ ነበር። አሁን በሞቴ ምኑ ይሆን የሚያስጨበጭበው? በህገ መንግሥት አንደራደርም? 

ወይንስ ይህቺን ወንበር አታገኟትም አትሰቡት ይሆን? ብቻ ነገሩ ስውር ነው። አስቁምልንም ነው። አማካሪዎቹ እነሱ ስለመሆናቸው ደግሞ እራሳቸው ጠ/ሚሩ ነግረውናል። 
አብንም ወዮልህ ነው … ቀጣዩ ኢላማ እሱ ነውና። ወይ ከሁለት // ከሦስት መተርትር የለመዱት ማህንዲሶች ያስተርትሩታል ወይ ይቦድሱታል ወይ ደግሞ ያስከስሙታል … ጠብቁት።

የሄልተኑ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ንግግር ከጦርነት በመለስ ማናቸውን አቅሙን ተጠቅሞ የፈለገውን ለማድረግ መሰናዳቱን ይጠቁማል ኦዴፓ። በ አዲስ ወግም መሰሉ አይተናል። አሁን ተዚህ ላይ ይቅርታ ተጠይቆበታል ብላችሁ እንዳስቁኝ። እስኪ 500 ሺህ ያሰፈሯቸውን ወደ ቀያቸው ይምልሱ፤ አዲስ አባባ የ ኢትዮጵያም የ አፍሪካም መናገሻ ከተማ ናት ብለው መግለጫ ያውጡ።

ህግ ሽረህ ሌላ ህግ አውጥትህ ከአንቦ ከንቲባ አምጥተህ ሾመህ፤ ከላይ እስከታች ኦዴፓ አድርገህ በቀጥታ የአዲስ አባባ ህዝብ ተጠሪነቱ ለናዝሬት / አዳማ/ አድርግህ እንዴት እና እንዴት ነው ይቅርታ እና ምንትሶ የሚታሰበው፤ የልብህን ፈጽምህ፤ የነገውን ትልምህን ለማሳካት ደግሞ ሌላ አቅም ትቃርማለህ …

 ምን የሚሉት ይቅርታ ነው? ዓመት በ ዓመት ነው ይቅርታ። እነሱ እኮ የመሰከረም ጉባኤቸው ላይ ኦሮማማ ነው አይዲኦሎጂያችን ብለዋል እኮ። የሆነ ሆኖ እኔ እሰከ ሄልተኑ ስብሰባ ድረስ እስከዛች ቀን ድረስ እንዲህ ንግሥናቸውን ሰፍ ያደርጋቸዋል ብዬ አላስብም ነበር … እኔ ያ „ጃኬት እናውልቅ“ ሞቶ ሰለባ ነበርኩኝ እና …  

·       እኔኑ ስለሚሞግቱኝ - ክብረቶቹ።

በቅድሚያ ቅንነት እና ንጹህ ልብ የሰጠኝን አምላኬን አምሰግነዋለሁኝ። አይጸጽትሽም ወይ ከ2017 ጀምረሽ ስትሞግች እንዲህ ሲሆን ታማኝነትሽ ለምትሉት መልካም ነገር አድርጌ ምን ይጸጽተኛል?

ሊጸጽታቸው፤ ሊጎረብጣቸው፤ ሱባኤ ሊገቡ የሚገባቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ጠ/ሚር ለማ መገርሳ ናቸው። ወደቁ። የአሁኑ የሙት መንፈስ ማገገሚያውም ተሰውሮ የተያዘው ነገር ቀዳዳ ፈጥሮ መሰሉ መደናበር አይቀሬ ነው።  እንደ ድርጅት ደግሞ በቀደመው ሥሙ ስለሚሻል ኦህዴድ ነው ሊጎረብጠው የሚገባ። ታሪኩ በልቋል።
  
ታማኝነት ለራስ ሰብዕና ስለሆነ የማያበድሩት የማይበደሩት ነው። እኔ እኮ የቀረበኝ ነገር የለም። ሚዛኑ የቀነሰው ታማኝነቱን ያጎደለው ነው። ቢጠፈውም ቢለጥፈውም ቢቀረቅረውም ያው በዬቦታው ተሸጉጦ የተያዘ ዓላማ ከኖረ ቀዳዳ በቀዳዳ ነው … አዎና!
እራሱ እኔ የቤተ መንግሥቱ ዕደሳትን በጥርጣሬ እዬተመለከትኩት ነው። እዛ ውስጥ ስላሉ ቅርሶች ሙሉ እውቀት የኢትዮጵያ ህዝብ ሰለሌለው ምን ሊሆን እንደሚችል ከሰሞናቱ ሁኔታ ጋር አገናዝቤ አብዝቼ ሰግቻለሁኝ።
  
ቤተመንግሥቱን ኦሮማማን አውራ እና ተጫኝ ሊያደርጉት እንደሚችሉ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው….  ልባሞቹ ከ150 ዓመት በሆዋላ ሲያሰርክቡን የአጤ ቴወድሮስን ቁንዳላ እኔ ከዛው ቢቆይ ሁሉ ብዬ ነበር። መተማመን የለም - ዛሬ ላይ። በዛ ላይ ታሪካችን ይጠሉታል። የበታችነት ከኖረ መከራ ነው። የእኛነት ታሟል። እኛነትን ለማስጠጋትም በትውስት ነው ነገረ አለሙ።  

ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ የታመቀ ጉዳይ ነው ያለው። በጠሉት ማንነት ውስጥ ሆነው ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ማሰብ ይገባል። … ቃል እና ተግባር አራባ እና ቆቦ ናቸውና … ትትርናው ትጋቱ ለኦሮማማ ሃይልነት ነው። የአዬር መንገዱ ተርሚናል ሴሪሞኒ የታዘብነውን ታዝበናል … የሰሞናቱ የሚሊዬነም እንዲሁ ... 

·       ተያያዥ ምርኩዝ …

„የኢትዮጵያ ህዝብ ነገም ቢሆን ሊጠራጠረን አይገባምአቶ ለማ መገርሳ /OBN/“


እኔ ግን መጠርጠር አይደለም እዬፈራሁዋችሁ ነው። እኔ እፈራለሁኝ ለአላዛሯም ኢትዮጵያ ቅርስ፤ ውርስ፤ ትውፊት፤ ታሪክ፤ ባህል፤ ተደሞ፤ ዕድምታ፤ ቅኝት …. በጣም ነው እምፈራው … መታመን በሰው ልክ፤ በተፈጥሮ ልክ ሲሆን መልካም ነበር። 

ምንም እኮ ቅደመ ሁኔታ ሳናበጅለት በልቁ ሙሉ መንፈሳችን፤ ህሊናችን፤ ሁለመናችን አምነን ስናስረክብ። ሲሆን ሲሆን ሆኖ በመገኘት ኩራት በተሆነ ነበር፤ ያ ቀርቶ ደግሞ ለውጥ አደናቃፊ ጽንፈኛ እያሉ መለቅለቅ የህሊናን ዳርቻ አቅም ያሳጣል … አበለቁት ታማኝነታችነን …

ውሉ የመንፈስ የህሊና የነፍስ ነበር ፕሬዚዳንት ለማ መገረሳ ውል የለብኝም እንደሚሉት የሰነድ አልነበረም። በርቀት በጣም በርቀት ስለ ነፍሳቸው ግድ ይለን ነበር። ስለ ውሎ አዳራቸው ግድ ይለን ነበር። በሳቸው ውስጥ ግን እኛ አልነበረንም። ነበርን የሚሉ ወገኖች ካሉ መቀጠል መብታቸው ነው …

እኔ ሥርጉተ - ሥላሴ ግን በፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ መንፈስ ውስጥ አለመኖሬን አሳምሬ አውቃለሁኝ ወደፊትም ይፈቅዱልኛል ብዬ ስላማላስብ ተስፋዬን ቀብሬ የሚሆነው አያለሁኝ።

ታማኝነት ከእኔ ቤት ከነፍሴ በላይ ነው … እነሱ የገበጣ ጨዋታ አድርገውታል አገር ስለማለት … የስንት ሺህ ገናና ታሪክ የሆነች ብርቅ - ድንቅ - ወርቅ ባዕት ተቀብለው አንድ ብሄር ውስጥ ወሰደው ለመቀርቀር እፍ ግብ ይላሉ። ከቻሉ ይሞክሩት ካሰነበታቸው።

… እዮር በማለዳው ነበር ቁጣውን በመግለጽ ምልክት ሲሳይ የባጃው ከሹመቱ ዋዜማ ጀምሮ …. መሬት ከሁለት ተገመሰ፤ ቤት ከሁለት ተተረተረ፤ መቀሌ አካባቢ መራድ ታዬ፤ ጅግጅጋ እሳት ከሰማይ ዘነበ፤ አንጅባራ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ዓይናቸው ደፍሮ ለማዬት የማይችለውን ታመራት አንድዬ አሳዬ … ሰሞኑንም ከጋዜጠኛ እስክንድር ጋር ፉክክር ለማድረግ ቤተ መንግሥት ላይ የጥድፊያ ጉባኤ ሲያሳናዱ ዓለምን ያሳደም ጥቁር መከራ መጣ። ፈጣሪም አልተደሰተባቸውም። ቀራንዮ የዋለበት ፍቅር ሲነድ ምን ይሁን?
·       ማግለል። ማስገለል።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን እውነቱ እና ሃቁ ላሳቸው ለፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ማለት ከኦሮሞ የደም ዝርያ የሌለው ወገን መንፈሳቸው አያስጠጋም። ይኮሳኮሳቸዋል። በዚህ አያያዝ ሃቅን በመደለዝ ጊዚያዊ ድል ቢያገኙም በቀጣይ ግን ታሪክ ሠርቶ የአገር ታቦት ሆኖ ለመዝለቅ አቅም ያለው ቋሚ እና ጽኑ መንፈስ ለማግኘት ይቸግራል። 

እሳቸው የተመሰጡበት፤ መስጠረውም ያያዙት የኦሮማይዝድ ማኒፌስቶ እና ስኬቱም እዮር ይዳኘዋል። የኦሮሞ ልጅ ሌላውን ሲዳ፤ ሲድል፤ ሲጠፋ፤ ፍትህ ሲያጓድል አይጎረብጣቸውም ወይንም አይሰነጥራቸውም።  

ይህን ደግሞ ከመሰከረም ጀምሮ አስተውለናል። ራስን መመርምር ለፈጣሪም መመቸት ነው ሁሉም አላፊ ነውና። ሰው ሆኖ በመፈጠር ውስጥ የቃላት መወድስ ሳይሆን በመሆን ውስጥ ያለ የደግነት ነገር መልካም ነው። ይህ ደግሞ ለማንም ሳይሆን ለራስም ህሊና።

ከእውነት ጋር መኖር ያፍልቃል - ያደመቃል - ያበለጽጋል ያበቅልላ - ያሰብላል። ከዚህ ማፈንገጥ ደግሞ ይነቅላል፤ ያከስላል፤ ያስረሳል፤ ያፈልሳል … ምርጫው የባለቤቱ ነው … ያ እንዳለፈው ሁሉ ዘመነ ጭጋግ የተሸከመው ዘመነ -ኦሮማማ ያልፋል። በፈጣሪ ተስፋ አለንና … የሰውንማ በዓይነት አዬነው … 


መሪ ሆኖ ወጥቶ እኔ የዚህ ወገን ብቻ ነኝ ማለት ነውር ነው … ለዛም ብቻ መትገት ጸያፍ ነው። ራስን ማገትም ነው። እኔ የእኔ ብቻ ነኝ ማለትም አይቻልም … ወይ „ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽ ባላሰፈርሽ ነው“ የሚባለው። 

·       ግራሞት።

 

ግራሞቴ የፕሮፖጋንዲስቱ ሰልፍ ነው። ለማስተባበል ህሊናን እንደ አወጣ በጨረታ ቸብችቦ ድርጎ ተሰፋሪው በረካከት። ራሱን ያሳመነው ለራሱ ይዋጣው የነገን ጸጸት ከቻለው። አላምጦ መዋጥ ያስፈልጋል።

 

ችግሩን እዬገፉ እዬገፉ ወደ ህወሃት ከመወስድ አፍንጫ ላይ ያለውን ገመና ዘርግፎ መፍትሄ መንገድ መውጫ ማሰብ ይገባል። አሁን እኮ ህዋህት የለም … እውነት በዬሙያው የተሰማራው አገርኛ ባለጉዳይ … ለጠፍ መሆኑ ይገርም ነው እስከ ወዲያኛው … ከሚገርሙኝ ሰዎች አንዱ አቶ ስዩም ተሾመ ናቸው … በዬት በዬት ዙረው የተሰማሩበትን ተልዕኮ አቅም ለማሰጠት ዙሪያ ገባ ሻታ ሲዞሩ ውለው እንደሚያደሩ በዝርገት እያስተዋልን ነው …  እነሱን እርሷቸው ስለ ኤፍረት ምንትሶኦ ቅብጥርሶ አንሱ አሉ ሆነ ነገር ዓለሙ … የሆነ ሆኖ ጊዜያዊ የዕብለት ጋብቻ አይዘልቅም ይናዳል … ዕውነት ሸቀጥ አይደለም እና …

 

እኔ የሚታዬኝ ከመቼውም የከፋ ሁኔታ ላይ መሆናችን ነው። ስለምን ሰው አልገባውም። በፍጹም የጉዞው እና የተጓጓዡ አመክንዮ ብልትን አልተረዳውም። በጣም የመረረ ተጋድሎ ይጠቃል ይህን ዘመን ብልቱን ለማወቅ።

ይህን ያህል ህዝብ ከመኖሪያ ቀዩ ተፈናቅሎ፤ እርዳታ እንዳያገኝ ታቀዶ እየተሠራበት ምንም አይመስላቸውም የኦሮማማ ልማታዊ ጋዜጠኞች፤ ቆራጣ ነገረ ሃዘኔታ የልባቸው መሰበር አይታይም እንዲያውም ድፈረት ነው እማዬው … እነሱ ስለ ክብር እና ዝናቸው ነው የሚጨነቁት … ውለታም ዋሉልን ባዮች ናቸው … የሚገርም እኮ ነው …

ክብር እና ዝና እኮ ዕውነት እና ፋክት አይሆንም። በፍጹም! ያ ሜዳ ላይ የፈሰሰ ህዝብ፤ አራስ፤ አዛውንት፤ የልጆች ዕንባ ላይ ሆኖ አሁንም ቅድምም ኬክ ቆረሳ፤ አሁንም ቅድምም ከረባት እና ገበርዲን ሸር ጉድ መራራ ነው። ጥቁር ነበር ሊለብሱ የሚገባቸው … ሁለቱም ጠ/ሚኒስትራት፤ ጠላፊውም ተጠላፊውም ጣማረኛዎቹ።

በሚሊዮን የሚገመት ህዝብ ተፈናቅሎ፤ ድህነቱ ታክሎ ይህን ያህል በስብከት ፓለቲካ የተሰወረን ፍላጎት ዕውን ለማድረግ መታከት ለእኔ እንደ ሥርጉተ - ሥላሴ ከንቱነት ነው። ወደ እውነት የመጡ ዕለት ሙግቱ ይቆማል በስተቀር ግን እሞግታቸዋለሁኝ …

ቢመራቸውም የነገረ ኢትዮጵያ ልቅና፤ ልዕልና፤ ተፈሪነት አዲሶቹ ገዢዎች ባለ ኦሮማማ ማንፌስቶኞች … እና ቤተኞች … ቅልጥ እና ቅብጡን ያስነኩት እኛ ደግሞ በብዕራችን እንናገራለን …  
እንለዋለን በድፍረት እና በእርግጠኝነት  … አንዲህ በአክብሮት … እና በተመስጦ ኢትዮጵያን ውስጠትም እንቃኘዋለን እንዲህ ብለን …   
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
·       ማጠቃለያ …

የኔዎቹ ነፍሶቼ ዘለግ ያለውን ሙግት አብረን ሰነበትንበት። ከእንግዲህ እንዲህ ፍትፍት አድርገን እንጂ እንደወረደ የሚሰጠን አጠውላጊ ክኒን አንወጥም። እኛም ለድንግኒታችን ለክብራችን ግድ ይለናል እና።

መታመንም ቁርጥም አድርጎ ለበላ ነፍስ አብዝቶ መጠራጠር ይገባል። የሚያምኑ ይመኑ መንገዳቸውን ጨርቅ ያድርግላቸው። እኛ በማር የተለኮወሰ የኦነግ ዓላማ ለማወራረድ አቅም የለንም። ለመፈራረስ ፈቀድም ይለፍም አንሰጥም። 

ቢያንስ ልባችን እና መንፈሳችን እናሸፍታለን። ያን የኦነግን ዓርማውን እራሱ ለማዬት እኔ ዓይኔ አይፈቅድልኝም። ኢትዮጵያን ባላንጣ ላደረገ መንፈስ አሽኮኮ የማድረግ ግዴታም የለብኝም። ሰማይም ይፈርዳል። የማሬያም መቀነት ፍርዱን ያሰጣል። የቃል ኪዳን መንበር ነውና።

ይልቅ አንዲት እምወዳት መንፈስ አለች። የደልዳላዋ ቀዳማዊት እምቤት ቢሮ „ለባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“ እስካሁን እንከን አላገኘሁበትም። ስለዚህ የመንፈስ የልብ ሽፍትነቱ አይመለከተውም ማለት ነው።

መንፈሱ ስለመጠለፉ እኔ ከሀምሌ ጀምሮ ጽፌያለሁኝ። ወንበሩ ባዶ መሆኑን በህልሜ አይቻለሁኝ። የአሁን ያዙኝ ልቀቁኝ መሰረታዊ ነገር ስለተነቃበት ምህንድስናው ነው።

 በጉዞው መንገድ ላይም የትራፊክ አደጋ ስለደረሰበት ነው፤ በቀጣዩ ሰሞን ለማጠፋፋት የለበጣ ጉዞ እናያለን፤ እናዳምጣለን … መጥኔ ብለናል ለማያልቀው  የስብከት አነባባሮ … ነገ በሌላ ጉዳይ እስክንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑልኝ ክብረቶቼ!
መመከቻ!
የሚኒስትሮች ሹመት – ሳይድበሰበስ! (ዮፍታሔ)
የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን አዲሱ መዋቅር የሹመት ዝርዝር:- በጥቂቱ
ይህስ ምን እንበለው ይሆንይሉኝታ የሚባል አልሰራላቸውም።  

1. እናትአለም መለስ …ዋና ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
2. ነጻነት አለሙ…………/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
3. ሳሙኤል ከበደ ……../ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
4. ዮሚ ተመሰገን…….……../ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
5. ካሳ /ሰንበት…….. አማካሪ (ኦሮሞ)
6. ውብሸት ወልዱ……..ልዩ ረዳት (ኦሮሞ)
·         ህመሙ በዓይነት ነውቡፌ …

https://www.youtube.com/watch?v=ejc6-XW19Vk&t=5s

The warning for journalists / አዲሱን መንግስት የሚፈታተኑ ጋዜጠኞች ማስጠንቀቅያ ደርሳቸው

 ኢንጂነር ታከ ኡማ ምክትል ከንቲባ ካቢኒያት የኦዴፓ ድርሻ

ዶር ታደለ ገብረመድህን ወርዶፋ ትምህርት ቢሮ ሰበታ ቢወለዱም ለረጅም ጊዜ የግርባው ብአዴን አባል የነበሩ አሁን ክንብንቡን አውልቀው አደ ኦዴፓ የተዛውሩ

እንጂነር ሽምልስ መሬት ልማት ኦዴፓ

ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ኮንስትራክሽን ኦዴፓ

ዶር ዮናስ ጫላ ጤና ቢሮ ኦዴፓ

አቶ ዘውዴ ቀጸላ ከንቲባ /ቤት ኦዴፓ

አቶ ደረጀ ፍቀዱ ፕላን ኮሚሽን  ኦዴፓ

አቶ ደረጀ ፈቃዱ ፕላን ኮሚሽን ኦዴፓ

ኢንጂነር አለም አስፋው ወርዶፋ አካባቢ ጥበቃ ኦዴፓ   

                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                            

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።